መስዋዕት ሁኚ
ሴት አይደለሽ ነይ ወደ ወደፊት
ትማሪ ዘንድ ስለ መስዋዕት
መላሽ ጆሮ አድርገሽ በልብሽ ከትቢ
ለመስዋዕት ተዘጋጅተሽ አበቢ።
ትኩስ ነው ውበት እሳተ ነበልባል
አላፊ አግዳሚ የሚበላ ዳግም የሚያባብል
አይራ'ቅም ከእሳት መድኃኒት ለክረምት
አይተው ደግሞ ተፈርቶ መፈጀት
ይህ ውበት እንዳው ከረገፈ
ከጊዜው ጎዳና ካለፈ
ጸጸት ነው ጸሀይ ስትዘቀዝቅ
ነፍስ ካላገኘች ሃቅ!
የሴትነትሽ ሃቅሽ መስዋዕት መሆን ነው
በአንቺ ነውና አዳም የሚበረታው
ስህተቱ ብትሆኚ ድኅነትም ሆነሻል
የእልፍ ዘመን መከራ በሴት ተፈጽሟል።
ለአዳምሽ ተሸሸጊ ለሁሉ አትታይ
በዘመን አትለኪ በሴት ልኬት ብቻ ታ'ይ
ለመወደድ ውደጂ ልብሽን ገብሪ
በአዳምሽ ጎን ፍቅር ዝሪ
በዕድሜሽ ከውበት በላይ ምግባርን ዘክሪ።
ያከብርሽ ዘንድ የልባምነት ዘውድ እንድትደፊ
የስጋ ሃሳብሽን በነፍስሽ በልጠሽ እለፊ
ጌጥሽ ይሁን ትህትና
እንግዳ ይመላለስ ከእልፍኝሽ ጓዳ።
ፋሲካ ሁኚ ደስታሽን ይትረፍ ለሌላ
ትንሳኤ ሁኚ ለድሃ ከለላ።
ራስሽን ተይ ከመታበይ ውጪ
መስዋዕት ሁኚ ለሴትነትሽ ከስጋ ድካም አምልጪ
ለክብር ልዕልና በራስ ዜግነት በሴትነት ታጪ።
❤🥰
ሴትነትሽ ከዓለም ለይቶ ይፈትንሻል የማትወጪው የመሰለሽ ነገር ሁሉ የሚታለፍ መሆኑን አስበሽ ከመልክሽ ይልቅ በልቦናሽ ላይ ስሪ። በፈጣሪሽ ቤት የምታበሪው መብራት ምግባር መሆኑን አስበሽ ስጋሽን ሰቅለሽ ለነፍስሽ ድከሚ❤ ለአዳምሽ ታዘዢ ለቤትሽ መልካም ፍሬ ሁኚ ለልጆች እናት ለሰራተኞችሽ ሰብሳቢ ለወዳጆችሽ መጽናኛ ሁኚ።
✍️ ቤዛዊት የሴትልጅ
ሚያዝያ 14/2017 ዓመተ ምህረት
>>Click here to continue<<