.......... ''ኪሎ ስንት ነው?'' እንድታየኝ ነበር የጠየኳት። እሷ ግን ስራዋ ላይ እየተዋከበች ''65'' ብላ ለሚያጣድፋት ደንበኞቿ ትመዝናለች። የትላንት ውበቷ እና መኮሳተሯ ዛሬም ደምቆ ይታያል። አንዴ እንኳን አታየኝም እንዴ እያልኩ ሰርቃ አየችኝ። የምገዛትን መጠኑንን እንደነግራት ይመስላል። ''በቃ ሁሉንም ልውሰድ '' አልኩኝ። ከልቤ! ሁሉም አፈጠጠ የእሷ ደግሞ ግልምጫም አለው። '' ዞር በል በናትህ '' ብላ አመናጭቃ ማስተናገዷን ቀጠለች። የቀሩት አንድ ያረጁ እናት ነበሩና 5ኪሎ እንድትመዝን አድርጌ ቅድሚያ ብሩን ሰጠኋት። ቡናማ ሻሽ ያሰሩት እናትም መረቁኝ ና ተቀብለው ከፊቷ ዘወር አሉ።
እኔ ግን ከመሸጫዋ ቦታ አልተንቀሳቀስኩም። '' ሌላውን ትመዝኚልኝ?'' አልኳት። እኔን አለማወቋ እየደነቀኝ። በምደነግጥለት ግልምጫዋ እምቢታዋን አሳየችኝ። ፈገግ ብዬ '' አላወቅሽኝም?'' መነጽሬን እያወጣሁ ጠየኳት። አየችኝ ውስጥ ድረስ መረመረችኝ። '' ስራ የፈቱትን አላውቅም '' አለች። የተናደውን እየደረደረች። ''የምርሽን ነው ጹጹ'' አልኩ። ጣረ ሞት ከፊቷ የቆመ ይመስል አፈጠጠች። መላ አካሏ ደረቋላ ከግንባሯ ላይ ችፍ ያለው ላብ ድንጋጤዋን አልደበቀም። '' ጹጹ'' ደገምኩላት። ሀሞት የቀመሰች ይመስል ተርገፈገፈች። '' ምን አይነት ቅሌታም እና ደፋር ነህ ከፊቴ የቆምከው'' ብላ ተነሳች።
ያልጠበኩት ነው የተፈጠረው። እታቀፋለሁ ብዬ ልቀጸፍ መሆኑ ቢገባኝ ወደኋላ ፈቅ አልኩ። ''ተረጋጊ እንጂ ጽዮን '' አልኩ በመታወቂያ ስሟ። '' ውረደት ሳላከናንብህ ከዚህ ጥፋ'' አለች። '' ቆ...ይ...እ....'' አላስጨረሰችኝም። ''ዞር በል አንተ ሰውዬ ሬሳህ እንዳይጎተት'' አለች እንደ ነጎድጓድ በሚያስገመግም ድምጿ። ዙሪያዋ ያሉት የሆነው ባይገባቸውም ከተቀመጡበት ተነስተዋል። አንድ ወጣት ጎረቤቷ ከሱቁ ዘሎ ወጥቶ ወደ እኔ መጣ። እጄን እየጎተተ መንገዱን እየመራኝ '' ይቅርብህ ከጹጹ ጋር ሙግት። ከተነሳባት ለእኛም ይተርፋልና ፍንጣሪው ሌላ ቀን ተመለስ። '' አለኝ። ዞር ብዬ ሳያት ወደ ስራዋ ተመልሳለች። የትላንት እልኋ ዛሬም ነበልባል ነው። ወጣቱ ትንሽ ሸኝቶኝ አሰናበተኝ። እኔም ያቆምኩትን መኪናዬን አስነስቼ ወደ ቤቴ መንገድ ጀመረኩ።
ጽዮን እልኸኛ ጽዮን ጣይቱ ዛሬም በኑሮ ስብራትም አልደቀቀችም። እንደትላንት በሚያውቋት ፊት ክቡር ናት። እሳተ ነበልባሏ ያስፈራል። ዘንድሮም ትፈጃለች። በመስኮቴ የሚገባው ንፋስ ትላንትን እየጎተት ያሳየኛል። ሰው እንዴት እንዲህ ይኖራል ከዕድሜ ብዛት አይበርድም አይደክምም። ጽዮን ያው ጽዮን ናት። መልኬን መርሳቷስ የዚህን ያህል ምን ጋር ተቀይሬ ትላንት የምትወደው የታመነችለት ፍስሃ ነኝ። እንዴት ረሳችኝ። እሳቷ ራሷን ፈጃት እንዴ። ...............ነገ አገኛታለሁ።
✍️ርዕስ የለውም❤️🩹
🥀🌿🌱ክፍል 1🍁🍁🍁🍁
🖋️የቤዛዊት ሃሳብ
@yebezigetmoch
#story #time
>>Click here to continue<<