አደራ ጠርጥሪኝ
ስምሽን ስሰማ እንባ አይኔን ካሞቀኝ
ስላንቺ ሳወራ ሳግ ደርሶ ካነቀኝ
ፀሀይ ከበረደኝ ሳቅ ከኔ ከራቀ
መከፋት ደስታየን ከእኔ ከሰረቀ
አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ
በእብዶች መካከል ደህና ከተሰኘሁ
በዝናብ ሲርሱ ደርቄ ከታየሁ
በትልቅ ሰው ለቅሶ ሳቄ ካመለጠኝ
ሀገር ባሳቀ ቀልድ እንባ ካጠመቀኝ
አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ
ከጨረቃ ጋራ ሳወጋ ካመሸሁ
ከሚያውቁሽ ከሚያውቁኝ ከራሴ ከሸሸሁ
አለም ከደበተኝ ከከረፋኝ ሀገር
በሆነ ባልሆነው ካለኝ ነገር ነገር
አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ
ይሄው አሁን እንኳ
ስላንቺ እየፃፍኩኝ ላብ ሞልቷል ግንባሬ
ቁጭ ብየ ራሱ ልሩጥ ይላል እግሬ
እኔ እወድሻለሁ ማለቱን ትቻለሁ
በስምሽ መማሉን ረስቼዋለሁ
ለምን ለምን ለምን
ለምን አንቺን ብቻ ለምን ከሰው መርጦ
የሚያርበተብተኝ
የሚያብሰከስከኝ ከሌላው አብልጦ
....ማለቱን ካበዛሁ
አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ
አወ ናፍቀሽኛል አልክድም ወድቄ
ዝም ብለሽ ነይልኝ አታብዢ ጥያቄ
መልሴ ሁኝኝና
ከወደቅኩበት ጥግ ነይ ፈልገሽ አንሺኝ
መራቅሽ አሞኛል በመቅረብ ፈውሺኝ
አደራ......
https://hottg.com/yebezigetmoch
>>Click here to continue<<
