TG Telegram Group Link
Channel: Ahadu picture
Back to Bottom
Channel created
​​❤️ጣፋጭ የፍቅር ቃላት❤️

💔የትኛውም የህይወት ፈተና ባጋጠመኝ ጊዜ ባንተ መፈቀሬን ሳስብ ልበ ሙሉነት ይሰማኛል!😍


💘ከማያቸው ሚሊዮን ከዋክብቶች በልቤ ውስጥ ምታንፀባርቀው አንተ ብቻ ነክ!❤️

💝ካንተ ጋር ማሳልፈው እያንዳንዱ ቅስበት ነብሴን በደስታ ትሞላለች!😘

💘በማህላችን ያለው እርቀት ትርጉም የለውም ምክንያቱም በስተመጨረሻ አንተን ስለማገኝ!

💕ሺህ ልቦች ላንተ ያለኝን ፍቅር ለመያዝ ትንሽ ናቸው!💋

💖ትላንት እና ዛሬ የማላውቃትንም ነገን ጨምሬ አፈቅርሀለሁ!💗


┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄

❤️
🍃

┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
💜 ማፍቀር ሀጢአት አይደልም
⇨ ነገር ግን በፍቅር ስም በሰው ስሜት ላይ መጫወት ትልቅ ሀጢአት ነው ።

 ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
❤️♡ ከተብቃቃህ ትንሹ ብዙ ነው ⇨ ከተስገበገብክ ብዙው ትንሽ ነው ⇨ ከወደድክ ሩቁ ቅርብ ነው ⇨ ከጠላህ ቅርቡ ሩቅ ነው ።
 
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
♥️😍ካንቺ የበለጡ ቆንጆዎች እንዳሉ አውቃለሁ ...
⇨ ነገር ግን የወደድኩሽ በአይኔ ሳይሆን በልቤ ነው
•┈┈•••┈┈•🌹•┈┈•••┈┈•
❤️የሚወድህ ሰው
ለራሱ ማድረግየማይችለውን ነገርአንተን ስለሚወድህናስለምያፈቅርህ ብቻለአንተ ግን ያደርገዋል
••┈┈• ♡ ••┈┈•••┈┈•

 ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌹ሁለት ከባባድ ጀግኖች ትግስትና
ጊዜ ናችዉ
 ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄

  ┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈
የመፈጠራችን ዋና ዓላማ ሌሎችን ለመርዳት ነው፤ መርዳት ካልቻልን ግን ቢያንስ አንጉዳቸው።
┈┈┈◦◎ ◎◦┈┈┈

┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈
ጨለማን ጨለማ አይገልጠውም፣ ብርሃን እንጂ፤ ጥላቻንም ጥላቻ አይፍቀውም፣ ጥላቻን ማጥፋት የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው።
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

🔥ክፈል 1

ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
በጠዋት ከ ቅዱስ ጊወርጊስ ቤተክርስቲያን የሚወጣው ህይወትን የሚያለመልም የቅዳሴ ዜማ በጆሮዬ አቀጨለና ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ።ከብርድ ልብሱ ውስጥ ሳልወጣ አይኔን ሸፍኜ ይሔን ጥዑም ዜማ እየኮመኮምኩ ሳለሁ "ዮርዲ ቁርስ ደርሷል" የሚል ድምፅ ከተመሰጦዬ መለሰኝ ።ብርድ ልብሱን ከአይኔ ላይ ቀስ ብየ ስገልጠው መጋረጃውን አምልጣ ሰርጋ ከገባችው የጠዋት ፀሐይ ጋር ተጋጨን።ቢጫ ቀለም ከተቃባው ምኝታ ቤት ጋር ፀሐይ ተደምራ ክፍሉን በብርሀን አሽቆጥቁጣዋለች።"ዋው ደስ የሚል እሁድ "አልኩና ከአልጋየ ላይ ወረድኩ። ................ቁርስ እንደነገሩ ከቀማመስኩ በኋላ አንድ ሲኒ ቡና ፉት ብዬ ወደ ክፍሌ ገባሁና ከውስጥ ዘግቼ ቁጭ አልኩ ።ትንሽ በሀሳብ ስባክን ቆየሁና "ደሳለኝ ያለኝ ነገር እውነት ነው እሱን መስማት አለብኝ" አልኩና በውስጤ ከተቀመጥኩበት በወኔ ተነስቼ ከመሳቢያው ውስጥ እስክሪብቶ እና ወረቀት አወጣሁና በድፍረት ጫር ጫር እድርጌ ወደ ኪሴ አስገባሁት ። ወደ መስታወቱ ተገጠቼ ከምስሌ ጋር ተፋጠጥኩ ።"ድፈር ዮርዲ አንተ እኮ የኔ ወንድም ነህ አንተ እኮ ዮርዳኖስ ነህ ታደርገዋለህ" የደሳለኝ ድምጽ ደጋግሞ ጆሮዬ ላይ ደወለ።በረጅሙ ተነፈስኩ እና መስታወቱ ውስጥ ሆኖ የሚያየኝን የራሴው ምስል "ድፈር ዮርዳኖስ ድፈር ካለመናገር ደጅ አዝማችነት ይቀራል " አልኩት ከሌላ ሰው ጋር የማወራ ያሀል ጮህ ብዬ ።ዛሬ ከየት እንደመጣ የማላውቀው የወኔ ካባ በላዬ ላይ ተደፍቷል ።ግቢያችንን ለቅቄ ጉዞ ጀመርኩ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዮርዳኖስ ተሾመ እባላለሁ ከእናቴ ከ ወ/ሮ አለም አወቀ እና ከአባቴ ከአቶ ተሾመ ታምሩ መስከረም 05,1992ዓ.ም ይችን ዓለም ተቀላቀልኩ ።ለቤተሰቡ ሁለተኛ ልጅ ነኝ አህቴ ቤዛዊት ተሾመ ።በጣም የምወዳት ታላቅ እህቴ ነች በሊትሌቸር ከአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በዚህ ክረምት ነው የተመረቀችው።አባቴ ነጋዴ ነው እናቴ የቤት እመቤት።ኑሯችን ከደብረ ማርቆስ 15 ኪ.ሜ እርቃ ከምትገኘው ትንሿ አምበር ከተማ ነው።ሀብታሞች አይደለንም ድሆችም አይደለንም የጎደለን የለም ።ቤተሰባችን ውስጥ ሁለት ተጨማሪ ሰዎች አሉ።እድሜ ጠገቧ አያቴ እና የቤት ሰራተኛዋ እልፍነሽ።ቤተሰባችን ፍቅር ነው። ፍቅር ማለት የእኛ ቤተሰብ ነው ብል ማጋነን አይሆንም! 2007 ማትሪክ ተፈትኜ ውጤት እየጠበኩ ነው ።ብዙ ጓደኞች አሉኝ።ደሳለኝ ግን ከጓዳኛ በላይ ወንድሜ ነው ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከግቢያችን በስተሰሜን በግምት 100 ሜትር ያክል ከተጓዝኩ በኋላ ከአንድ ትልቅ ግቢ ላይ ደረስኩ።ትንሽ ከአቅማማሁ በኋላ "አብርሃም አብርሃም " ብዬ እንደተጣራሁ ያ እንደ ጦር የምፈራው ምዕታተኛው የሔዋን ድምፅ ማነው አለኝ።መልስ አልመለስኩም ልቤ አታሞውን ይደልቅ ጀምሯል። በሩም ተከፈተ ወኔየን ሰብሰብ አድርጌ ቆምኩ።

ይቀጥላል...

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘______❥❥
😘ሰሜናዊት ሙሽራ🔥

😘ክፍል 2

ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ
.
.
.
"እንዴ ዮርዲ እንዴት ነህ"አለች ሔዋን።
"አብርሀምን ፈልጌ ነበር "አልኳት ሰላምታዋን አልሰማሁም አሉ።
ጉንጬን ዳበስ አደረገችና "ዮርዲዬ ዛሬ ደግሞ ሰላምታ የለም እንዴ ምን ሆንክብኝ የኔ አስቀያሚ ደህና አይደለህም?"አለችኝ እንደመጨነቅ ብላ።"ሒዊ ምንም አልሆንኩም አብርሃምን ማግኘት ብቻ ነው የምፈልገው" አልኳት አይኗን የመሸሽ ያህል ወደ መሬት አቀርቅሬ።ሔዋን ያለመፈለግ ስሜት ተሰማት መሰለኝ ተበሳጭታ መንቀር መንቀር እያለች አብርሀምን ለመጥራት ወደ ውስጥ ገባች። አብርሀም መጣ።ሳቂታው አብርሀም እሱ ማለት ለመሳቅ የተፈጠረ ፈገግ ለማለት ብቻ የሚኖር አይነት ልጅ ነው።
"ዮርዳኖስ እንዴት ነህ"አለ አብሪሽ ፈገግ ብሎ
"ደህና ነኝ ሁሉ ሰላም ነው አይደል"አልኩት
"ሰላም ነው ። በጠዋት ምን ጎርፍ ጣለህ?
"ውይ አብሪሽዬ ስራ ላይ ነበርክ እንዴ?"አልኩት እንደመሳቀቅ ብዬ
"አረ በጭራሽ ምንም ስራ የለኝም ከዚህ በፊት በዚህ ሰዐት መጥተህ አታውቅም ብዬ ነው" አለኝ
"በል እንግዲያስ ስራ ከሌለህ ከለመድነው ቦታ እንሒድ እማማክርህ ጉዳይ ነበረኝ።"አልኩት
"በደስታ ነዋ እሺ የምልህ"አለ አብሪሽ እየሳቀ።ተያይዘን ከለመድንው ቦታ ሔደን ተቀመጥን።ለብዙ ደቂቃዎች ያህል ስንጨዋወት ቆየን እና።"እሺ ወንድም ዮርዳኖስ ለምን ነበር የፈለግከኝ ?"አለኝ
ትንፋሼን ሰብሰብ አድርጌ ለመናገር ተዘጋጀው "ምን መሰለህ እኔ ሔዋንን አ...ፈ...ቅራ...ታለሁ ለብዙ ጊዜ ልነግራት እወስን እና ድፍረት እያጣሁ ወኔ ከእኔ ገሸሽ እያለ ስቸገር ቆየሁ።"አልኩና የማማጥ ያህል ተጨነቄ ተነፈስኩ።ቀና ብዬ አብርሀምን ስመለከት ደነገጥኩ።ምንም አይነት የስሜት መለወጥ አይታይበትም።አልደነገጠም አልተገረመም አይኔ ጋር የሆነ ነገር እንደሚፈልግ ሁሉ አይኖቹን አይኔ ላይ ተክሏል።"እንዴ እንደዚህ ተጨንቄ በመከራ ነግሬው አልሰማኝም ማለት ነው"አልኩኝ በውስጤ።ግራ መጋባቴን የተመለከተው አብርሃም "ዮርዳኖስ ሔዋንን እንደምታፈቅራት አቃለሁ"ብሎኝ እርፍ
"አረ በቂርቆስ አትቀልድ "አልኩት
"እሚቀለድበትን ሰዐት እና ቦታ አውቃለሁ ትንሽ ልጅ አይደለሁም"አለኝ ኮስተር ብሎ
"እና ጠንቋይ ትቀልባለህ ልበል?እኔ እኮ ከ ጓደኛዬ ከደሳለኝ ውጭ ለማንም ትንፍሽ አላልኩም።እንዴት አንተ ልታውቅ ቻልክ?"አልከት
"እሱን በሰፊ ፕሮግራም እናወራለን ።አሁን ከእኔ ምን እንደሚጠበቅ ንገረኝ እና እንለያይ ዝናብ ሊዘንብ ይመስላል"አለኝ ሰማዩን ቀና ብሎ እየተመለከተ።
"አብርሀም ለአመታት ያህል እንደወንድም ከጎኔ ውስጥ ከእቅፌ ላይ የነበረችን ልጅ በድንገት ከፊቷ ቆሜ አፈቅርሻለሁ ለማለት ሞራል አጣሁ።አንተን ማስቸገር ካልሆነብኝ ይችን ወረቀት አድርስልኝ?" አልኩት
"እንዴ ዮርዲ እኔ ሌላ ሰው መሆኔ ነው ካላስቸገርኩህ የምትለኝ በል ስጠኝ እና ልሒድ"አለ አብሪሽ ለመሔድ እየተነሳ
"ወረቀቱን ሰጠሁት እና፤ስማ ደግሞ መልሱን ዛሬ ትፃፍልኝ እና መልስልኝ?"አልኩት
"እሺ መልካም እድል 10:00 እንገናኝ"አለና እየሮጠ ሔደ።ሰዓቴን ተመለከትኩ 6:03 ይላል።ቤት ለምሳ ይጠብቁኛል ብዬ ወደቤቴ አመራሁ።የጠዋቷ ፀሐይ ለውሸት ነበር የወጣችው።ቤት ከመግባቴ ትንሿን የአምበር ከተማ ዶፍ ዝናብ በአፍ እና በአፍንጫዋ ያዳፈት ጀመር።ቤተሰቦቼ በዛሬው ሁኔታዬ ሳይወዛጋቡ አልቀሩም ።ምሳ ቀመስኩ እንጂ አልበላሁም።ምሳ ተበልቶ የምሳ ሰዓቱ ቡና ሲጠጣ እኔ ግን እምቢ ብዬ ክፍሌን ዘግቼ አልጋየ ላይ ጋደም አልኩ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የማይታለፍ ነገር የለም እነዚህ አርባ አመት ያህል ረዝመው ያስጨነቁኝ አራት ሰዓታት በመከራ አለፉና ጉዴን ለመስማት
ከተለመደው ቦታ ቀደም ብዬ ሔድኩ።ከ30 ደቂቃ ጥበቃ በኋላ አብርሀም በ50 ሜትር ርቀት ላይ ሲመጣ አየሁት።የሞት መልዕክት ይዞልኝ የመጣ ይመስል ሳየው ልቤ በአፌ እስክትወጣ ያህል መምታት ጀመረች።

ይቀጥላል

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
😘ሰሜናዊት ሙሽራ🔥

💞ክፍል 3

ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
ከሁለት አመታት በኋላ ..........................

ከሁለት አመት በፊት ያልታየችው ሔዋን ዛሬ ግን መነጋገሪያ ሆነች።ማንም ያላየውን ውበቷን ተመልክቶ በፍቅሯ የተነደፍው እሱ ብቻ ሳለ፤ዛሬ ግን ስር ስር ባዬች በዙ።ጉድ ተባለ ይችን የመሰለች ልዕልት ከዚህ ጋር ምን ትሰራለች አይመጥናትም አይገባትም ተባለ።እውነት ነው ዮርዳኖስ ቆንጆ የሚባል ባይሆንም ለወንድ ልጅ የሚገባውን ያህል ደስ የሚል ልጅ ነዉ።ፍቅራቸው ያስቀናል ።ማንም ምንም ቢያወራ ሔዋን እኔ የ ዮርዳኖስ ነኝ ከእሱ የሚለየኝ ሞት ብቻ ነው አለች።ዛሬ ሐምሌ 13 ነው ከሔዋን ገር ፍቅር ከጀመሩ ሁለተኛ አመታቸውን እያከበሩ ነው።ሁለቱም 12ኛ ክፍል ተፈትነው ውጤት እየጠበቁ ነው።ዮርዳኖስ ሶሻል ሳይንስ እርሷ ደግሞ ናቹራል ሳይንስ ነበር የገቡት ።
"ኩራተኛዋ ልዕልት"አለና ዮርዳኖስ ጉንጯን ሳም አደረገጋት።
"ማነው ባክህ ኩራተኛ ያደረገኝ፤እኔ እንደሆኩ ማንንም የማላስከፋ ሩህሩህ ልብ ነው ያለኝ"አለች የጉንዮሽ ስርቅ አድርጋ እየተመለከተችው።ዮርዳኖስን ለማስቀናት ሁሌ የምትናገራት ሽሙጥ መሆኗ ነው።
"እሱን ተይውና ኩራተኛማ ነሽ።ያኔ እስረኛ ክፍል እያለን ለአብርሃም የላኩልሽን ደብዳቤ ምን ብለሽ ነበር የመለስሽልኝ?"አላት
ከአፉ ቀለብ አደረገችና"እኔ ለአንተ መሆን አልችልም አቻህን ፈልግ ደፋር !"አለችና ሳቀች።መቼም ስትስቅ እንኳን የአፍቃሪዋን የጠላቷንም ልብ ያስደነግጣል ።
"ግን ምን አስበሽ ነበር?"አለ
"አንተ ደግሞ፣የሴት ወግ መሆኑ ነዋ በአንድ ጥያቄ እሻ ያለች ብቸኛዋ ሴት እንድባል ፈልገህ ነው እንዴ?"ቀጠለች እና "ደሳለኝ አይመጣም እንዴ?"አለች
"አረ የሱን ነገር ተይው" አለ እንደመሳቅ ብሎ ።
"ምነው ምን ብሎ አናደደህ ደግሞ"አለች ለመስማት እየጓጓች
"አንድ ቀን አነሱ ቤት ደርሰን ስንመለስ ፡አንዲት ቆንጆ ልጅ ከሆነ ሰው ጋር ቆማ ስትሳሳም ተመለከትን።"
"ከዚያስ?"አለች ሔዋን
"ከዚያማ ሞን ቢለኝ ጥሩ ነው "ይቺ ደግሞ ከዚህ ቦርኮ ጋር ምን ትሰራለች አለኝ።እኔም ምነው ዋናው ነገር መፋቀራቸው ነው አልኩት ።ቀለብ አደረገና ፍቅር እውር ያደርጋል የሚባለውን ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ አረጋገጥኩ ።አለኝ"
"አንዴት? አልኩት።
"ምን እንዴት አለው እያየኸው ይቺ ቆንጆ ከዚህ ጉርድ በርሜል ጋር፤ሌላኛው የእኔው ጉድ" አለና በስርቆት አየኝ
"ምን ለማለት ፈልገህ ነው ?አልኩት
"ያው አንተ ከሔዋን ጋር ማለት ነዋ"አለና መናደዴን ሲመለከት "ያሉትን ነው"አላለኝም መሰለሸ።
ሔዋን ልቧ እስኪፈርስ ሳቀች እና "በቃ እሱ ግቢ ሔዶ ከመጣ በኋላ ስራው ሁሉ አንተን ማናደድ ሆነ አይደል"አለች ያልጨረሰችውን ሳቋን ለመጨረስ የምትስቅ በሚመስል መልኩ ደግማ እየሳቀች።
"አንቺማ ሳቂ የእኔ አስቀያሚ"አለና ሳም አደረጋት
"በቃ ማታ ከደሳለኝ ጋር ሆነህ ላግኝህ ልደታችንን እናከብራለን"አለች እና ፍዝዝ አለች
"እሺ የእኔ እመቤት ታዛዥ ነኝ የልደት ስጦታዬን እንዳትረሺ"አለ ዮርዳኖስ
"በደምብ ነው ያለህ የዛሬው ልዩ ነው"አለች ፍዝዝ እንዳለች።
ሁኔታዋ አላመረውም ።እንደዛሬው ሁና አይቷት አያውቅም።ከተገናኙ ጀምሮ በስስት ነበር የምትመለከተው።
"እሺ በቃ ግቢ፤ የማታ ሰው ይበለን"ብሎ ከንፈሯ ጋር ማህተም አስቀመጣና ምን ሆና ይሆን እያለ እያሰላሰለ ወደቤቱ ገባ።

ይቀጥላል

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

💞ክፍል 4

ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ
.
.
.
ዮርዳኖስ ቤት ሲገባ ደነገጠ አፉን ከፍቶ ቀረ።ቤቱ በዲም ላይት አሸብርቋል ።ከበሩ ፊት ለፊት የ ዮርዳኖስ እና የሔዋን ፎቶ በትልቅ መስታወት ተንጠልጥሏል።ከላይ እንኳን ለሁለተኛ አመት የፍቅር ጅማሪያችሁ አደረሳችሁ።የሚል ወረቀት ተለጥፏል።ልቡ ተሸበረ።"ዛሬ የሚፈጠር ነገር አለ እንጂ ካለነገር ልቤ አልፈራም፤ሔዋንም ልክ አልነበረችም"አለ በውስጡ ።እህቱ ቤዛ ወደ ሳሎን ገባች እና "ሰርፕራይዝ"ብላ ከሃሳቡ አባነነችው።
"በቃ ስራ አጥ መሆን እንደዚህ ነው የሚያደርገው? ለአንቺ ስራ ፈጠራ መሆኑ ነው አይደል?እስኪ ይሔን ሁሉ ለደከምሽበት ምንያህል ክፍያ ነው የምትጠይቂኝ?"አለ ዮርዲ ለመቀለድ
ቤዛ አኮረፈች እና ተመልሳ ወደ እናቷ ሔደች ።
"አንተ ምላሳም ሰምቼሃለሁ!አንተን ለማስደሰት ይሔንን ሁሉ ደክማ እንደዚህ ነው መልስህ?"አለች ወይዘሮ አለም እየሳቀች ።
እውነት ነው ቤዛዊት ከተመረቀች ድፍን ሁለት አመት ሞላት።ስራ የሚባል ነገር የለም።ከአባቷ ከአቶ ተሾመ ጋር ንግዱን እያጦጧፈችው ነው።አሁንማ ተስፋ ቆርጣ የስራ ማስታወቂያ ማየት ካቆመች ስድስት ወር ሞላት አረ አንዲያውም የተመረቀችበትን የትምህረት መስክ ሁሉ ሳትረሳው አልቀረችም ።
ዮርዲ ጓዳ ሲገባ እናቱ ምግብ በመስራት ተጠምዳለች።ቤዛ ደግሞ ለምቦጯን ጥላ ተቀምጣለች።
"አንቺ ደግሞ ሰው መቀለድ አይችልም እንዴ?"አለ ዮርዲ ፀጉሯን እንደ ህፃን ልጅ እዬደባበሰ
"አንደኛ ስራ አጥ አትበለኝ፤ሲቀጥል እኔ ስራ አጥ አይደለሁም ነጋዴ ነኝ አሺ።"አለች ኮስተር ብላ።
"እስኪ በእኔ ሞት በስነፅሁፍ ተመርቆ ነጋዴ አይከብድም " አለት ዮርዲ።
"አሱን ከጥቂት አመታት በኋላ በእኔ ቦታ ስትሆን ትነግረኛለህ ወሬኛ"አለች ቤዛ
"አንተ ስራ ፈት ሒድ ወደ ክፍልህ አባትህ እቃ አስቀምጦልሀል"አለች ወይዘሮ አለም
"እእእ ስራ ፈት ብለውማ የሰው ሞራል አይንኩ ወይዘሮ አለም"አለና ጓዳውን ለቆ እየወጣ ዞር ብሎ ቤዛን አየት ሲያደርጋት ነጠላ ጫማዋን አውልቃ ጀርባውን አቀመሰችው።ሳሎኑን አቋርጦ ወደ ክፍሉ እየሮጠ ገባ።
"ደግ አደረግሽ ትንሽ ምላሱን አርፈን እንቆያለን"አለች እና ወይዘሮ አለም ተሳሳቁ።
ዮርዳኖስ ክፍሉ ሲገባ አልጋው ላይ አዲስ ልብስ ተቀምጦለታል።ዋው አለና አንስቶ ተመለከተው።ሰማያዊ ጅንስ ሱሪ እና ብሉ ብላክ አጀ ጉርድ ሸሚዝ።የለበሰውን ሸሚዝ አወለቀ እና አዲሱን ሸሚዝ ለበሰው ።ወደ መስታወቱ ተጠገና ራሱን እየተመለከተ ቁልፎችን ቆለፋቸው።
"አንተ ያበደ ነው ሸበላ ነው የሆንከው
"አለች እልፍነሽ በመስኮት ታይ ኖሯል ልብስ እያጠበች ።
"አረ ተይ አልፊቱ አታሹፊብኝ" አለ ዮርዳኖስ
"አባቴ ይሙት ጋሼ ምርጫ ይችላሉ"አለች እልፍነሽ
"አንቺ ግን እስከ አሁን አጥበሽ አትጨርሽም እንዴ? የዛሬው ደግሞ ከአስራ ሁለት እስከ አስራሁለት ሰዐት ነው እንዴ አጠባው"አለ ዮርዲ
"ምን ባክህ ኬኩን ላዝዝ ሔጄ ነበር ለዛ ነው"አለችው
"የምን ኬክ ነው ቆይ እናንተ ሰዎች እንዴ ዛሬ ምን የተለየ ነገር አለ።እኔና እሷ እኮ የምናከብረው እዛው ከምንገናኝበት የሾላ ዋርካ ላይ ነው።"አለ ተገርሞ
"በል ስራ አስፈታኸኝ" ብላ ወደ ልብስ አጠባዋ ገባች።እሱም መዘነጡን ተያያዘው ።አባቱ የገዛለትን ሱሪ ለበሰው እና አጁን ወደ ኪሱ ሲከተው ኪሱ ውስጥ የሆነ ነገር አገኘ።በፍጥነት አወጣው እና ሲመለከተው ትንሽ ካርቶን ነች።ከፈተው።ውስጡ ሀብል ነበር ።ከካርቶኗ አወጣ እና ሲያይ ተንጠልጣዩ ጋር ኤች H ፊደል አለ።እንዴ "አባዬ ስሜ ጠፋበት እንዴ?" አለና አንገቱ ላይ አንጠልጥለው።ዝንጥ ብሎ ከክፍሉ ወጣ እና ወደ ጓዳ ተመለሰ።
"ትፍ ትፍ ከአይን ያውጣህ ልጄ! አንተ 18ኛ አመትህን እንኳን ስታከብር እንደዚህ አልዘነጥክም።"አለች እና እናቱ ግንባሩን ሳም አደረገችው
"ዛሬ ምሳ ሰዓት የለንም እንዴ 9ኝ ሰዐት አየሆነ እኮ ነው"
"ምነው ራበህ እንዴ" አለች ወይዘሮ አለም
"አይ እንደሱ እንኳን አይደለም ግን አባዬም የለም ብዬ ነው"አለ
"አባትህ እስኪመጣ እኔም እጨርሳለሁ ሒድ ለደሳለኝ ደውልለት የእሱም እቃ ተቀምጦለታል ቤዛ ክፍል አለልህ"አለች ወይዘሮ አለም ።
ዮርዳኖስ ግራ ተጋባ "ቆይ እነዚህ ሰወች ምን አስበው ነው?" ይሔ ሁሉ ሽር ጉድ ምንድን ነው።እናቱ ብዙ የድስት አይነት ደርድራለች ።ማህበር ያለ ነው ያስመሰለችው ።እንዲህ እንደተወዛገበ ወደ ሳሎን ሔደና ለደሳለኝ ደውሎ አሁን እንዲመጣ ነግሮት ወደ ቤዛ ክፍል ሔደና ለደሳለኝ የተቀመጠለትን እቃ አየው። ገረመው የእሱን አይነት ልብስ ነበር የቀመጠው ።ወደ ክፍሉ ይዞት ሔዶ ተቀመጠ።የ ዮርዳኖስ አባት የሁለቱን ጓደኛሞች ፍቅር ሲያወራ ውሎ ቢያድር አይጠግብም።በሁለቱ ልጆች ምክንያት ቤተሰቦቻቸው ተዛምደዋል። በእድሜ ደሳለኝ አመት ይበልጣል። ደሳለኝ ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ በሶፍትዌር አንድ አመት አስቆጥሮ ነው የመጣው።ዮርዲ ደግሞ ዩኒቨርስቲ ለመግባት ውጤት እየጠበቀ ነው።
ቀና አለና ከግድግዳው ጋር የተሰቀለውን የሔዋንን ፎቶ ተመለከተ ።"የእኔ ልዕልት ሺ አመት ኑሪልኝ"አለ ፎቶዋ ላይ እንዳፈጠጠ።
ሔዋን ቀይ መልክ ያላት፣አፍንጫዋ ሰልከክ ብሎ የወረደ፣ጥርሶቿ በስርዓት የተቸመቸሙ እና ብርሀን የሚፈነጥቁት አይኖቿ ዛጎል የሚያካክሉ ሲሆኑ ፀጉሯ ከጀርባዋ ላይ ወርዶ ወርዶ እንደቄጠማ የተነሰነሰ ጡቶቿ የአራት መከራክር ተራራን መስለው የተቀሰሩ።አጠር ያለ ቁመና ያላት እና እና ቀጠን ያለች ሰትሆን ወገቧ ችቦ አይሞላም ወገቧ ተብሎ የተዘፈነላት አይነት ሴት።በአጠቃላይ ውብ የሆነች እንስት ነች።
"አንተ እስከ አሁን አበባውን አልገዛኸውም "አለና ደሳለኝ ዮርዳኖስን ከሀሳቡ አባነነው።


ይቀጥላል

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

❤️ክፍል 5

ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
"አፈር ብላ ጥላ ቢስ ሳታንኳኳ ትገባለህ እንዴ?"አለ ዮርዳኖስ
"ሙሽራው ዘንጠሀል ዮርዲ ሙት እንዴት እንዳመረብህ"አለ ደሳለኝ "ባክህ ይሔንን ልበስ እና ማን እንደዘነጠ ትነግረኛለህ።"አለና ዮርዳኖስ አባቱ የገዛላቸውን ሰጠው ።" አረ በለው ማች ማድረግ ግን ፋዘርየ ተቸገሩ" አለ የለበሰውን ልብስ አውልቆ አዲሱን እየለበሰ።
"አሱን ተወው እና በዚህ ተበልጠሀል" ብሎ ዮርዳኖስ ሀብሉን ከሸሚዙ አውጥቶ አሳየው ።
"አንተ ምን ነክቶህ ነው አሱን እኮ ለሔዋን እንድትሰጣት ነው ፋዘርየ የገዛው ፍጠነህ አውልቅ"አለ ደሴ እየሳቀ
"አንተ ደግሞ ይሄን የት አወቅክ? እኔ እኮ ኤች ፊደል ምንድን ነው እያልኩ ነበር ለካ ሔዋን! ነው ምን አይነት ቀሽም ነኝ በናትህ "አለ ዮርዲ ።
"ስማ ፋዘርየ በቃ ብቸኛ ወንድ ልጅ ስለሆንክ እንደዚህ ያቀብጥሀል የእኔ አባት ቢሆን እንኳን ፍቅር የጀመርኩበትን ሊያከብርልኝ እንዳፈቀርኩ ስነግረው ነው ገና ከቤተሰቡ ዜግነቴን የሚነጥቀኝ ።"አለ ደሳለኝ እየሳቀ።ደሳለኝ ለብሶ ጨረሰ እና ወደ መስታወቱ ተጠጋ "እ ዮርዲ እንዴት ነኝ ?"አለ
"ዘናጭ ቁጥር አንድ፤አንተ እኮ ቅጠል ብትለብስም ያምርብሀል"
ብሎ እንደተናገረ አቶ ተሾመ ገባ ።"በለው ውበት መንታ ልጆች መሰላችኋል" አለ
"እንዴ ምንድን ነው አባዬ ራስህን ተመልክተሃል?ቆይ ምንድን ነው ነገሩ ግራ አጋባችሁኝ"እኮ አለ ዮርዲ የአባቱን ሱፍ እያደነቀ
አቶ ተሾመ ሳቀና የያዘውን ሽቶ በላያቸው ላይ አርከፈከፈው ።
"በሉ ወደሳሎን ኑ ምግብ ቀርቧል።"ብሎ ትቷቸው ወደ ሳሎን ሔደ።
"ደሴ የምታውቀው ነገር ካለ ንገረኝ ሰው ሁሉ ምን ሆኗል?"አለ ዮርዲ
"በል ነገር አትፈልፍል ምሳ አልበላሁም መብላት እፈልጋለሁ"አለ ደሳለኝ
"የዛሬ ምሳ በመክሰስ ሰዐት ሆኗል"አለና ወደ ሳሎን ሲገቡ ወለሉ በቄጠማ አብዷል ።ቤዛ እና ወይዘሮ አለም ተመሳሳይ ጥልፍ ያለው ጥበብ ለብሰዋል ።እድሜ ጠገቧ አያቱ የሀበሻ ቀሚስ ለብሰው ሶፋ ጋር ተቀምጠዋል ።እልፍነሽ እንደነገሩ ዘንጣ ረከቦቱ ጋር ተቀምጣለች።ዮርዲ እና ደሴ የዮርዳኖስን አያት ጉልበታቸውን ስመው ተመርቀው ወደ ምግብ ጠረጴዛው ሔደው ከእነ ቤዛ ጋር ተቀላቀሉ ።ወይዘሮ አለም ወደ ደሴ ጆሮ ጠጋ ብላ "መልዕክቴን ለእናት አባትህ አድርሰሀል?"ብላ አንሾካሾከች ።
ደሳለኝ አዎንታውን በምልክት ለገሰ።
ዮርዳኖስ አሻግሮ ሲመለከት ሶስት ካሳ ቢራ ተደርድሮ አየ።"አንተ ደሴ ምንድን ነው ከእኔ የተደበቀው?"አለ ዮርዳኖስ ደሴን ተጠግቶ
"ሊያገባ ነው "አለ ደሴ
"ማነው የሚያገባው ?"አለ ዮርዲ ደንግጦ
"አቶ ተሾመ "አለና ደሴ ሳቀ። አነጋገሩ ስለገረመው ዮርዲ እየተናደደ ቢሆንም ሳቀ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ምግብ አንደነገሩ ተቀማመሰ እና እልፍነሽ ቡና ልታፈላ ጉድ ጉድ ማለት ጀመረች ።በር ተንኳኳ ። እልፍነሽ ልትከፍት ሔደች
"ቤት ለእምቦሳ"ብለው የደሴ ቤተሰቦች ገቡ ።
"እምቦሳ እሰሩ "ብለው የዮርዳኖስ ቤተሰቦች ሰላምታ ተለዋውጠው ቦታ ስጥተው አስቀምጧቸው ።
"ሙሽራው ና እስኪ ይሔን አስቀምጥ"አለና የደሴ አባት አቶ ሀብቴ የተጠቀለለ ጠርሙስ ለዮርዲ ሰጠው።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
"አንተ ደሴ 11:30 ሆነ እኮ ሔዋንን እናግኛት"አለ ዮርዲ
"ተረጋጋ ሰዓት አለን ፥ደግሞ ደውላልኝ ነበር ስትጨርስ እንደምትደውል ነግራኛለች።"አለ ደሴ
"እሺ አንተ ግን እኛ ላይ ነው የምታድረው።ያንን ቢራ አመድ ስናደርገው ነው የምናድር።መቼም ምክንያቱ ባይገባኝም ድግስ ተደግሷል ድግሱን ትተህ አትሔድም "አለ ዮርዲ
"ትጠራጠራለህ እንዴ የትም አልሔድም። ሰማ ሳልረሳው ሔዋን የግጥም ደብተርህን አዘጋጅተህ አስቀምጥልኝ ብላለች" አለ ደሴ
"ምነው ለምን ፈልጋው ነው"
"ዘልዛላ ነው በስነ ስርዓት አያስቀምጥም "አለችኝ አለ ደሴ
"አትዋሻ !"አለ ዮርዲ
"ዮርዲ ሙት እንደዛ ነው ያለችኝ"አለ ደሴ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከደቂቃዎች በኋላ የግቢ በር ተንኳኳ ።እልፍነሽ ሔዳ ከፈተችው።
ቤት ውስጥ የነበሩ አይኖች በሙሉ ወደ በሩ ተወረወሩ ።
ዮርዳኖስ ግን አፉን ከፍቶ ቀረ።
"ደሴ ህልም ነው በለኝ ምንድነው የማየው"አለ እየተንተባተበ።

ይቀጥላል

@Ethio_leboled #Share
❥❥______________❥❥
😋ሰሜናዊት ሙሽራ😋

💞ክፍል 6

ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
"ደሴ ህልም ነው በለኝ።ምንድን ነው የማየው?"አለ ዮርዲ እየተንተባተበ ።
"ሙሽራው አታስፎግራ ቀብረር ብለህ ቁም።ቤተሰብ ትውውቅ መሆኑ ነው"አለ ደሴ ዮርዳኖስን ጠጋ ብሎ
"የምን ቤተሰብ ትውውቅ ?እኔ የሔዋንን ቤተሰቦች አላውቃቸውም?ወይስ የእኔ ቤተሰብ ሔዋንን ከእነ ቤተሰቧ የማያውቅ መሆኑ ነው?አንድ ሰፈር ውስጥ ለብዙ አመታት እኮ ኖረናል።ደሴ አባዬ ምን እያደረገ እንደሆን ምንም ሊገባኝ አልቻለም።"አለ ዮርዲ
"አንተ ፈገግ በል ሔዋን እያየችህ ነው አታስደብራት"አለ ደሴ
ዮርዳኖስ የግዱን ፈገግ ብሎ ለቤተሰቡ ሰላምታ ሰጠ።ሁሉም ቦታ ቦታውን ይዞ ተቀመጠ።የደሳለኝ እናት አና አባት አንድ ሶፋ ላይ፣የሔዋን ቤተሰቦች አብርሀምን ጨምሮ ሌላ ሶፋ ላይ ።ደሴ፣ዮርዲ እና አቶ ተሾመ አብረው ተቀምጠዋል።ቤዛና ወይዘሮ አለም መስተንግዶውን ተያይዘውታል ።እልፍነሽ ቡናውን እያደራረሰች ነው።
ዮርዳኖስ በሀፍረት ሽምቅቅ እንዳለ ቀና ብሎ ሔዋንን ተመለከታት ።በጥበብ አሸብርቃ ሙሽሪት መስላለች።"ሺ አመት ኑሪልኝ የእኔ ልዕልት።"አለ በውስጡ ።አይኑን ከእሷ ላይ መንቀል አልቻለም።የእሱ አልመስልህ አለችው ።ደሴ በጫማው እረገጠ እና "አረ ፍሬንድ ንቃል ምንሼ ነው "አለ ደሴ
"ወይ አፈጠጥኩ እንዴ "አለና በሀፍረት አንገቱን ደፋ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ቡናው ተጠጥቶ፣ምግቡ ተበልቶ አሁን ቢራ ተከፍቶ ጨዋታው ደርቷል ።አቶ ተሾመ ደሴን አጁን ይዞ ወደ ኮሪደሩ ወሰደው እና የሆነ ነገር አንሾኳሽከው ተመለሱ።አቶ ተሾመ ሔዶ ሲቀመጥ ደሴ ከምግብ ጠረጴዛው አጠገብ ቆመና አጨበጨበ።ጆሯችሁን አውሱኝ ለማለት ነበር።ሁሉም በፀጥታ ወደ ደሳለኝ ዞሩ።
"በመጀመሪያ ጥሪያችንን አክብራችሁ ስለመጣችሁ በአቶ ተሾመ እና በወይዘሮ አለም ስም ምስጋናየን አቀርበዋለሁ ።"ጭብጨባ ተከተለ።
"በመቀጠል ወንድሜ ዮርዳኖስ እንዲሁም እህቴ ሔዋን እንኳን ለሁለተኛ አመት የፍቅር ጅማሪያችሁ አደረሳችሁ እያልኩ ኬኩን እንድትቆርሱ እጋብዛችኋለሁ ።"አለ ደሴ ።ሔዋን እና ዮርዲ በጭብጨባ ታጅበው ወደ ምግብ ጠረጴዛው አመሩ።ኬኩን እየቆረሱ ቤዛ ፎቶ አነሳቻቸው ።ደሳለኝ ምስጋና አበርክቶላቸው ወደ መቀመጫቸው ሸኛቸው ።
"በመቀጠል ወንድሜ ዮርዳኖስ ለሔዋን ስም እንዲያወጣላት እና አንዲዘፍንላት ።እጋብዛለሁ ።"አለ ደሴ ።ጭብጨባ ተከተለ ።
ዮርዲ ያላሰበውን ዱብዳ ነገር ደሴ ሲያወርድበት በድንጋጤ ድርቅ ብሎ ቀረ።ሁሉም መነሳቱን እየጠበቁ እንደሆነ ሲመለከት የግዱን ፈገግ ብሎ ተነሳ ።
"እሺ በቅድሚያ ለዚች ልዕልት ልጅ ስም እንድታወጣላት ዕድል ሰጠሁህ "አለ ደሴ እየሳቀ
ዮርዲ በድንጋጤ ብዛት አፍንጫው ላይ ችፍፍ ያለውን ላቡን በእጁ ሞዠቀ እና መናገር ጀመረ።
"በመጀመሪያ ያላሰብኩት ነገር ስለተፈጠረ መደንገጤን አልክድም ። እንደዚህ አይነት ፕሮግራምም ሰርፕራይዝም አጋጥሞኝ አያውቅም ።ሁላችሁንም ላመሰግን እወዳለሁ ።ሲቀጥል ለዚች እንደ ከዋክብት ለምታበራ ልጅ የሚመጥናት ስም ባይኖረኝም "ሳልዕሳዊት"ብየ አውጥቼላታሉሁ "አለ ዮርዲ
"ትርጉም "አለ ደሴ እየሳቀ
"ትርጉሙ ሶስተኛዋ ማለት ነው "አለ
"ሶስተኛዋ ምን?"አለ የሔዋን አባት አቶ አንድነት
ደሳለኝ ቀለብ አደረገና "እንግዲህ እኔ ሲመስለኝ በአስራ ስምንት አመት ውስጥ ያፈቀራት ሶስተኛዋ ሴት መሆኑ ነዉ።"አለና ሳቀ።የእሱን መሳቅ ተከትሎ ቤቱ በሳቅ ተናጋ።
ዮርዲ ሳቁ ጋብ እስኪል ጠበቀና"እንተ ብቻችንን ስንገናኝ ትነግረኛለህ"አለ ዮርዲ ደሴን በፍቅር ጎሸም አድርጎ ።ቀጠለና"ሔዋን ማለት ለእኔ ከእናቴ እና ከእህቴ ቀጥሎ ያገኘኋት ሶስተኛዋ ሴት ነች ።ስለዚህ ሳልዕሳዊት ።ተናግሮ ሳይጨርስ ጭብጨባ ቀደመው ።
"ዝፈንላት ላላችሁት ሁለት አመት ሙሉ ዘፍኜላት ክር ጨርሻለሁ ።እንደማፈቅራት ንገሩልኝ" አለና ሀብሉን ከደረት ኪሱ አውጥቶ ሔዶ አንገቷ ላይ አደረገላት እና ግንባሯን ሳም አድርጎ ወደ መቀመጫው ተመለሰ።ጭብጨባ ተከተለ።
"አሁን ደግሞ ለአቶ ተሾመ መድረኩን እለቃለሁ ።"አለና ደሴ እየሳቀ ወደ ቦታው ተመለሰ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አቶ ተሾመ ተነሳና መናገር ጀመረ ።"በመጀመሪያ ልጄ ዮርዲ ላመሰግንህ እወዳለሁ ።በአንተ ምክንያት ከሁለት ቤተሰብ ጋር ተዛምጃለሁ።ከሔዋን ቤተሰቦች እና ከደሴ ቤተሰቦች።እኔ እና የሔዋን አባት አቶ አንድነት ተመካክረን ስጦታ ገዝተናል ።እሱም ምንድን ነው እ....እንግዲህ ልቦቻችሁ በፍቅር ተሳስረዋል ።እኛ ደግሞ በቀለበት ልናስተሳስራችሁ ወደድን።"አለና የቀለበት ፓኬቱን ለዮርዳኖስ ሰጠው ።
ቀለበቱን አጠለቀላት እሷም እንደዚሁ ።ቤቱ በዕልልታ እና በጭብጨባ ድብልቅልቅ አለ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ፕሮግራሙ ተጠናቀቀ ።የደሳለኝ ቤተሰቦች እና የሔዋን ቤተሰቦች አመስግነው ወደ እየቤታቸው ተበተኑ ።
ሔዋን፣አብርሃም እና ቤዛ ስፕራይት ይዘው ደሳለኝ እና ዮርዳኖስ ደግሞ ቢራ እየጠጡ።የዮርዳኖስን ክፍል በአንድ እግሯ እስክትቆም ድረስ በሳቅ በጨዋታ አመሹ ።
ሔዋን ስልኳን ተመለከተች 3:08pm ይላል ።"እንግዲህ ሸኙን ሊነጋ እኮ ነው"አለች እየሳቀች
"ገና በሶስት ሰዐት "አለች ቤዛ
"አይ መሽቷል ይሒዱ" አለና ዮርዲ ተነሳ ።ከመሳቢያው ውስጥ ደብተሩን አወጣና "ይሔዉ አዘጋጅ የተባልኩት የግጥም ደብተር"አለና ለሔዋን ሰጣት ።
ተቀበለችው እና በተራዋ አብርሀምን ፖስታ ተቀብላ"ይሔው ስጦታየ "ብላ ለዮርዲ ሰጠችው ።
መሳቢያው ውስጥ አስቀመጠው ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ደሳለኝ እና ዮርዳኖስ ሔዋንን እና አብርሀምን ይዘው እነ ሔዋን በር ደረሱ ።ሔዋን መጀመሪያ ደሴን አቅፋው ደህና አደር አለች እና ወደ ዮርዲ ተመለሰች ።
ዮርዲ ትክ ብሎ ተመለከታት ።እነኛ ውብ አይኖቿ እንባ ቋጥረዋል።
"ምነው እማ ምን ሆንሽብኝ"አለ እንባዋን እየጠረገላት
"ደስ ስላለኝ ነው "አለችው እና ከንፈሩን በከንፈሯ ከደነችው ።
አንገቱ ውስጥ ሆና "ጠብቀኝ"አለችው
"እማ ግን ደህና ነሽ ?"አለ ዮርዲ
"ፖሰታውን ነገ ክፈተው "አለች እና ጥብቅ አድርጋ አቅፋው" ደህና እደር "ብላ እያለቀሰች ከአብርሃም ጋር ተያይዘው ገቡ።

ይቀጥላል

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

🔥ክፍል 7

ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
ከአስር አመት በፊት .....................................
ከኮረብታማው ጥንታዊ አምበር ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ግርጌ ድሮ በጣሊያን ወረራ ጊዜ በጣሊያን ይዞታ ውሰጥ የነበረው እና ጣሊያን በአባት አርበኞች ድባቅ ተመታ ሴራዋ ተንኮላሽቶ አፍራ ስትመለሰ ስራ ያቆመው የድንጋይ ወፍጮ እና ሴራሚክስ አምራቹ ሰፊ ግቢ በ1999 ዓ.ም እደሳ ተደርጎለት ስራ ጀመረ ።ባላ ሀብቱ ከአዲስ አበባ መጥቶ የገዛው ሲሆን ስሙ ኢሳያስ ተ/አረጋይ ይባላል ።የደብሩ አስተዳዳሪ እና ጠባቂ የአባ ቶማስ ዘመድ ነው አሉ እየተባለ ጭምጭምታ ይሰማል ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ጥንታዊው አምበር ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን የተመሰረተው ሁለቱ ወንድማማቾች ማለትም አብርሀወአጵብሀ ወይም ኢዛና እና ሳኢዛና ኢትዮጵያን ይገዙበት በነበረበት ዘመን ክርስቶስ ከተወለደ 300 አመት ገደማ እንደተመሰረተ አባቶች ይናገራሉ።ቤተ ክርስቲያኗ በግራኝ አህመድ ወረራ ጊዜ የጥፋቱ ገፈት ቀማሽ እንደሆነች እና እንደተቃጠለች አንዳንድ የታሪክ መፅሐፍት አና አፈ ታሪኮች ያስረዳሉ።ከዚህ በተጨማሪ ግን ለአካባቢው ማህበረሰብ እንቆቅልሽ ሆኖበት እየኖረ ያለው ነገር ከደብሯ በሰተ ደቡብ በኩል ያለው ሰፊው ኮረብታማ ቦታ ነው።ቦታው አጅግ የሚያስገርም ከመሆኑ በተጨማሪ ሲቆሙበት የሚያሰማው ድምፅ ለእንግዳ ሰው በድንጋጤ ይገድላል።ቦታው ሲረግጡት የሚያወጣው ድምፅ ከከበሮ አይተናነስም ።ህብረተሰቡ ውስጡ ዋሻ ሰለሆነ ነው አንደዚህ የሚጮኸው ይላሉ ።እውነት አላቸው።አዎ ዋሻ ነው ማረጋገጫው ደግሞ ከኮረብታው ምስራቃዊ አቅጣጫ ወረድ ብሎ ለዋሻው መግቢያ ተብሎ የተሰራ በሚመስል መልኩ ቅርፅ አልባ መስኮት መሳይ ቀዳዳ አለ።በተለምዶ የዘንዶው ዋሻ በር ተብሎ ይጠራል። ጥንት አባቶች እና እናቶች ንብረታቸውን ከጠላት ለማሸሽ የቆፈሩት ዋሻ ነው ይባላል ።ወስጡ መንፈሳዊ የሆኑ እና መነሰፈሳዊ ያልሆኑ ሀብቶች እንደተደበቁ እና በዘንዶ እንደሚጠበቅ ሰፊው ማህበረሰብ ብትጠይቀው የሚሰጥህ መልስ ነው።ወደ ውስጥ ግን ማንም አልገባም ማንም ሊገባ አልሞከረም።ምክንያቱም የዘንዶ እራት መሆን የሚፈልግ የለም።እየተባለ ይወራል።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከአምስት አመት በፊት ........................
የሔዋን ትልቅ ወንድም የአቶ አንድነት የግል ልጅ ምናሴ አንድነት ይህን የጥንታዊ ቅዱስ ቂርቆስ አስገራሚውን ኮረብታማ ቦታ ጎብኝቶ የተመለሰ ማግስት የውሀ ሽታ ሆነ።የአካባቢው ኗሪ የዮርዳኖስን ቤተሰቦች ጨምሮ ምናሴ የት ደረሰ ብለው ጠየቁ።የሔዋን ቤተሰቦችም ምናሴ ዲቪ ደርሶት አሜሪካ ሔደ ብለው ተናገሩ ።ኗሪው የአቶ አንድነት ልጅ አሜሪካ ሔደለት ብለው የአቶ አንድነትን ቤት በድግስ አስጨንቀውት ሰነበቱ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከአንድ አመት በፊት .....................................
"እሰኪ ስለ ስደት ምን ትያለሽ ?"ሲል ሔዋንን ዮርዳኖስ ጠየቃት
"ህዝባችን እኮ ኑሮን ለማሸነፍ ቤተሰብ ለመርዳት ራስን ለመለወጥ ብሎ ከእናት ሀገሩ እየወጣ በበረሃ የጊንጥ ሲሳይ በባህር ደግሞ የአሳ ነባሪ እራት እየሆነ ፣ገሚሱ ደግሞ አልሳካለት ብሎ ተጠርዞ ሲመለስ ተስፋ ቆርጣ ፤የዚች ምስኪን ሀገር እጣፈንታ እርሱ ትክሻ ላይ መሆኗን ዘንግቶ በሱስ እየዳከረ የሱን ህይወት አባላሽቶ እሱን እያዩ ለሚያድጉ ታናናሽ እህት እና ወንድሞቹ ነገን እንዳያዩ የአይን ቆብ ሆኖባቸው የተሸከመውን የሀላፊነት ቀንበር ከ ጫንቃው ላይ ጥሎ ለቤተሰብም ለሀገርም ሸክም ይሆናል።ተሳክቶለት የወጣውም በአፍ ብቻ እናት ሀገሬን እወዳታለሁ።ከማለት ውጭ ለዚች ሀገር ምን የፈየደላት ነገር አለ?እንዲያውም የዚች ምስኪን ሀገር ጥሪት ሊያጫርስ ከነጫጭባ ፈረንጅ ባላንጣ ጋር ሆኖ ለወጥመዱ ሽቦ ሲያቀብል ይውላል። እስኪ የእኔን ወንድም ምናሴን ተመልከት ።ለእናት ሀገሬ እሞታለሁ እኔ የምኖረው እሷ ስትኖር ነው ።ጥርኝ አፈሯን ልሼ እንዳደኩ ሁሉ የላስኩባትን ጥርኝ አፈር ወርቅ አድርጌ እመልስላታለሁ እያለ ኖሮ እድል ሲቀናው ይኸው ትቷት ሔደ።ምን አደረገላት?ምንም።ጭንቅላት ያላቸው ሰዎች በእስኮላር መልኩ ይወሰዳሉ ።ተምረው መጥተው ለዚች ሀገር የፈየዱት ነገር አለ?የለም።የእግሯን እሾህ በመርፌ ለመንቀስ የሞከረ ምሁር እስከ አሁን አላየሁም አልሰማሁም ።በሔዱበት ሀገር እስረኛ ሆነው ይቀራሉ ።እስኪ እሩቅ ሳንሔድ ከዚው ከመንደራችን እንነሳ ።እንዳወቀ ካሴ ምሁር ይባላል ።ሳይንቲስት ይባላል ።ግን ሳይንቲስት ሆኖ ለዚች ሀገር ምን ጠቀማት?ይልቅ በችግር ማቃ የሞተችውን እናቱን ለመቅበር በእልፍ አእላፍ የፈረንጅ ወታደር ታጅቦ።መጣ።አስቀበረ።እንባው እንኳን ሳይደርቅ ነበር አንጠልጥለው የወሰዱት ።ይሔ ዘመናዊ ባርነት አይደለም ?አየህ የአገርህን ሰርዶ በአገርህ በሬ ድሮ ቀረ። የአገርህን ጥሪት የአገርህ ልጆች
አሳልፈው ሰጡ ለፈረንጆች ።ብሎ አገሬው መተረት ከጀመረ ቆይቷል ።ይቺን ሀገረ እግዚአብሔር ይቺን የተስፋ ምድር የቺን የቃል ኪዳን ሀገር ኢትዮጵያን ፤ቀቢፀ ተስፋ በልባችን ያደረብን ወጣቶቿ ከተስፋ መንገድ እየራቅን በትንሳኤዋ ፋንታ ተስፋዋን እያጨለምን እኛ ሌላ ሀገር እንሽታለን ።የእኛን ቤት እያፈረስን ለባዕድ አገር ምሰሶ እንተክላለን ።"ብላ በምሬት ስትናገር ቆይታ "የግል አሰተያየቴ ነው"አለችው።

ይቀጥላል

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

💞ክፍል 8

ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
"አንተ ዮርዲ ዮርዲ ተነሱ እንጂ ቁርስ ደርሷል እኮ"አለችና ቤዛ ብርድ ልብሱን ገፈፈቻቸው።
"ምን አለበት ትንሽ ብንተኛ"አለ ዮርዲ እያዛጋ ያለውን አፋን በመዳፉ እየሸፈነ ።
"ሁለት ሰዓት ሆኗል እማዬ ከጊዮርጊስ እስክትመለስ ተነስታችሁ ጠብቋት"አለች እና ትዕዛዝ ሰጥታ ተመለሰች ።
"አንተ ግን ደና ነህ ?"አለ ዮርዲ ደሳለኝን እንዴት ሲጠጣ እንዳመሸ እያስታወሰ።
"አንተ እራስህ ደህና ነህ?አንተ ስትጠጣ ያመሸኸው ፀበል መሆኑ ነው እንዴ እንዳልጠጣ ሰው ደና ነህ የምትለኝ "አለ ደሴ ቀና ብሎ ዮርዲን እያየው ።
"ማን ብዙ እንደጠጣ ቤዛ ትጠየቅ !አሁን ተነስ ሻወር እንውሰድ እና ቁርስ እንብላ" ብሎ ዮርዲ ከአልጋው ላይ ወረደ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዮርዲ እና ደሴ ማታ የጠጡት ቢራ ርሀብ ዘርቶባቸው ነበር ያደሩት ።ቁርስ አመጋገባቸውን እያዩ መላ ቤተሰቡ አስቂኝ ትዕሪት የሚያዩ በሚመስል መልኩ በአግራሞት ነበር የሚመለከቷቸው ።ቁርስ ከተበላ በኋላ እልፍነሽ የጠዋቱን ቡና ለማድረስ ጉድ ጉድ ማለቷን ተያያዘችው ።በዚህ መሀል አቶ አንድነት ጨዋታ ጀመረ ።
"እኔ እምልህ ደሴ እንዲያው ይሔ ልጅ ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲን ሲመርጥ ዝም አልክ?ወይ እዚሁ ደብረማርቆስ አለበለዚያ እዛው ወደ አንተ አታስሞላውም ነበር "አለ አቶ አንድነት
"ፋዘርየ እኔም እንደዛ አስቤ ነበር ነገር ግን አልሰማም አለ የነገስታት የፃድቃን የቅዱሳን መፍለቂያ ብዙ ተዐምር የሚፈፀምበት ብዙ ታሪካዊ ቦታዎች ባሉበት ሰሜን ሸዋ ሔጄ ነገስታቱ ካረፉበት ቅዱሳኑ ከተወለዱበት ቦታ ተቀምጬ ነው የጀመርኩትን መፅሐፍ ማጠናቀቅ የምፈለገው፣ለመፅሐፌ ቦታው ይጠቅመኛል አለ ደራሲው ወንድሜ።"አለና ዮርዲን ቸብ አደረገው ።
"እንግዲህ ካለ ምን ይደረጋል እሱ ከወሰነ ወሰነ ነው የማንንም ሀሳብ አይሻም"አለ አቶ አንድነት የቀረበለትን ቡና ፉት እያለ።
"በራስ መተማመኑን እወድለታለሁ ግን አንዳንዴ ሰው የሚነግረውንም መስማት አለበት ።"አለች ወይዘሮ አለም ስታዳምጥ ከቆየች በኋላ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዮርዲ ደሴን የሆነ ነገር በጆሮው ሹክ አለውና ተያይዘው ወደ ዮርዲ ክፍል ገቡ።ዮርዳኖስ ከመሳቢያው ሔዋን የሰጠችውን ፖስታ አወጣና ከፈተው ።ውስጡ ሀብል እና የታጠፈ ወረቀት አለ።ሀብሉን አወጣ እና እጁ ገር አሰረው ።
"እህ አንገትህ ላይ አድርገው እንጂ "አለ ደሴ በአግራሞት እየተመለከተው
"አይ ግዴለም ሳልሳዊት ታደርግልኛለች ።"አለና ወረቀቱን ፈታታው ።ማንበብ ጀመረ።
"የእኔ ወድ ከመወሰኔ በፊት ላማክርህ ይገባ ነበር።ነገር ግን አባየም የአንተ አባትም መናገሩ ችግር እንደሚፈጥር ነገሩኝ።እኔም የሰማሁት አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው።አዎ ለወንድሜ ለምናሴ በዚህ ሰዐት እንደማስፈልገው እና እንደምሔድ እንዲሁም ፕሮሰሱን አባዬ እንዳስጨረሰልኝ ሰማሁ።ታውቀለህ ሀገር ጥሎ መሔድ አማራጭ እንደሆነ ባላምንም ግን የእኔ መሔድ ወንድሜን የሚጠቅመው ከሆነ ምንም አማራጭ የለኝም ።የጀመርከውን መፅሐፍ እንደምትጨርሰው ቃል ግባልኝ።በቅርብ ጊዜ እንገናኛለን እንደምትጠብቀኝ አውቃለሁ።ግን ጠብቀኝ አፈቅርሀለሁ።
የአንተው ሔዋን"
አንብቦ እንደጨረሰ ሰማይ እና ምድሩ ተደበላለቀበት።መሬቱ ዞረበት የመሬት መሽከርከርን ዛሬ ሳያምን አልቀረም።በቁሙ አልጋው ላይ ዘፍ ብሎ ተቀመጠ።ደሴ ደነገጠና ወረቀቱን አነበበው ።ቅስሙ እንክት አለ።ምንም ለማለት አልደፈረም ምንም ሊል የሚችለው ነገር የለምና ከጎኑ ቁጭ አለ።ዮርዲ ከተቀመጠበት ተነሳና በፍጥነት እርመድ እርመድ እያለ ግቢውን ለቆ ወጣ ደሴ ተከተለው ።ትንሽ እንደተራመዱ ከእነ ሔዋን ደጅ ላንድ ክሩዘር መኪና ሲሔድ ተመለከተ።ባለበት ቁጭ አለ።ደሴ ዮርዲን ከአንገቱ ቀና አድርጎ ተመለከተው እንባወ እንደ ጅረት ሲወርድ አየ።ደሴ የዮርዳኖስን እንባ ሲመለከት ውስጡ ታወከ ባር ባር አለው።ዮርዳኖስን ሲያለቅስ አይቶት የማያውቀው ደሴ ዛሬ እንባውን ሲመለከት ውስጡ አለቀሰ።እንባው ገንፍሎ ፊቱን ሸፈነው።ከተቀመጠበት አነሳ እና እንደ ታመመ ሰው ድግፍ አድርጎ ወሰደው።ማንም ሳያያቸው በጓሮ በር ይዞት ገባ እና አስቀመጠው ።
"ዮርዲ አንተ የእኔ ወንድም ነህ ይሔንንም ታልፈዋልህ "አለ ደሴ ።
"ደሴ እንዴት ብዬ ሔዋን ትቼ እንዴት ወደፊት ልራመድ"አለ እንባው እየተናነቀው ።
"ሳይለፉ የሚበሉት እንደማይጣፍጥ ሁሉ ሳይፈተኑ የሚኖሩት ኑሮ ትርጉም አልባ ነው።ደግሞ ሔዋን ትመልሳለች ሀገሯን፣ቤተሰቧን፣ፍቅሯን በትና የምትኖር ልጅ አይደለችም።ስለዚህ አንተ በምን በማንም ሳትሰናከል ትልቅ ሰው ሆነህ።በመፅሐፍህ ዝነኛ ሆነህ ጠብቃት።አቅሙ አለህ ደግሞም ታደርገዋለህ አልጠራጠርም የእኔ ወንድም ነህ በእያንዳንዷ እርምጃህ ከፊትህ እግዚአብሔር ፣ድንግል ማርያም ፣ከጐንህ መላዕክት ፣ፃድቃን፣ሰማዕታት ፣ቅዱሳን በዙሪያህ ደግም የምትወዳቸው የሚወዱህ ሰዎች እንዳሉ እና እኔ ወንድምህ ደግሞ የጉዞህ አንድ አካል እንደሆንኩ አስብ"ብሎ አቀፈው ።
ዮርዲ ቀና ብሎ ግድግዳው ላይ ከተንጠለጠለ ጥቀስ ላይ አይኑን ተከለ።
"በፈተና የሚፀና የተባረከ ሰው ነው ።"
ያዕ 1፥12 ይላል ።
ደጋግሞ ሲመለከተው ከቆየ በኅላ "ትወደኝ የለ አበርታኝ እንደፈቃድህ ይሁንልኝ ።"አለ ዮርዲ ።
"ጎሽ እተማመንብሀለሁ አሳፍረኸኝም አታውቅም "አለ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ደሳለኝ ቤት የምሰራው ስራ አለኝ ከሰዓት በኋላ እንወጣለን ብሎ ወደ ቤቱ ሔደ።እሱም ሳሎን ገብቶ በዝምታ ተቀመጠ።ዝምታ የማያውቀው ዮርዲ ጭምት ሆነ።ነሁልሏል ።በራሱ አለም ውስጥ ገብቶ ሌላ አዲስ ሰው ሆኗል።
"ልጁ ምን ሆኗል ዛሬ?አንተ ዮርዲ ምን ሆነህ ነው እንዴ ቤቱን እኮ ጭር አደረግከው።"አለች ወይዘሮ አለም።እውነት ነው ዮርዲ ከሌለ ቤቱ ህይወት የለውም ማለት ይቻላል።ዮርዲ ዝም አለ ማለት ቤቱ ዝም አለ ማለት ነው።
ዮርዲ ቀና ብሎ እናቱን ተመለከተና ዝም አለ።
"አንተ መልስላት እንጂ እየጠየቀችህ አይደል?"አለ አቶ ተሾመ።
አባቱ ሲናገር የበለጠ ተናደደ ሊቋቋመው አልቻለም ስሜቱ ገንፍሎ ሲወጣ ታወቀው "አባዬ ዝም በል ምንም የምትልበት አፍ የለህም ምንም አትበለኝ"ብሎ ዮርዲ ደነፋ ።ሁሉም በድንጋጤ አፋቸውን ከፍተው ቀሩ።ዮርዲ እንኳን እንደዚህ አባቱን ሊናገር ይቅርና ከእድሜ እኩዮቹ ጋር እንኳ እዚህ ግባ የሚባል እሰጣ ገባ ውስጥ ገብቶ አያውቅም ።
ወይዘሮ አለም ተነስታ ዮርዳኖስን በአይበሉብሽ ጥፊ ፊቱን ከመታችው በኋላ "አንተ ከመቼ ያመጣኸው ባህሪ ነው?ጭራሽ አባትህን እንደዚህ ትናገራለህ"አለች
"ምክንያታችሁን ንገሩኝ ቀለበት አስራችሁ ከፍቅሬ የለያያችሁበትንን አሜሪካ የላከችሁበትን።"
አቶ ተሾመ ዮርዳኖስ የተናደደበት ስለገባው።ተረጋግቶ መናገር ጀመረ።"ልጄ ምናሴ ችግር ላይ እንደሆነ እና ሔዋን እንደምታስፈልገው ብቻ ነው አቶ አንድነት የነገረኝ።ሌላ ማብራሪያ ሊነግረኝ አልፈለገም ግን ከአንድ አመት በኋላ እንደምትመጣ በእርግጠኝነት ነግሮኛል።እኔ ትሒድ ብዬ ተስማምቼ አልላኳትም ልትሔድ እንደሆነ ነው የነገረኝ።ላስቀራት አልችልም እኔ በአንተ እንጂ በእሷ የመወሰን መብት የለኝም።ስለዚህ እኔን እንደጥፋተኛ አትመልከተኝ ።እንዲያውም ለአንተ የሚበጀውን የቃል ኪዳን ቀለበት አቶ አንድነትን ጨቅጭቄ እንድታደርጉ አደረኩ ።"አለ አቶ ተሾመ
በዚህ ጊዜ ዮርዳኖስ ተፀፅቶ እናቱንም አባቱንም ተንበርክኮ ይቅርታ ጠየቀ።

ይቀጥላል

@Ethio_leboled #share
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

💞ክፍል 9

ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
ከእነ ሔዋን ደጅ የተነሳው ላንድ ክሩዘር መኪና 15 ደቂቃ ያህል ከተጓዘ በኋላ ሴራሚክስ አምራቹ ሰፊ ግቢ በር ላይ ሲደርስ ቆመ።
"እንዴ አባዬ እዚህ ምን እሰራለሁ?እዚህ ድንጋይ ተሸካሚ ልታደርገኝ ነው እንዴ"አለች ሔዋን
አቶ አንድነት በሔዋን አነጋገር ፈገግ ብሎ "አይደለም ልጄ ከመሔድሽ በፊት እዚህ የሚጨርስ ጉዳይ አለ"አለ
ሔዋን የወንድሟ ጉዳይ ስለሆነ ምንም ማለት አልፈለገችም።ሲኦል እንኳን ቢሆን እሔዳለሁ በሚል አቋም ፀንታለች።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አቶ አንድነት ሔዋንን ተሰናብቶ አስተዋይ እንድትሆን አስጠንቅቋት።በመጡበት መኪና ተመልሶ ሔደ።አብሯት የቆመው ወጣት የግቢውን መጥሪያ ደወል እየተጫነ።"ኢያሱ እባላለሁ"ብሎ እጁን ለሰላምታ ዘረጋላት።
"ሔዋን"ብላ አፀፋውን መለሰችለት
"ስላገኘሁሽ ደስ ብሎኛል"አለ
"አመሰግናለሁ እኔም ስለተዋወኩህ ደስ ብሎኛል"አለች
ከደቂቃዎች በኋላ በሩ ተከፈተና ተፈትሸው ገቡ።ድንጋይ ወፍጮው ምንም አይነት ሰው አይታይበትም።ከፊት ለፊቱ በተጣለው ድንኳን ውስጥ ግን ሴራሚክስ አምራቾች ቡድን ወደ ሀያ የሚደርሱ ወጣቶች እየተሯሯጡ ነው።
ኢያሱ ጋር ለመተዋወቅ ያህል እያወሩ፤ ቡድኑ አጠገብ ሲደርሱ "በስራ የተጠመዱት ወጣቶች "እህታችን እንኳን ደህና መጣሽ"ብለው እያንዳንዳቸው ተዋውቀዋት ወደስራቸው ተመለሱ ።ኢያሱ እና ሔዋን በኢያሱ መሪነት ወደ ሰፊው አዳራሽ አመሩ።ብዙ ክፍሎች አቋርጠው ከሔዱ በኋላ አንድ ክፍል ላይ ሲደርሱ ቆሙ።በሩን አንኳኳ እና ከፈተው።ሲገቡ ኮምፒውተር ላይ ያፈጠጠ ወጣት ተቀምጧል።እጁን ለሔዋን ዘረጋላት እና "ሔኖክ እባላለሁ"አላት ወጣቱ
"ሔዋን"አለች የዘረጋላት መዳፉን እየጨበጠች
"በቃ ተዋወቁ እኔ ወደስራ ልመለስ"ብሎ ኢያሱ ሔደ።
ሔኖክ የቢሮ ስልኩን ነካካ እና "ሔሎ አባ መጥታለች"ብሎ መልስ ሳይጠብቅ ስልኩን ዘጋው ።
"እሺ ሔዋን አሜሪካ ለመሔድ መቼም ጓጉተሻል አይደል ?" ሔኖክ ፈገግ ብሎ ጨዋታ ለመጀመር ያህል ጠየቃት
"አረ በፍፁም የማያውቁት ሀገር እኮ አይናፍቅም"አለች ኮስተር ብላ
"እሱስ ልክ ነሽ። ግን እኛ ሰዎች ስንባል አዲስ ነገር ፈላጊዎች ነን"አለ ሔኖክ
"አዎ አዲስ ነገር ፈላጊዎች ነን ነገር ግን አዲስ ነገር፣ለውጥ ስንሻ ጥቅሙን እና ጉዳቱን ማመዛዘን አለብን።ለውጥ እንፈልጋለን እና ከመሬት ተነስተን ለውጥን መናፈቅ የለብንም።እናታችን ሔዋን በገነት በአማረ ቦታ ላይ እየኖረች ነገር ግን የጠላት ምክር ተቀብላ የማታውቀውን ናፈቀች ያላየችው መንግሰት አማራት ስታ አዳምን አሳታቸው።ከምድረ እርስት ተባረሩ ።አየህ በግብዝነት ለውጥን አዲስ ነገርን መናፈቅ የለብንም ።ምክንያታዊ የሆነ አዲስ ነገር ነው መሻት ያለብን።ይቅርታ ብዙ አወራሁ መሰለኝ"አለች ሔዋን ።
"አረ ልክ እኮ ነሽ እኔም የአንቺን ሀሳብ እጋራለሁ"አለ ሔኖክ
"ግን እዚህ ለምን እንደመጣሁ አልገባኝም " ተናግራ ሳትጨርስ ግርማ ሞገሳቸው የሚያስፈራ አባት በሩን ከፍተው ገቡ።ሔዋን ደነገጠች።ታውቃቸዋለች አባ ቶማስ ናቸው ።የጥንታዊ ቅዱስ ቂርቆስ ደብር ጠባቂ እና አስተዳዳሪ ናቸው።ለሔዋን ቤተሰቦች ደግሞ የንስሐ አባት ናቸው።ሔዋን ከተቀመጠችበት ተነስታ ጉልበታቸውን ስማ በመስቀል ተባርካ።ተቀመጠች ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሔዋን በአባ ቶማስ መሪነት ረጅም ኮሪደር አቋርጠው ከሔዱ በኋላ አንድ ክፍል አባ ቶማስ ከፈቱ እና ሻንጣዋን እንድታስቀምጥ ነገሯት ።ወደ ውስጥ ስትገባ ክፍሉ መሬት ላይ በስርዓት የተነጠፈ ፍራሽ አንድ ጠረጴዛ እና ወንበር አለው።ቁልፍ ሰጧት እና
"ልጄ ካልደከመሽ ቆልፊው እና ተከተይኝ"ብለዋት መልሷን ሳይሹ ፊታቸውን አዙረው መንገዳቸውን ቀጠሉ።

"እንዴ ቃለአብ"አለ ዮርዲ ከፊታቸው ብስክሌት እያሽከረከረ የሚመጣውን ልጅ ለደሳለኝ እየጠቆመው
"ማነው ቃለአብ?"አለ ደሴ ግራ በመጋባት አይነት ስሜት ውስጥ ሆኖ ።
ዮርዲ ግን እያዳመጠው አልነበረም።ልቡም አይኑም ብስክሌቱን እያሽከረከረ ከሔደው ልጅ ጋር አብሮ ሔዷል።ከአይኑ እስኪሰወር ድረስ ተመለከተለው ።ደሳለኝ በአግራሞት ሲመለከተው ከቆዬ በኋላ "አንተን እኮ ነው ቃለአብ ማነው?"አለና ደግሞ ጠየቀው ።
"ባክህ ተወው"አለና በግርምት ጭንቅላቱን ወደግራ ወደቀኝ ናጠው።
"እህ ይሔ ልጅ ጋር በሔዋን ተገናኝታችኋል ማለት ነው"አለ ደሴ ለማወጣጣት በሚመስል መልኩ
"አንተ ተው ስሟን አታንሳ ልቧ ይሸበራል "አለ ወሬ ለመቀየር
የደሳለኝ ጭቅጭቅ አላስቀምጥ ሲለው ዮርዲ በተሸናፊነት ስሜት"የሚጠቅም ታሪክ የለውም ብዬ ነው"አለ
"እሺ ልስማው ደግሞ ከመቼ ጀምሮ ነው እኔ ያልሰማሁት ታሪክ የተደበቀኝ"አለ ደሴ ።
"ምን መሰለህ"አለ እና ጉሮሮውን ጠራረገ።"ምን መሰለህ ይመስለኛል የዛሬ ስድስት ወር አካባቢ ነው።የሚገርም ህልም አየሁ።ቤዛ ነች እኔ ክፍል ድረስ የሆነ ልጅ ይዛ መጥታ "ዮርዲዬ ቃለአብ ይባላል መንታ ወንድምህ ነው"አለችኝ።ምን ያህል ደስ እንዳለኝ አትጠይቀኝ።ቃለአብ ብዬ አቀፍኩት አሱም ወንድሜ ብሎ እቀፈኝ ።የሚገርምህ እሱ ሲያቅፈኝ የተሰማኝን ስሜት ሔዋን እንደምታፈቅረኝ ነግራኝ ያቀፈችኝ ቀን እንኳ አልተሰማኝም ።"አለና በረጅሙ ተነፈሰ።
"የሚገርም ነው ግን እንዴት እስከዛሬ አልነገርከኝም?"አለ ደሴ
"እኔ ለራሱ እረስቼው ነበር።አሁን ብስክሌት እያሽከረከረ ያለፈው ልጅ ይሔን ነው መንታ ወንድምህ ብላ ያስተዋወቀችኝ።"አለ ዮርዲ
"እስኪመለስ ጠብቀን ለምን አንተዋወቀውም" አለ ደሴ ።
"ግን ሌላ ነገር እንዳትዘባርቅ ተዋውቀነው እንለያያለን "አለ ዮርዲ
"ችግር የለውም"አለና ደሴ የጊዮርጊስ መግቢያ በር ጥግ ይዘው ቆሙ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከ አምስት ደቂቃ ጥበቃ በኋላ ልጁ ከሔደበት እየተመለሰ በ200 ሜትር እርቀት ላይ ተመለከቱት።እየጠበቁት እንደሆነ እንዳይባንንባቸው እየተንቀሳቀሱ ጠበቁት።በአጠገባቸው እልፍ ሲል "ወንድሜ ወንድሜ"ብሎ ደሴ ተጣራ
ባለ ብስክሌቱ ዞሮ ተመለከተና እሱን እንደጠሩት ሲያረጋግጥ ብስክሌቱን አዙሮ መጣ።
"ሰላም እንዴት ነህ "አለና ደሴ እጁን ለሰላምታ ዘረጋ ዮርዲም ተከተለ።
ልጁ አፀፋውን መለሰ እና "ምን ልርዳችሁ?"አለ ፍፁም ትህትና በተሞላበት አነጋገር
"ወንድም በፍጥነት ማድረስ የነበረብኝ መልዕክት ነበር ካላስቸገርኩህ ብስክሌቱን ለአስር ደቂቃ አከራየኝ"አለ ደሴ
"አረ የምን ኪራይ ነው የምትለው!ሒድ መልዕክትህን አድርስ" አለና ከብስክሌቱ ላይ ወርዶ ብስክሌቱን ለደሴ ሰጠው ።
ደሴ በፍጥነት ብስክሌቱን እያሽከረከረ ከአይናቸው ተሰወረባቸው ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
"i think ዮርዳኖስ?አለ ልጁ ዮርዳኖስን ሲመለከት ከቆየ በኋላ ።
ዮርዲ ደንገጥ ብሎ "አዎ ነኝ ግን እንዴት ልታውቀኝ ቻልክ?"አለ
"ከሁለት ሳምንት በፊት የተዘጋጀው የግጥም ምሽት ላይ ግጥምህ አንደኛ ነበር የወጣው ።ስታቀርብ ተመልክቼሀለሁ።ጥሩ ገጣሚ ነህ ስላገኘውህ ደስ ብሎኛል ቃለአብ እባላለሁ"ብሎ በድጋሜ እጁን ዘረጋላት ።
"ምን አይነት ግጥምጥሞሽ ነው በህልሜ ቤዛ ስታስተዋውቀኝም ቃለአብ ብላ ነበር ።የሆነ ነገርማ አለ"አለ በልቡ ዮርዲ የዘረጋለትን እጁን እየጨበጠ ።
"እኔም ስላገኘሁህ ደስ ብሎኛል"አለ ዮርዲ
"ሰፈርህ እዚህ አካበቢ ነው?"አለ ቃለአብ
"አዎ ከዚህ ትንሽ ወረድ ብለህ ከምታገኘው ናዝሬት ከሚባለው ሰፈር ነኝ።አንተ ግን ከዚህ በፊት አላውቅህም እዚህ ሰፈር አይደለህም መሰ
ለኝ?"አለ ዮርዲ
"ልክ ነህ እዚህ ሰፈር አይደለሁም ገበያ ሰፈር ነኝ ለመተዋወቅ ያህል ሰዎች ለሰዎች ትምህርት ቤት የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ነኝ በአዲስ አመት አስረኛ ማለት ነው?"አለ ቃለአብ የአንተስ በሚል ጥያቄ አዘል አስተያየት እያየው ።
"እኔ ደግሞ 12 ተፈትኜ ውጤት እየጠበኩ ነው።"አለ ዮርዲ
"ዋው ደስ ይላል! ለአዲስ አመት ዋዜማ የግጥም ምሽት ላይ ትሳተፋለህ ብዬ አስባለሁ?" አለ ቃለአብ
"እያሰብኩ ነው ።ግን ለምን ጠየቅከኝ?"አለ ዮርዲ
"እኔም እሳተፋለሁ ብዬ እያሰብኩ ነበር መተዋወቃችን ጥሩ አጋጣሚ ነው ለምን በጥምረት አዲስ ስራ ሰርተን አናቀርብም?"አለ ቃለአብ
"ገጣሚ እንደሆንክ አላወቅኩም ነበር።ለማንኛውም አስቤበት እነግርሃለሁ ።"አለ ዮርዲ
"መልካም።እንግዲያስ ቁጥሬን ያዝ እና ደውልልኝ።አብረን ባንሰራ እንኳን እኔ ለምሰራው አስተያየትህን ትለግሰኛለህ"ብሎ ስልክ ቁጥር ተለዋወጡ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከደቂቃዎች በኋላ ደሳለኝ ብስክሌቱን እያበረረ መጣና አመስግኖ ለቃለአብ ሰጠው።ቃለአብ ብስክሌቱን እየገፋ "እንደዋወል እሺ ዮርዲ"ብሎ ሔደ።
"እንዴ እንዲህ በአንዴ"አለ ደሴ እየሳቀ።
ዮርዲም ያወሩትን ነገር በዝርዝር ለደሳለኝ ነገረው።
"ስማ ግን ምን አይነት መገጣጠም ነው የሆነ ነገራችሁ ደግሞ ይመሳሰላል።"አለ ደሴ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ማታ ዮርዲ አልጋው ውስጥ ሆኖ ስለ ቃለአብ እያሰበ ነበር።የሆነ ደስ የሚል ስሜት እየተሰማው ነው።ስልኩን አነሳና ከቃለአብ የተቀበለውን ቁጥር ፌስቡክ ላይ ሰርች አደረገው።"ቃለአብ ተሾመ"የሚል ፕሮፋይል አወጣለት።ዮርዲ ብቻውን እስኪያወራ ድረስ ተገረመ።"ጭራሽም የአባታችን ስም ተገጣጥሟል"አለና ቪው ፕሮፋይል ብሎ ሲመለከት የተወለደበት ቀን ከራሱ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ አገኘው።መስከረም አምስት አስራ ዘጠኝ ዘጠና ሁለት።"የሆነ ነገርማ አለ።"ብሎ ዮርዲ ደመደመ።

ይቀጥላል

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

🔥ክፍል አስር 10

ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
ሔዋን ከኮረብታው አፋፍ ላይ ቆማ ዙሪያ ገባውን ተመለከተች።ከኮረብታው ምስራቃዊ አቅጣጫ የዚባ ወንዝ ከአፍ እሰከ አፉ ጢም ብሎ ሞልቶ ይጥለመለማል።ክረምት መሆኑን ተከተሎ ዙሪያ ገባው ጋራው ሸንተረሩ በአዝርእትና አረንጓዴ በሆኑ እፀዋቶች ተሸፍኗል።የሚነፍሰው ነፋስ ለአዕምሮ እርካታን ይሰጣል።ከተማ ለምኔ እንዲሉ ያደርጋል ።
"እዚህ ቦታ ከዮርዲ ጋር ትዝታ መቅረፅ ነበረብን"ብላ ተፀፀተች።
"ነይ ልጄ ተከተይኝ"አሉ አባ ቶማስ ኮረብታውን ቁልቁል እየወረዱ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ቁልቁለቱን ወርደው እንደጨረሱ የዘንዶው ዋሻ በር ላይ ሲደርሱ ቆሙ።"ልጄ ከዚህ በፊት መጥተሽ አይተሽው ካልሆነ በአፈታሪክ የምትሰሚው የዘንዶው ዋሻ በር ማለት ይሔ ነው "አሉ አባ ቶማስ
"መጥቼ እንኳን አላውቅም ቦታው ደስ ይላል"አለች ሔዋን ።
"በጣም"አሉ አባ ወደ ውስጥ ለመግባት ጎንበስ ብለው።
"አባ ምን እያደረጉ ነው ውስጥ እኮ ዘንዶ አለ እየተባለ ነው የሚወራው ።?እንዴት አልሰሙም "አለች ፍርሀት እየተናነቃት
"ልጄ አትከተይኝም"ማለት ነው አሉ አባ ከአንገታቸው ሰበር ብለው እየተመለከቷት።
"አረ እከተለወታለሁ"አለች በድንጋጤ ውስጥ ሆና ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አስራ አምስት ሜትር ገደማ በሆዳቸው እየተሳቡ ከተጓዙ በኋላ ዋሻው መስፋት ጀመረ።የእጅ ባትሪያቸውን ከኪሳቸው አወጡ እና አበሩት።"ተነሺ ልጄ ከዚህ በኋላ ቆመን ነው የምንራመደው።"አሉ ወደፊት ባትሪያቸውን በጨለማው ዋሻ እያበሩ።ዋሻው ተጠርቦ እንደተሰራ ባትሪው ከዋሻው ግድግዳ ላይ ብርሀኑ ሲያርፍ የሚታየው የመጥረቢያ ቅርፅ ያሳብቃል።ውስጥ ለውስጥ ብዙ ከተጓዙ በኋላ አንድ ቦታ ሲደርሱ ቆሙ።ባትሪያቸውን ፊት ለፊት ሲያበሩት አንድ አነስተኛ ከእንጨት የተሰራች በር ላይ የባትሪው ብርሀን አረፈ።
አባ ቶማስ በሩን ለመክፈት ሔዱ።ሔዋን ግን በፍርሀት ሁለመናዋን
እያላባት ነበር። ያየቻቸው ፊልሞች ላይ በዘንዶ ሲዋጡ በህሊናዋ እየመጣ፤ከአሁን አሁን ዘንዶ መጣብኝ እያለች በፍርሀት ተኮማተረች።
"ልጄ ወዲህ ነይ አሉ" አባ
ሔዋን በፍርሀት ሽምቅቅ እንዳለች ወደ አባ ቶማስ ተጠጋች ።ወደ ተከፍተው በር እንድትገባ ጋበዟት።
፨፨፨፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨፨፨፨፨
ሔዋን ወደ ውስጥ እንደገባች፤አባ ቶማስ ከዋሻው ግድግዳ ላይ ማብሪያ ማጥፊያ ተጭነው መብራት አበሩ።ሔዋን ህልም አለም ውስጥ ያለች እያቀዠች መሰላት።ክፍሉ ከሸክላ በተሰሩ ጋኖች ተሞልቷል።ከዚህም በላይ ያስገረማት ግን እዚህ ዋሻ ውስጥ እንዴት መብራት ሊኖር ቻለ።ለዛውም ደግሞ እዚህ ክፍል ብቻ ነው።
"ልጄ ነይ ከዚህ ተቀመጪ" ብለው ዋሻው ሲፈለፈል አብሮ ከተሰራ መደብ ቢጤ ነገር ላይ አስቀመጧት እና ከፊት ለፊቷ ተቀመጡ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
"ልጄ አባቶቻችን ጠንካሮች ነበሩ።አባት አርበኞች ጠላትን ፊት ለፊት ሲዋጉ ሴቶች እና በአቅማቸው የደከሙት ደግሞ እንደዚህ አይነት ተዓምራዊ ዋሻ እየፈለፈሉ ንብረቶቻቸውን ይሰውሩ ነበር።ጣልያን ኢትዮጵያን ሲወሩ አባቶች ይሔንን ዋሻ ፈልፍለው ንብረቶቻቸውን ደበቁ።ነገር ግን ለአቅም አስቸግራ ውስጥ ውስጡን ስራዋን መስራት ስትጀምር እና ንጉሰ ነገስት ከአገር ወጥተው ሲሔዱ።ጠላት በማን አለብኝነት ጥንታዊ ቅርሶችን ከእየቦታው እየቃረሙ እየዘረፉ ከዚህ ጥንታዊ ቂርቆስ ደረሱ።እነዚህ ሰላቢዎች ከይሲዎች እንዴት እንደሆነ በማይታወቅ መልኩ ይሔን ዋሻ ደረሱበት ።እሰየው የዘረፍነውን የምናከማችበት አገኘን ብለው።ከእየ አካባቢው የቃረሙትን ሀብት እያመጡ እዚህ ማከማቸት ጀመሩ ።ለታሪክ እንዳይበጅ አድርገው ወደ ዋሻው የሚገቡ አባቶችን በግፍ ገደሏቸው።የዋሻውን ምስጢር የሚያውቅ በሙሉ አለቀ። ዘንዶ ውስጥ እንዳለ እና ውስጥ የሚገቡትን እየሰለቀጠ እንደሆነ የተዛባ ታሪክ ተወራ።የነገሩትን የሚያምን ይሔ ምስኪን ህዝብ የውሀ ሽታ ሆነው የቀሩትን አባቶች ዘንዶ ዋጣቸው ብሎ መሪር ልቅሶን አለቀሰ።የደም እንባ አነባ።ቦታውም የዘንዶ ዋሻ ተብሎ ተሰየመ።ከዛ በኋላ ይሔ ቦታ ተፈርቶ እየኖረ ነው"ብለው እያዳመጠቻቸው እንደሆነ ተመለከቱ እና ቀጠሉ ።
"ከዚያ በኋላ የድንጋይ ወፍጮ እና ሴራሚክስ ማምረቻውን አዳራሽ ጣሊያን አነፁ።ግን አላማቸው ድንጋይ መፍጨት አልነበረም።"ብለው ቀና አሉና ተመለከቷት።

"ታዲያ ድንጋይ ወፍጮ ድንጋይ ከመፍጨት ውጭ ሌላ ምን አለማ አለው?"አለች ሔዋን በፅሞና ስታዳምጥ ከቆየች በኋላ ።
በጥልቅ አስተያየት አይኗን ሲመረምሯት ከቆዩ በኋላ "አየሽ ልጄ የአነፁት አዳራሽ የጀርባ ግድግዳው ከዋሻው ምዕራባዊ በር ጋር የተያያዘ ነው።የአዳራሹ የጀርባ ግድግዳ ላይ በር አለ።በሩ የትም ሳይሆን የሚወስደው ወደ ዋሻው ነው።ምክንያቱም ግድግዳው ከተራራው ጋር ተጣብቆ የተገነባ ነው።ይሔ ክፍል ተለይቶ መብራት የተገጠመለት ለጥበቃ እንዲመቻቸው ነው።አየሻቸው እነዚህ ጋኖች ጣልያን የዘረፋት እና አባቶች ደብቀውት የነበረ ወርቅ ብር አልማዝ እንቁ የተሞላ ነው።ወፍጮው የተመሰረተበት አላማ እነዚህ የአካበቱአቸውን ቅርሶች ለመጠበቅ እና እንዲሁም የተፈጨ ድንጋይ አስመስለው ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ እንዲመቻቸው ነው።ነገር ግን የኢትዮጵያ አምላክ እግዚአብሔር ቸር ነው።ኢትዮጵያን ሊጨክንባት አልወደደም እና ለአርበኞች ፅናትን ሰጥቷቸው አገራችሁ አገራችን ብለው የተቀመጡትን ጣሊያኖችን አባረሩ።ከእየቦታው ቃርመው ያስቀመጡትን ሳያሸሹ ወደ አገራቸው ተመለሱ።የድንጋይ ወፍጮው እስከ 1998ዓ.ም ተዘግቶ ነበር። ነገር ግን 1999 ዓ.ም አቶ ኢሳያስ ተ/አረጋይ ገዝቶ እንደ አዲስ ስራ ጀመረ።አሁንም አላማው ድንጋይ መፍጨት አይደለም።"አሉ እና ከሚያስገመግመው ድምፃቸው አረፉ።
ሔዋን በታሪኩ ብትመሰጥም ለእሷ ለምን እንደሚነግሯት አልገባትም ።ይሔ ታሪክ እና የእሷ አሜሪካ መሔድ ምንም የማይገናኝ ነገር ሆኖ ታያት።
"እሺ አላማው ምንድን ነው"አለች ሔዋን።
"እሱን ወንድምሽ ይነግርሻል?"አሉና ለመሔድ ተነሱ
"ይሔን ታሪክ እንዴት ሊያውቁ ቻሉ?አለች
"አሱን አሁን የምነግርበት ጊዜ አይደለም"አሉ አባ
"እሺ መቼ ነው የምበረው?"አለች
"ነገ ከኢያሱ ጋር አዲስአበባ ከነገ በስቲያ ደግሞ ወደ አሜሪካ ትበሪያለሽ ትኬትሽ ተቆርጧል"አሉ መብራቱን እያጠፉ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ትንሿን ክፍል ለቀው ሀያ አምስት ሜትር ገደማ ከተጓዙ በኋላ ከብረት የተሰራ በር አገኙ።ባትሪውን ሔዋን እንድታበራላቸው ሰጧት እና ከቀሚሳቸው ኪስ ብዙ ቁልፎችን የያዘ ማሰሮ አውጥተው ሰረገላ ቁልፋን አሽከርክረው ከፈቱት።ሔዋን የነገሯት እውነት መሆኑን አረጋገጠች።በሩ ሲከፈት ቀጥታ የአዳራሹ ኮሪደር ላይ ነበር የገቡት።ከጨለማው ወጥታ ብርሀን ስታገኝ ሰላም ተሰማት።ነገር ግን አባ ጀምረው ያልቋጩት ታሪክ እየከነከናት ነው።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሔዋን ከተሰጣት ክፍል ውስጥ ጋደም ብላ በአየችው ነገር ብቻዋን አየተገረመች ድንገት አንድ ሀሳብ መጣላት እና ቦርሳውን መጎርጎር ጀመረች ።ከትንሽ ፍለጋ በኋላ ከዮርዲ የተቀበለችወን የግጥም ደብተር አወጣችውና መመርመር ጀመረች ።አንድ ርዕሰ ላይ አፈጠጠች።"ፈራሁ"ይላል ገፅ አገላበጠች እና ግጥሙን አወጣችው
ፈራሁ ውስጤ ቃተተ
ስጋት ልቤ ሸመተ
ፈራሁት ፍርሀቴን
እንዳላጣት ሔዋንን
የሚል አጭር ግጥም ነው "የእኔ ጌታ አታጣኝም።ይልቁንስ አንተን እንዳላጣህ እኔ እፈራለሁ"አለች እና ቀለበቷን ተመለከተች ።በቀለበቱ ውስጥ ምስሉን ሳለች እና ፈገግ አለች።ለመጀመሪያ ጊዜ የላከላትን ደብዳቤ አስታወሰች።
".............ሔዋን እንዴት እና መቼ እንደሆነ ባላውቅም አሁን እየተሰማኝ ያለው ስሜት ያ ነው።አዎ አፍቅሬሻለሁ።" የደብዳቤው የመጨረሻ መስመር ነበር።አንብባ እንደጨረሰች ቢንጎ ፣የስ ፣ፈጣሪ ሆይ ተመስገን እያለች አልጋዋ ላይ ጨፈረች።እንዴት አድርጌ ልንገረው እያለች ይሉኝታ አንቋት ሴት ወንድን መጠየቅ ለህብረተሰቡ ሀፍረት መስሎ በሚቆጠርበት መንደር።ፍቅሯ ቤቷ ድረስ አንኳኩቶ ሲመጣ ነፍሷ ሀሴት አደረገች።ታዲያ የሴት ልጅ ወጉ ነውና እሷም "አልፈልግህም እኔ አንተን አልወድህም አቻህን ፈልግ"ምናምን ብላ ፅፋ ላከችለት።
በነጋታው ከቤቷ አስጠርቶ ነበር በነገር የጠመዳት ዮርዳኖስ።መቼም ከዚህ በኋላ አንዴ ፈንድቷል ወደፊት እንጂ ወደኋላ መርገጥ እንደሌለ ልቡን አደንድኖ ነበር የሔደው።
"ቆይ ማነኝ ብለሽ ነው የምታስቢው?"አለ ዮርዲ
"ይቅርታ ወንድሜ እኔ ራሴን እንደ ማንም ማሰብ አልፈልግም እኔ ሔዋን ነኝ"አለች ኮራ ቀብር ብላ።
"አልሽ እንጂ ከዚህ በላይ?እኔን አቻህን ፈልግ ትይኛለሽ?"አለ ንዴቱ አናቱ ላይ ወጥቶ ያልበው ጀምሯል ።
"ዮርዳኖስ ልትጨቃጨቀኝ ከሆነ የመጣህ ባክህ ተወኝ እኔ የአንተን ጭቅጭቅ የምሰማበት ጊዜ የለኝም"አለች
ዮርዲ ገና አሁን ደሙ ፈላ።ከዚህ በፊት ተገናኝተው መለያየት የሚከብዳት ልጅ ዛሬ ጊዜ የለኝም ስትለው ደሙ ሞቀ።
"እየውልሽ ሔዋን ቤዛ ትሙት ከዚህ በኋላ ተመልሼ መጥቼ አልጨቀጭቅሽም ግን አንድ ነገር ላስቸግርሽ አለ ዮርዲ ።"
ሔዋን ቤዛ ትሙት ካለ ከአቋሙ ውልፍት እንደማይል ስለምታውቅ ሆዷን ፍርሀት ፍርሀት እያላት
"ምን"አለችው
'አይኔን እያየሽ አልፈልግህም በይኝ"አለ ዮርዲ በቆራጥነት
ሔዋን ትንሽ ሳትግደረደር እንደዚህ ስለደረቀባት ተናደደች።ግን የማይሆን ነገር ተናግራ ነገሩን ማበላሸት ስላልፈለገች "ዮርዲ አፈቅርሀለሁ አንተን ችሎ ማን ይጠላል የልጅነት ህልሜም ፍቅሬም ነህ "ብላ አቀፈችው።
ከሀሳቧ ስትመለስ ፈገግ አለች እና ከደብተሩ መሀል ያስቀመጠችውን ፎቷቸውን አውጥታ ግንባሩ ላይ ሳም አደረገችው።

ይቀጥላል

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

💞ክፍል 11

ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
ቀኑ ጷጉሜ 5 ነው።የአዲስ አመት ዋዜማ።በጠዋት ፀሐይ እዩኝ እዩኝ ማለት ጀምራለች።ከአሁኑ መስከረም ወር መጣሁ እያለ በሚመስል መልኩ እለተ ዋዜማው እንቁጣጣሽን መስሏል።የዮርዳኖስ ቤተሰቦች አዲስ አመትን ለመቀበል ሽር ጉድ እያሉ ነው።ዮርዳኖስ ጥሩ ውጤት በማምጣት ቤተሰቡን አስደስቷል ።የዩኒቨርስቲ መግቢያ ነጥብ 491 ነው ያስመዘገበው።
ዮርዳኖስ ሔዋንን ከተሰናበተ በኋላ ጨዋታ እና ሳቅ ከእሱ ኮብልለው ሔደዋል።ጭምት ሆኗል።ዝምተኛ ሆኗል።ቤት ውስጥ ገፍተው ካላወሩት እሱ እንደበፊቱ ቤተሰቦቹን በወሬ መጥመዱን እርግፍ አድርጎ ከተወ ውሎ አደረ።ቤተሰቡም ምክንያቱን ስለሚያውቁ እሱን ለማስደሰት መከራቸውን ሲያዩ ነው የሚውሉት።
"ዮርዲ ስልክህ አየጠራ ነው"አለች ወይዘሮ አለም
ዮርዳኖስ ስልኩን ከቻርጀሩ ላይ ነቅሎ ሲመለከት ቃለአብ ነው የደወለው ። ዮርዳኖስ ስልኩን አነጋግሮ ከቃል ጋር ተቆጣጥረው ስልኩን ዘጋው።
ቃለአብ እና ዮርዳኖስ ከብስክሌቱ ቀን በኋላ በደንብ ተዋውቀዋል ።የሁለቱ የደሳለኝ እና የዮርዳኖስ ፍቅር ላይ ቃለአብ ተጨምሮበት ደምቀዋል።ነገር ግን ዮርዲ ውስጡን የሆነ የሚረብሸው ነገር አለ።ቃለአብን ሲያይ ልቡ ይሸበራል።ምክንያት አልባ ፍርሀት ያስጨንቀዋል።
ቃለአብ ዮርዳኖስን እና ደሳለኝን ለመተዋወቅ ቀናት አልፈጀበትም በአንዴ ነበር በሁለቱም ልብ ውስጥ መግባት የቻለው ።በአዲስ አመት ደሴ ወደ ዋቻሞ ዮርዲ ደግሞ ወደፊት ወደ ሚደርሰው ዮኒቨርስቲ ሲበታተኑ ቃለአብ ብቸኝነት እንደሚገድለው እያሰበ ነው።እዚህ ግቡ የማይባሉ ጓደኞች ያሉት ቃለአብ ጓደኝነትን ከዮርዲ እና ከደሴ በዚች አጭር ጊዜ ውስጥ ተምሯል።ፍቅርን በደንብ ከትበውታል።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ደሳለኝ ሲመጠ ቤት ቤት ውስጥ ወይዘሮ አለም እና ዮርዳኖስ ብቻ ናቸው ያሉት።ወይዘሮ አለም የዳቦ ቡኮ እያዘጋጀች ሲሆን ዮርዲ ደግሞ የአዲስ አመት ዋዜማን አስመልክቶ ለተዘጋጀው የግጥም ምሽት ግጥሙን እየተለማመደ ነው።አቶ ተሾመ በግ ለመግዛት ደብረ ማርቆስ ሔዷል።ቤዛ ደግሞ ሱቅ የአባቷን ቦታ ተክታ እየሰራች ነው።እልፍነሽም የሚገዛዛውን ለመግዛት ገበያ ወጥታለች።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
"እኔ እምልህ ግጥማችን የሚያሸንፍ ይመስልሀል?"አለ ዮርዲ ደሳለኝን በፍቅር እያየው ።
"እንዴታ ከዚህ በፊት ተሸንፈህ አታውቅም።አሁን ደግሞ ከቃለአብ ጋር ነው በጥምረት የሰራችሁት።ሁለቱን ትጉህ ወንድሞቼንማ ማንም አይበልጣቸውም "አለ ደሴ ኩራት እየተሰማው።
"እሺ አሁን ለቃል ደውልለት እና እንውጣ አብረን መለማመድ አለብን።ቅድም እኮ ደውሎ ደሴ ይምጣና እደውልልሀለሁ ብዬው ነበር።"አለ ዮርዲ
"እሺ እደውልለታለሁ።ግን አንተ ስላየኸው ህልም ለምን አትነግረውም መንታ ወንድሜ እንደሆንክ ነው የሚሰማኝ ብሎ ለመናገር እንደዚህ መፍራት ምንድን ነው?አለ ደሴ
"ባክህ ባልነግረውም እኮ አሁን የወንድማማች ያህል ነው የቀረበን"አለ ዮርዲ
"አየህ አንተ እሱን በአጋጣሚ ሳይሆን በምክንያት ነው ያገኘኸው።ደግሞ አልገባህ አለኝ እንጂ የሆነ ነገር እየሸተተኝ ነዉ" አለ ደሴ ።
"እስኪ ማታ ከፕሮግራሙ በኋላ እምናየው ይሆናል።"አለ ዮርዲ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ምሽቱ በግጥም ተወዳዳሪዎች ደምቋል።በእየ እረፍቱ የባህል ቡድኑ ሞቅ ያለ ውዝዋዜ እያቀረቡ ግዙፋን የትንሣኤ አዳራሽ በዓል በዓል አሽትተውታል ።ሶስተኛ እና ሁለተኛ የወጡት ልጆች ግጥማቸውን አቅርበው አሁን አንደኛ ማን እንደወጣ ሁሉም በጉጉት እየጠበቀ ነው።
"አንድ ሞቅ ያለ የባህል ሙዚቃ ጋብዘናችሁ ተመልሰን እንገናኛለን መልካም አዲስ አመት"ብሎ መድረክ መሪው ለተወዛዋዦች መድረኩን ለቀቀ።
ዮርዳኖስ ቃለአብ እና ደሳለኝ ሁሉም የበዓል ልብሳቸውን ለብሰው አሸብርቀው በረድፍ ተቀምጠዋል።ከአንድ ማህፀን የወጡ ወንድማማቾች ነው የሚመስሉት።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
"የዚህ የግጥም ምሽት አሸናፊ ከዚህ በፊት ከአንዴም ሁለት ሶስት ጊዜ በተደጋጋሚ የግጥም ምሽትን ሽልማት የወሰደው እንዲሁም የወረዳችን ታዳጊ ገጣሚ በሚል ከወረዳ ባህልና ቱሪዝም ሜዳሊያ የተበረከተለት ዮርዳኖስ ተሾመ እንዲሁም ለግጥም ምሽት እንግዳ የሆነው ቃለአብ ተሾመ በጥምረት "ትንሳኤሽ" በሚል ርዕስ አሸናፊ ሆነዋል።ወደ መድረክ" አለ መድረክ መሪው ።
ዮርዲ እና ቃል ወደ መድረክ ሲወጡ ወንድማማቾች ናቸው እንዴ የሚል ሹክሹክታ ጭብጨባውን አልፎ እየተሰማቸው ነበር።ደሳለኝ ዮርዲ እና ቃል መድረክ ላይ ወጥተው ማይክ እስኪቀበሉ ድረስ ቆሞ በፌሽታ ጮቤ እየረገጠ ነበር።

ግጥሙን አቀረቡ ።ታዳሚ በሙሉ ቆሞ አጨበጨበላቸው።የግጥም ምሽት ታዳሚ በሙሉ በፊት ዮርዲ አሸንፎ ካጨበጨበለት በላይ ዛሬ ከቃል ጋር ጥምረታቸውን አድንቆ ጥበብ ውለታችሁን ትክፈላችሁ ብሎ መረቃቸው።ዘለዓለም አንድ ላይ ተጣምረው መድረክ ላይ ደምቀው እንዲታዩ ደሳለኝ በልቡ ፀለየ።
ቃለአብ ደስታውን መቆጣጠር አቅቶት እዛው መድረክ ላይ"የአንተ ወጤት ነው"እያለ ዮርዲን ደጋግሞ ያቅፈዋል።ዮርዲ ቃለአብ ሲያቅፈው ልቡ ሰትንሸራት ይሰማዋል ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ፕሮግራሙ ከተጠናቀቀ በኋላ ሶስቱም የሻነው ባር ውሰጥ መጠጥ አዝዘው ደስታቸውን እያከበሩ ነው።
"ዮርዲዬ የሆነ ነገር ልነግርህ እያሰብኩ ነገር ግን እየፈራሁ እተወዋለሁ ።"አለ ቃል
ደሳለኝ ጣልቃ ገባና "ከዛ በፊት ዮርዲ የሚነግርህ ነገር አለ እሱን አድምጠው"አለ ዮርዳኖስን ተናገር በሚል አስተያየት እያየው
"እሺ ልስማህ ወንድሜ ቀጥል "አለ ቃል
ወንድሜ ብሎ ሲጠራው ዮርዲን የሆነ ነገር ነዘረው "ግዴለም አንተ ቀጥል እኔ ቀስ ብዬ እነግርሃለሁ "አለ ዮርዲ
ቃለአብ ከብርጭቆው ተጎነጨና"ዮርዲዬ እንደ እውነቱ ከሆነ አንተን ያወቅኩህ ያው እንደነገርኩህ የግጥም ምሸት ፕሮግራም ላይ ግጥም ስታቀርብ ነው።በፕሮግራሙ ላይ ለውድድር ስቀርብ የመጀመሪያ ቢሆንም ለመታደም ግን አልፎ አልፎ እመጣ ነበር ።የመጀመሪያ ቀን እንዳየውህ እንዴት እንደደነገጥኩ አትጠይቁኝ።"
"ለምን"አሉ ደሴ እና ዮርዲ በአንድ ድምፅ
ቃል ዮርዲን ትክ ብሎ ሲመለከት ከቆየ በኋላ ብርጭቆው ላይ የቀረውን መጠጥ በአንድ ትንፋሽ ጭልጥ አደረገና መናገር ጀመረ።
"ገና እንዳየውህ ልቤ በፍጥነት መምታት ጀመረች።ወንድሜ ወንድሜ መስለህ ታየኸኝ" አለና ቀና ብሎ ዮርዲን ሲመለከት ዮርዲ በጉንጮቹ እንባ ሞልቶ እየፈሰሰ ነበር።
"እኔም እኮ የመጀመሪያ ቀን ያገኘውህ በአጋጣሚ ሳይሆን በምክንያት ነው"አለ ዮርዲ
ደሳለኝ ድራፍቱን ፋት እያለ የሚፈጠረውን በጉጉት እየጠበቀ ነው ።
ቃለአብ ዮርዲ ለምን እንዳለቀሰ ባይገባውም ያገኘውህ በምክንያት ነው የሚለው የዮርዲ ንግግር ልቡ ላይ ቀርቷል ።
"በምን ምክንያት ነው ያገኘኸኝ"አለ ቃል
" ደሳለኝ የዚያን ቀን ብስክሌቱን የተበደረህ እውነት ፈልጎት ሳይሆን እኔ እና አንተ ተቀራርበን እንድናወራ ነበር ።አየህ ከወራት በፊት ህልም አየሁ..........ብሎ ያየውን ህልም ነገረው።"ዮርዲ ተናግሮ እንደጨረሰ ቃለአብ እያነባ ተነሳና ወንድሜ ብሎ አቀፈው።
፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
"ለእናቴ ብቸኛ ልጅ ነኝ አባቴን አላውቀውም እሱ ግን ያውቀኛል።በእየ ጊዜው ልብስ ይልክልኛል።እናቴን አባቴን አስተዋውቂኝ ስላት ትቆጣለች ትናደዳለች።ወንድም እህት የሚባል ነገር የለኝም።"አለ ቃል እንባ እየቀደመው ።
"ቃል እኔም እኮ ወንድም የለኝም ግን
አለኝ አየህ መወለድ ቋንቋ ነው ይባል አይደል?ደሴ ከእናቴ ማህፀን ባይወለድም ለእኔ ግን ወንድሜ ነው።ደግሞ ከዚህ በኋላ እንደዚህ ስትል እንዳልሰማ እኔም ደሴም ወንድሞችህ ነን"አለ ዮርዲ።
ቃል በደስታ ማበድ ነበር የቀረው ።ምንም ማለት አልቻለም ደሴን እና ዮርዲን እየተካካ ያቅፋቸዋል።
"እስከ አሁን ሳዳምጥ ነበር አሁን ደግሞ አድምጡኝ ልናገር"ብሎ ደሴ መናገር ጀመረ።"እውነት ሔዋን ከሔደች ጀምሮ ዮርዲ እንደዚህ ሲደሰት አይቼው አላውቅም።ቃለአብ አንተ ዮርዲን ህይወት ዘርተህበታል።ዮርዲ ፈገግ ሲል ወጥሮ ይዞኝ የነበረው ጭንቀት ለቀቀኝ።አንድ ነገር ግን አሁንም እየከነከነኝ ነው።በሁለታችሁ መካከል የሆነ ነገር እንዳለ እየተሰማኝ ነው።በጣም እኮ ነው የምትመሳሰሉት "አለ ደሴ
ቃል እና ዮርዲ በደሴ እየሳቁ ነበር እየቀለደ መስሏቸው ።ነገር ግን ደሴ እየቀለደ አልነበረም ።

ይቀጥላል

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

🔥ክፍል 12

ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
ሰከንዶች እየበረሩ ደቂቃን ደቂቃዎች ዞረው ሰዓትን ሰዐታት ተሽከርክረው ቀናትን ቀናት ተደምረው ሳምንታትን ሳምንታት ተጣምረው ወራትን እየፈጠሩ ይሔው በደብረብርሀን ዮኒቨርስቲ ዮርዳኖስ አንድ ሴሚስተር ሊያስቆጥር ጥቂት ሳምንታት ቀርተውታል ።የሔዋን ናፍቆት ቢያንገበግበውም ነገር ግን ደሴ እና ቃል በእየቀኑ እየደወሉ ብርታትን ሰጥተውታል ።ሔዋን ደውላ አታውቅም።ለምን ብሎ ቤተሰቧን ሲጠይቅ የሔደችበት ቦታ ይሔንን አይፈቅድም ብቻ ነው መልሳቸወ።እሱም ከትራሱ በላይ ፎቶዋን አንጠልጥሎ ጠዋትም ማታም እንደ ስዕል አድኖ ይሳለማታል ።ታዲያ ዘላለም የሚባል የዶርሙ ልጅ አንድ ቀን "እኔ እምልህ ዮርዲ ፥ማን እሚሏት ሰማዕት ነች ባክህ እንደዚህ ጠዋት ማታ እሚሰገድላት?ነገረኝ እና እኔም ለነፍሴ ይሆነኝ ዘንድ ልስገድላት"ብሎ ቀልዶበታል።ዮርዲ የተመደበበት ዶርም ሁሉም ሰው ይቀናባታል።ፍቅራቸው መተሳሰባቸው ከብዙ አመት ቅርርብ የመነጨ እንጂ የአንድ ሴሚስተር ብቻ አይመስልም ።የመጀመሪያ ቀን በዘላለም እና በዮናስ መካከል የተፈጠረው ሰጣገባ ሁሉንም የዶርም አባላት አስበርግጎ ነበር።
..............እንዲህ ሆነ....................
ዮርዳኖስ ከተመደበበት ብሎክ 23 ማስታወቂያ መለጠፊያው ላይ የተመደበበትን ዶርም እና የዶርም አባላት ተመለከተ።
ዶርም 106 ይልና
👉ዮናስ ግሩም
👉ዮናስ ካሳ
👉ዮናታን ስለሺ
👉ዮርዳኖስ ተሾመ
👉ዘላለም ደሴ
👉ዝናቡ አከለ
እነኚህ ጋር ነበር ዮርዲ የተመደበው ።ዮርዳኖስ ዶርም ሲገባ ሁሉም አልጋቸውን አነጥፈዋል እሱ ብቻ ነበር የቀረው ።ሰላምታ ስጥቷቸው አልጋውን አነጠፈና ለመመዝገብ ወደ ዲፓርትመንት ወረደ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ምሽት ላይ ሁሉም አልጋቸው ላይ አድፍጠዋል።ዘላለም እና ዮናታን ከአንድ አካባቢ ሳይሆን አይቀርም የመጡት ወሬያቸው ደርቷል ።
ታዲያ ዮናታን ጋር ዘላለም ሲያወራ ቆየና በድንገት ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተረተ
"የወሎ ልጅ ማር ነው አዘንብለሽ ጠጪው
ሌላው ቅራሪ ነው ምንግዜም አታጪው"አለ ዘላለም ድምፁን ከፍ አድርጎ ።
ከፊት ለፊት የተኛው ልጅ በደመ ነፍስ ተነሳና ዘላለም ላይ ተከመረበት አንገቱን አንቆ ይዞ "ማነው ቅራሪ አንተ ማንን ነው ቅራሪ የምትለው።"ብሎ ለመማታት እጁን ሲሰነዝር ሌሎች ልጆች ከአልጋው ላይ ወርድው አገላገሏቸው።የተናደደው ልጅ ንዴቱ ሲበርድለት ዘላለም ለስለስ ብሎ ለማግባባት ሞከረ።
"ምን መሰለህ ወንድሜ እንዲሁ ሳይህ ጎጃሜ መሰልከኝ እና ጎጃሜ ደግሞ ቅኔ በመዝረፍ አንደኛ ናቸው ሲባል ሰምቼ የመጣህበትን እንደኔ በቅኔ እንድትነግረኝ አስቤ እንጂ ሌላ ተንኮል አስቤ አይደለም።"አለ ዘላለም ይቅርታ እየጠየቀ።
"ወንድም ይቅርታ አድርግልኝ እኔ በአንድ ቀን ብሔር ተኮር ነገር ለመናገር አስበህ መስሎኝ እንጂ እኔም መጥፎ ሰው አይደለሁም።ለማንኛውም ዮናስ ካሳ ከጎጃም ሞጣ ነኝ።"ብሎ ሔዶ ጨበጠው።
"ዘላለም ደሴ ከውሎ የደሴ ልጅ"ብሎ አፀፋውን መለሰለት።
ሁሉም እራሳቸውን አስተዋወቁ
ዮርዳኖስ ተሾመ ከጎጃም ደብረማርቆስ አካባቢ
ዮናስ ግሩም ከአዲስአበባ
ዮናታን ስለሺ ከወሎ የዘላለም የሰፈር ልጅ ነኝ
ዝናቡ አከለ ከወሎ የራያ ልጅ ነኝ ከጥሙጋ
ተዋወቁ ሌሊቱን በሙሉ ሲያወሩ አደሩ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዮናታን ዮናስ ካሳ እና ዮናስ ግሩም ስማቸው ተመሳሳይ ሰለሆነ ለማቆላመጥ አስቸገረ።ዮኒ ብሎ ሰው ሲጣራ ሶስቱም አቤት እያሉ ተቸገሩ።ስለዚህ ለሁሉም ቅፅል ስም ተሰየመ
ዮናስ ካሳ👉ዮኒ ጎጃሜ (ጎጄ)
ዮናስ ግሩም 👉ዮኒ
ዮናታን ስለሺ 👉ናታን👉ናቲ
ዮርዳኖስ 👉ዮርዲ
ዘላለም 👉ዞላ
ዝናቡ 👉ዜኖ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👉ዞላ ማለት እየቀለደ ለመኖር የተፈጠረ በሚመስል መልኩ ሲቀልድ እንጂ ቁምነገር ሲያወራ ተሰምቶ አይታወቅም።በስህተት እንኳ ቢያወራ ዞላ ቁምነገር በአንተ አያምርም ብለው አፉን ያዘጉታል።ቤተሰቦቹ ተጭነው ስላሳደጉት ግቢ ከገባ ቀን ጀምሮ እንደልቤ ሆኗል ።ተከልክሎ ያደገ ልጅ ስለሆነ አሁን ያየው ሁሉ ያምረዋል።ሁሉን ቀማሽ ሆኗል።በእነዚህ ትንሽ ወራት ውስጥ ሀይለኛ ሱሴ ሆኗል።በዚህ ፀባዩ ዮርዲ ሁሌም ይናደዳል ።
👉ዮኒ ማለት ቁምነገር ነው ምክንያታዊ ሰው።ወሬወቹም ድርጊቶቹም በምክንያት የተደገፉ ናቸው።ተከራክሮ የማሳመን አቅሙ በጣም ከፍተኛ ነው።ድንጋይን ዳቦ ነው ብሎ ሊያበላ የሚችል ሰው ነው።ከዮርዳኖስ ጋር ልብ ለልብ ተገናኝተዋል ።
👉ዜኖ ማለት ካላወሩት የማያወራ ከዶርሙ ለየት ያለ ባህሪ ያለው ሰው ነው።ዶርም ከጓደኞቹ ጋር የሚያሳልፈው ጊዜ ኢምንት ነች ።የትኛውም እንቅስቃሲያቸው ላይ ተሳታፊ አይደለም።ስለ ህይወቱ ስላሳለፈው እና ስለሚኖረው ላይፍ ለማንንም ትንፍሽ አይልም ቁጥብ ነው።ጓደኛው ሀንድ አውት ብቻ ነው።
👉ዮኒ ጎጄ ማለት ነገሮችን አጋኖ የሚያወራ የጠበበውን አስፍቶ ያላየውን ምስል ፈጥሮ ያልሰማውን ጥሩ ተረት መስርቶ ያልሆነውን ሆነ የማይሆነውን ይሆናል ብሎ የሚናገር ልጅ ነው።ታዲያ ለጨዋታ ድምቀት እንጂ ነገር ማስፋት ሱስ ሆኖበት አይደለም።ቁምነገር ላይ ቁምነገረኛ ነው።
👉ናቲ ማለት አወዛጋቢ ሰው ነው።እንዲያውም አንዳንዴ ሳሙና እያሉ ይጠሩታል።ያሙለጨልጫል።ዶርም ነኝ ብሎህ ካፌ ታገኘዋለህ።ካፌ ነኝ ብሎ ኳስ ሲጫወት ይገኛል ።ክላስ ልገባ ነው ብሎ ቴኒስ ሲጫወት ትይዘዋለህ።ታዲያ ነገሮችን በእቅድ ያለመምራት ችግር እንጂ ሌላ አመል አይደለም።
👉ዮርዲ ያው ሔዋን ከመለየቱ በፊት እንደነበረው ተጫዋች ባይሆንም።በመጠኑም ቢሆን ይቀልዳል ይጫወታል።

ሔዋን እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ ወደ ሔኖክ ቢሮ አመራች።ኮሪደሩን አቋርጣ ከቢሮ ስትደርስ ለማንኳኳት እንኳን ጊዜ አላገኘችም።በሩን ከፍታ ገባችና ፈቃድ እንኳን ሳታገኝ ከእንግዳ መቀበያው ወንበር ላይ ተቀመጠች ።
ሔኖክ በአግራሞት ሲመለከታት ከቆየ በኋላ"ሔዋን ምነው የሆንሺው ነገር አለ እንዴ?"አለ
"አቶ ሔኖክ እየሆነ ያለው ነገር ምንም ሊገባኝ አልቻለም"አለች ለምቦጯን እንደጣለች ።
"ሔዋን በመጀመሪያ ደረጃ አቶ እንዳትይኝ ብዬ ደጋግሜ ነግሬሽ ነበር።ሲቀጥል ነገሮችን ተነጋግረን መፍታት እየቻልን እንደዚህ መቆጣቱ አስፈላጊ መስሎ አይታየኝም"አለ ሔኖክ
"እንዴት ነው የምረጋጋው?እዚህ አዳራሽ ውስጥ ታግቼ ይሔው ስድስት ወር ሞላኝ።ለወንድሜ ጉዳይ ብላችሁ አምጥታችሁ ምግብ ቀቃይ አድርጋችሁ አስቀመጣችሁኝ።ሔኖክ እውነት በቃኝ ከዚህ በላይ መታገስ አልችልም ወደ ቤቴ ነው መሔድ የምፈልገው"አለች ሔዋን ።
ሔኖክ የተናገረችውን በአፅንኦት ሲያዳምጥ ከቆየ በኋላ"ሔዋን ትዕግስትሽ ይቺ ብቻ ከሆነች መሔድ ትችያለሽ እውነቱን ልንገርሽ ለዚህ ፕሮጀከት ምናሴ እና አባ ቶማስ ሲመርጡሽ አኔ ተቃውሜ ነበር።ደግሞም ልክ ነኝ ህፃን ነች ብስለት ይጎድላታል ብየ ስናገር አይ እንደ እድሜዋ ሳትሆን እድሜዋን ቀድማ የሔደች በሳል ነች አሉ።ግን የታለ ብስለትሽ"ብሎ የመውጫ ወረቀት ፅፎ ሰጣት ።
ወረቀቱን ቆሻሻ ማስቀመጫ ቦክሱ ውስጥ ጣለችና"አይደለም እኮ ሔኖክ የፕሮጀክቱ አላማ እኮ ምንም አልገባኝም ደግሞስ ወንድምሽ ጋር ትሔጃለሽ ብላችሁ አምጥታችሁ በእኔ ተርታ ሌላ ሰው ላካችሁ እኔም እኮ ግራ ቢገባኝ ነው"አለች ሔዋን በሔኖክ ንዴት ደንግጣ ።
"እሺ የፕሮጀክቱን አላማ ማወቅ ነው የፈለግሽው?እንግዲውያስ እዚሁ ጠብቂኝ"ብሎ ሔኖክ ክፍሉን ትቶ ወጣ ።
ሔዋን ስህተት የሰራች መስሎ ተሰማት "ከመናገር በፊት ማዳመጥ ከስህተት ያድና
ል"የሚሉት የአባ ቶማስ ንግግር ከጀሮዋ ሲያቃጭል ወይኔ ምን ይሻለኛል?ሔኖክ ምን ያደርግ ይሆን ብላ አሰበች ።
ከደቂቃዎች በኋላ ሔኖክ ኢያሱን ይዞ ገባና ከሔዋን ፊት ለፊት አስቀመጠው ።
"ኢያሱ ከየት እንደመጣህ እና ለምን እንደመጣህ ለሔዋን ንገራት?አለ ሔኖክ ትዕዛዝ በተሞላ አነጋገር
"የአቶ ኢሳያስ ተ/አረጋይ ብቸኛ ልጅ ነኝ ከአዲስአበባ ከመጣሁ አንድ አመት አለፈኝ።ለምን እንደመጣሁ አላውቅም ግን በጉጉት እየጠበቅኩ ነው ለጥሩ ነገር እንደተመረጥኩ ይሰማኛል።ለምን እንደመጣሁ እስኪነግሩኝ ድረስ ያው ሴራሚክስ አምራቹን ቡድን እየመራሁ ነው ።"አለ ኢያሱ
"መሔድ ትችላለህ "ብሎ ሔኖክ ኢያሱን አሰናበተው
"ሔዋን አሁንም ልሒድ ካልሽ መብትሽ ነው አስገድደን ልናቆይሽ አንችልም።አንድ ነገር ግን ቃል የምገባልሽ ምናሴ ነገሮችን አስተካክሎ በቅርቡ ከአሜሪካ ይመልሳል ያኔ ስራችንን ለአንቺ ብቻ ሳይሆን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ እናደርጋለን።እስከዚያ ለሴራሚክስ አምራቹ ቡድን ከእነሱ ጋር ምግብ ማዘጋጀት አይከብድሽም።"አለ ሔኖክ
ሔዋን በቅርቡ ወንድሟ እንደሚመጣ ስትሰማ ውስጧን ደስታ ሞላት "ፕሮጀክቱን ለማወቅ ከተነሳ ጉጉት የመነጨ ስሜት እንጂ በሌላ አትተርጉመው።ይቅርታ ሔኖክ"አለች ሔዋን
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሔዋን ክፍሏ ገብታ ሰሞኑን ስለመጣው ልጅ እያሰበች ነበር።ስታየው ዮርዳኖስን እየመሰላት ትደናበር ይዛለች።አንድ ቀን ይሔ መደናበሯን ተመልክቶ "እናት እንደዚህ ከምትደናበሪ አፈቅርሀለሁ ብለሽኝ እርፍ አትይም እንዴ"ብሎ አሾፎባታል።
ታዲያ እሷም አልተደናበርኩም ለማለት ያህል"ምን አይነት እብድ ነው ያመጡብን ሲያስጠላ።"ብለዋለች።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሔዋን ክፍሏን ቆልፋ ወጣች እና ሴራሚክስ ማምረቻ ድንኳኑ ፊት ለፊት ካለው የዘንባባ ዛፍ ጥላ ላይ ተቀመጠች ።ቡድኑ ላይ ተፍ ተፍ ከሚሉት ወጣቶች መካከል ከእንግዳው ልጅ ጋር አይን ለአይን ተገጣጠሙ።ሔዋን ደነገጠች እና አንገቷን ደፋች።ልጁ በሲሚንቶ የተጨማለቀ እጁን ቧንቧው ላይ ታጠበና በለበሰው ዩኒፎርም እያደራረቀ ተጠጋት።ሔዋን መሬት ተከፍታ ብትውጣት ደስተኛ ነበረች።እጇን ጨበጣት እና ከጎኗ ተቀመጠ።
"ቃለአብ እባላለሁ" ብሎ ፈገግ አለ።
"ሔዋን" አለችው ኮስተር ብላ
"እንዴት እዚህ ልትመጪ ቻልሽ?" አለ
"እንዴ አንተን ልጠይቅህ እንጂ ገና ሳምንት ሳይሞላህ ስድስት ወር የተቀመጠን ሰው እንዴት መጣሽ ይባላል?"አለች
"ኦ ይቅርታ፤እኔን አባ ቶማስ ናቸው ያመጡኝ ትልቅ የትጥቅ ትግል እንደሚጠብቀኝ ነግረውኛል"አለ ፈገግ ብሎ
"የት ነው አባ ቶማስን የምታውቃቸው?"አለች
"ለእኔም ለእናቴም የንስሐ አባት ናቸው"አለ
"ልክ እንደ እኔ ማለት ነው።እሳቸው ግን ለዚህ ቦታ ትመጥናለህ ብለው መምረጣቸው ገርሞኛል" አለች
"ምን ለማለት ፈልገሽ ነው ባክሽ ?"አለ ትክ ብሎ እያያት
"ቃለአብ ስራ ትተህ ነው የመጣኸው"አለችው
ለመሔድ እየተነሳ"ግን ስታይኝ አትደናበሪ እንደምታፈቅሪኝ ንገሪኝ ልረዳሽ ዝግጁ ነኝ"ብሎ ትቷት ሔደ።
ሔዋን ደነገጠች ባለችበት ፍዝዝ ብላ ቀረች።

ይቀጥላል

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
HTML Embed Code:
2024/06/18 14:12:50
Back to Top