TG Telegram Group Link
Channel: ወግ ብቻ
Back to Bottom
ከ 35 እስከ 40 አመት እድሜ ክልልን ስትመታ ወይም ስትቃረብ ነገሮች ይቀየራሉ

ምን ይቀየራል?

👇🏾

ወላጆችህን: ቤተሰብህን: ወዳጆችህን: ፍቅረኛህን: ልጆችህን ወደህ ወደህ በስተመጨረሻ ራስህን መውደድ ትጀምራለህ

የአለም ችግር በአንተ ጫንቃ ላይ የወደቀ ነገር አለመሆኑን ትረዳለህ: የሚያብሰለስሉህ ነገሮች እና ምክንያቶች ይቀንሳሉ

ከምስኪኖች ጋር በጉሊት ንግድ ሂሳብ መከራከር ታቆማለህ: ተፍ ተፍ የሚል ሰው ስትመለከት ከአንተ ኪስ ይልቅ የእነርሱ ላብ እና ድካም ይበልጥብሃል

አንድ ሰው የሆነን ታሪክ ደግሞ ቢነግርህ "ነግረኸኝ ነበር እኮ" ብለህ አታሳቅቅም: መደመጥ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ስለምትረዳ ታሪኩን ታስጨርሳለህ - ምናልባት ሰውዬው ታሪኩን ሲያወራ ትዝታውን እያደሰ ይሆናል

ሰዎችን በየሚሰሩት ስህተት ፌርማታ እያቆምክ ማረም ይደክምሃል: የዚህችን አለም ስህተቶች የማረም ሃላፊነት የአንተ እዳ እንዳልሆነ ትረዳለህ

ከልብስ ይልቅ ማንነት እንደሚበልጥ ትረዳለህ: ከምግብ ይልቅ የውስጥ ሰላም ዋጋ እንዳለው ይገባሃል

ከአንተ በእድሜ ያነሱ ሰዎች አጉል አራዳነት ሲጫወቱ እና ያለፍክበን መንገድ ሲሄዱበት አያናድድህም: "እድሜያቸው ነው" ብለህ ታልፋለህ እንጂ አትበሳጭም

ከማያከብሩህ ሰዎች እና የማትፈለግበት ቦታ አትውልም: ራስህን አክብረህ ገለል ትላለህ እንጂ

የሚተናነቅህ ግብዝነት አይኖርም: በመተው ታምናለህ - ሰዎችን ከማሳደድ ይልቅ ለህሊናቸው አሳልፈህ መስጠት ትመርጣለህ

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Zemelak endrias
" ትወደን የለ አበርታን "

( መውደዱን ለመግለፅ ማኖሩ አይበቃም ? )

ካሊድ አቅሉ

~   ~   ~   ~   ~    ~   ~    ~    ~    ~

ትወደኝ የለ አበርታኝ ትለዋለች አንድዬን እንደሚወዳት እንዴት በእዚህ ልክ ተማመነች ? መማፀንዋ አጊንታው መውደድዋን የገለፀችለት ይመስላል ምንዋ ተነክቶ ነው በእዚህ ልክ ፈጣሪን የተማፀነችው ?  ልጠይቃት አስቤ በማያገባኝ መግባት መስሎ ተሰማኝና እራሴን ቆጠብኩ ። ለሶስት ሰዓት ሙሉ ሊክቸሩ ሲያስተምር እሷ አርሚቸር ወንበርዋ ላይ " ትወደኝ የለ አበርታኝ " ብላ ፅፋ እሱኑ ታደምቃለች ፊትዋ ጥቁር ብልዋል ከፍቅረኛዋ ጋር ተጣልታ ይሆን ?

" ይቅርታ የኔ ውድ ካስከፍሁ እንታረቅ " ብላ  ባለንጋ ጣቶችዋ ፀጉሩን ስትዳብስ በምናቤ ታየኝ ። ፍቅር አለብኝ መሰለኝ የእሷዋን መከፋት ከወንድ ጋር ብቻ አያያዝኩት ። እሷ ቃሉን በማድመቅ ላይ ናት ። አይንዋ ያሳሳል ሆድ ያስብሳል አላያትም ብለው ቢገዘቱ የሚረታ ውበት አላት ። በሀሳቤ ፈረስ ስጋልብ የተማሪዎች ጫጫታ  አነቃኝ አይኔን  ቀና ሳደርግ ከሰሌዳው ላይ (Quiz) የምትል ፅሁፍ አስተማሪው አሳርፈው አየው ። ከሴት ፈተና ወደ ቀለም ፈተና ይሄን እስተማሪና ህይወትን ሚያመሳስላቸው ነገር ሳይናገሩ መፈተናቸው ነው ። እኔም ወረቀት አወጣውና እንዲ ብዬ ቃል አሳረፍኩ ( ትወደን የለ አበርታን )
" በእዚህ ልክ እንደሚወዳቹ በምን ተማመናቹ ?" ለምትሉን ጭንቁ ሲጠናብን አንድ መልስ አዘል ጥያቄ እናቀርባለን . . .
(መውደዱን ለመግለፅ ማኖሩ አይበቃም ?)
~  ~  ~  ~  ~   ~    ~   ~   ~ ~ ~  ~

@wegoch
@wegoch
@paappii
"  ብሌኔ ትለኝ የል?"
"አዎ"
"ያላንቺ በድን ነኝም ብለኸኛል"
"ነኝኮ"
"ታዲያ ትተኸኝ አትኺዳ? በሌን ብቻዋን ምን እርባን ይኖራታል"
"እማዬ ሆዴ! አዎን ማያዬ ነሽ።የእናቴ  ቤት እየተቃጠለ ዓይኗን እየጠነቆሉባት ዓይኖችሽን እያየሁ በፍስሃ ልኑር? አተላ ነገር ነው የሚሆነው።"
" አንተ ብቻህን ምን ትፈይድላታለህ?"
"ለዛ አይደል መኼዴ?   እንደኔ አይነት ብዙ ወዳሉበት"

   "የኔ ጌታ እሺ በለኝና አትሂድ....ምንም አልዋጥልሽ እያለኝ ነው"
"እእእ አሁንስ?" አላት ከአገጯ ቀና አድርጎ ከንፈሯን ከሳማት ኋላ።

ምንም ቃል ሳይወጣት ለደቂቃ አሻቅባ እያየችው ቆየችና ድንገት በሁለቱም ዓይኖቿ እንባዋን ታረግፍ ጀመር

"እናት እንዲሁ ከብዶኛል እንባሽ ተጨምሮ አልችለውም " አለና ለራሱ ደረቱ ላይ አጥብቆ አቀፋት።

"አንቺን ሲነኩሽ ማሰብ አልችልም ።ያቺ ሰባት ወንዶች የደፈሩዋት .... ተይው ግን እሳቱ የተቀጣጠለበት ኼደን ካላጠፋነው እሱ  መቶ ያቃጥለናል ።"

"እግዜሩ ካልቀጣቸው ሰው በምን አቅሙ ያኚን ጋኔን ይመክታል?  አላማረኝም ተው......"
"አልተውም 😂"ግንባሩዋን ጉንጮችዋን አገጭዋን አይኖችዋን ከንፈሩዋን ተራ በተራ ስሞ ሲያበቃ "
"አንቺን የመሳሰሉ ጥኒኒጥ ልጆቼ አኚህ የሳጥናኤል ተኩላዎች ባሉበት ተወልደው እንዲያድጉ አልፈልግም" አላት በዓይኖቹ ዓይኖቿን አተኩሮ እያየ።

ምንም ብል ድካም ነው ብላ አሰበችና ዝምታን መረጠች።  ዓይኖቻቸው እንደተገለጡ እኩለሌሊት ካለፈ ወዲያ እንግላል በተኛበት  ክንዱዋን ደረቱ ላይ አስሞርክዛ ቀና አለችና ቁልቁል ስትመለከተው

"ባንቺ አየን ያንድዬን ስራ
ያለእቅድ እንደሚሰራ
ፈጣሪ ተራቆብሻል
ጥበቡን ማሳያ አርጎሻል"እያለ ማንጎራጎር ጀመረ።
"ስሜትህን ለመደበቅ አትጣር ,የእውነት ምን እየተሰማህ ነው?"
                 "እስከዛሬ ሽቅብ አይቼሽ አላውቀውም ወይ ቁልቁል አይተሺኝ አታውቂም? መኮሮኒ አፍንጫ አይደለሽ እንዴ""
"ጌታ የምሬን ነው" አለች ቆጣ ብላ።
"ጌታን እውነታው ጎራዳ ነሽ"
"ታውቃለህ ግን.......ኡፋ እንደውም ተወው በቃ"አለችና ደረቱ ላይ ተኝታ እጇን ፀጉሩ ስር ሰዳ ማሻሸት ጀመረች።
" ዎ አትነካኪኝ,  ለሊት መንገደኛ ነኝ ይደክመኛል"
"ስድ ! ሂድ ወደዛ"
"ነይ ወደዚ😂😂" ከትከት እያለ ሳቀ።ከደረቱ ላይ ተነስታ ጀርባዋን ሰታው ተኛች።እየሳቀ ዞረና ፊቱን አንገቱዋ ስር ሸጉጦ እጁን በወገቡዋ አዙር ሆዷ ላይ አደረገና እቅፍ አደረጋት።

ዓይኗን ስትገልጥ ወገግ ብሏል ።ዞር ስትል ብቻዋን ነች።የሌሊት ልብሷን እንደለበሰች ወርዳ ሩጫ ጀመረች።ቦታውጋ ስትደርስ ማንም አልነበረም።ጠጋ አለችና የመስሪያ ቤቱን ጥበቃ
"ምልምሎች የሚሳፈሩት ከዚህ አልነበር እንዴ? አባቴ"
" አዎን ከዚሁ ነው በለሊት ወጡ እኮ"

እጢዋ ዱብ አለ።
" አላለቅስም!! ሰው መንገድ ሲኼድ አይለቀስም ሰላም ተመለስ ነው ሚባለው"ብቻዋን እንደእብድ እያወራች ወደ  ቤቷ ገባች።ከዚያች እለት በኋላ ያወቁዋት ሰዎች
"ፍንጭታም ነች ወይንም ጭርሱንም ጥርስ የላትም ይሆናል" እያሉ ያሟታል።ቀበሌ የሚሰራ ሰው ቤቷ አቅራቢያ ስታይ ጉልበቷ ይከዳታል በእጃቸው ወረቀት ይዘው ከሆነ ደግሞ ሰው "አበደች?"
እስኪላት አሪ እያለች ታለቅሳለች።ቤቷ ሚመጣ ሁሉም ሰው ሊያረዳት የመጣ ይመስላታል ።

   የፈሩት ይደርሳል ሚሉት እውነት ይመስላል።ጎህ ሳይቀድ ተሰብስበው በሯን አንኳኩ ።ከፍታ እንዳየቻቸው እንባዋ ረገፈ። ደብዳቤው ምን ይላል አላለችም ።ሃገሬው ለሁለት ተከፍሎ ገሚሱ በሷ የደረሰ በማንም አይድረስ ሲል ሌላው አሟርታ ገደለችው አላት።

ይህ ከሆነ ከወራት በኋላ ሰፈሩ ዳግም በለቅሶ ድብልቅልቅ አለ።

     መጣ!!!
ሞቷል የተባለ ሰው በህይወት ሲመለስ እንዲህ ያስለቅሳል ማለት ነው በማለት እየተገረመ መልሶ መልሶ
"የታለች?" ሲላቸው ።
"ሞትህን መቋቋም ከብዷት እራሷን አጠፋች" ብለው መለሱለት።ተሰብስቦ የሚያለቅሰውን ሰው እየከፈለ ወቶ ኼደ።አልተመለሰም።

ሰብሰብ ብለው ከቤተክርስቲያን እየተመለሱ እመንገድ ዳር ላይ የተቀመጠውን እብድ እየተመለከቱ
"አዪዪ ያን የመሰለ ልጅ እምጽ ...እንዲ ከምያንገላታው በገደለው" ያሻቸውን እንዳሻቸው ፈረዱበት።ስንቱ ይሆን ለነሱ ጋሻ ልሁን ብሎ በተመሰቃቀለ "በገደለውን" ያተረፈ አመድ አፋሽ ።
    
ጫሪ Enat Kassahun @ethioma1

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ከፋኝ ብዬ ነበር ብቻዬን የሆንኩት ። የምፈልገው ነገር አልሆነም ብዬ ነበር የተሸሸግኩት ።

ጠይም ናት ሳቂታ ። ደሞ ስትስቅ ታምራለች ስታወራኝ ረጋ ብላ ነው ። ተገናኝተን ሳንስቅ ሳንሿሿፍ ቀርተን አናውቅም ። ከሆነ ግዜ በፊት የሆነ ወቅት ባገኛት ብዬ አስቤ አውቃለሁ ።

ለምን ለኛ የሚሆኑ ሰዎች ወይ ፈጥነው ወይ ዘግይተው ይመጣሉ ? በሰዓቱ ለምን አይመጡም ??

አለመገጣጠም ከመተላለፍ ይሻላል !!።

ናይል ድብርት የሚያጠቃት ናት ። ናይል ድብርቷ እየተባባሰባት ነበር። "አግዘኝ መደበር ተስፋ ቢስ መሆን ደክምኛል" አለች።

"እሺ" ብዬ አቀፍኳት ። እንድለቃት አልፈለገችም ነበር። ስለድብርቷ ገምቼ አውቄባት እንጂ በቃሏ ምንም ብላኝ አታውቅም ነበር ። ከእቅፌ ሳስወጣት አይኗ እምባ ነበረበት ።

ከሶስት ቀን በኋላ ሁሉ ነገር ሲሰለቸኝ ። ስልኬን ዘጋሁት ብቻዬን ሆንኩኝ በተቻለኝ መጠን አልጋዬን ላለመልቀቅ ሞከርኩ ።

ከአስራ ሶስት ቀን በኃላ ስልኬን አበራሁኝ ። ናይል ቴክስት ልካልኝ ነበር "ፈልጌሃለሁ" የሚል ወድያው ናይል ጋር ደወልኩ ስልኳ ዝግ ነበር ደጋገምኩት ያው ነው ። በአስራ አራተኛው ቀን እቤቷ ሄድኩ : ናይል አልነበረችም ።

ሰፈሯ ስሄድ የሚጠራልኝ ልጅ ፣ባለሱቁ ፣አከራይዋ ሁሉም ራሳዋን አጥፍታለች አሉኝ ።

ስላላመንኳቸው ሁሉንም ደጋግሜ ነው የጠየኳቸው ሁሉም ፊታቸው እውነታቸውን እንደሆነ ያስታውቃሉ ።

እንዴት እንደከፋኝ ....

መኖር እፈልጋለሁ አግዘኝ እያለችኝ ። እራስ ወዳድነት ነው መሰለኝ እንዳልሰማት ከለከለኝ ።

ሞቷ ውስጥ እጄ አለበት ። ለመሞት ስትመቻች ሸኝቻት ነበር ።
ስቅስቅ አልኩ ። ድብርት ሀዘን ከፀፀት ጋር ከባለፈው በላይ አዝረከረከኝ ። ስልኬን መዝጋት ፈልጌ ነበር እንደ ባለፈው መደበቅ ፈልጌ ነበር ።

ፈራሁ የሆነ ሰው ሲጠራኝ ባልሰማውስ ?፣ ቢያመልጠኝስ ?

ለራስ ብቻ መኖር ለካ አይቻልም!!


By Adhanom Mitiku

@wegoch
@wegoch
@paappii
አባቴ ሁሉ ነገርን መጋፈጥ ይሰብራል ይላል ። ጀግና ሁኔታን የሚረዳ ነውም ይላል ።

እኔ የምጋፈጠው ለማሸነፍ ጀግናም ለመሆን አይደለም ሲደርሱብኝ ነበር ።

አፈግፍጌ አውቃለሁ ። ያፈገፈኩኝ ግዜ የሚሰማኝ ስሜት መጥፎ ነው ።

አባቴ "የማያፈገፍግ ታጋይ በቶሎ ይሞታል" እያለ የውትድርና ገጠመኙን ያጣቅስልኛል ።

በሂወቱ ምድር ላይ እንደኔ የሚጨነቅበት ጉዳይ ያለ አይመስለኝም

"እሱ ማስረዳት አይችልም በዛ ላይ ያፈጣል ....ችግር የሚፈታው አንገት ለአንገት በመተናነቅ ይመስለዋል" ይላል ።

"አንዱ ይገለዋል አጉል ቦታ ይመቱታል የሰው ሰው እጁ ላይ ይጠፋል" ይላል

"እኔ በሂወት የኖርኩት እጅ ሰጥቼ ነው ። ይሄው ከዛ በኃላ ያገኘሁት መዓረግ እና ደስታ ይቆጠራል ?? "

አባቴ ትኩረቱ ስለሆንኩ መሰለኝ
ልጁ ስለሆንኩ መሰለኝ
ስላሳደገኝ መሰለኝ
ስለሚያስብልኝ መሰለኝ

ከኔ በተሻለ እኔን ያውቀኛል ። ስለኔ ገምቶ የተሳሳተበት ግዜ አላስታውስም

"በጠበል አልወጣ ያለ ጂኒ አለበት" ይላል ።

የሆነ ቀን ተሳካልኝ ልጄ ልብ ገዛልኝ ስለቴ ሰመረልኝ ብሎ በመሃበርተኛው ፊት ተናዞ ስለቱን እንዳስገባ የመሃበርተኛው ልጅ አዲሱ ነገረኝ

ስለት ካስገባበት ቀን ጀምሮ ሳሰላስል ልብ ገዛ እንዳለው አይነት ሰው ሆኛለሁ ።
ደርሰውብኝ ያለፍኳቸው ቀምተውኝ የተውኳቸው ትተውኝ ያለቀስኩበት ስፍራ ብዙ ነው ።

ምን ብሎ ተስሎ ይሆን ስለቱ የሰመረው??

ምን አለ አሁን ትልቅ ህልም እና ህልሙን መተግበርያ ጥንካሬ ስጠው ብሎ ቢሳልልኝ

By Adhanom Mitiku

@wegoch
@wegoch
@paappii
በሰርጓ ቀን ያማረባት ብቸኛዋ ሴት ናት ለኔ ­-የአጎቴ ልጅ ሜሪ።

እንደሌሎቹ የሜካፕ ናዳ ፊቷ ላይ አዝንባ፤ አዲስ መልክ ይዛ አልመጣችም፤ ያው...እግዜር አንዴ ተጠብቦ ተጨንቆ ሰርቷት የለ? ከዚ ወዲያ የሜካፕ ባለሞያዎች ከማበላሸት በቀር ምን ይጨምራሉ?- ምንም።

ንጥት ያለው ቬሎዋ መሬት ላይ፤ የተፈጥሮ ፀጉሯ ደሞ ጀርባዋ ላይ ተንፏሏል፤ ውብ ገጿ ላይም አንዳች ሚያክል ደስታ ድሩን ሰርቷል።
ሁሌም ደስተኛ ነች የምትባል ሴት ብትሆንም፤ የዛሬው ግን የተለየ ነው፤ የደበዘዘ ሮዝ ቀለም የተቀባውን ከንፈሯን ከፈት እያደረገች፤ሀፍረት የቀላቀለ ፈገግታ ትጋብዘናለች።

ፀጉሯ ላይ የሚያንፀባርቅ ነገር ይታያል፤ አክሊል ካናቴራ ነው፤ ሄዶባታል አጥገልፀውም ምክንያቱም... የምር ንግስት የሚያስመስል ግርማ ሞገስ አላት።

በቀኝ እጅዋ እንደሷ የፈኩ ነጫጭ አበቦችን፤በግራ እጅዋ ደሞ የመጪው ባሏን ክንድ ቆልፋ ይዛለች፤ በኤሊ እርምጃ ወደ አዳራሹ በማዝገም ላይ ናቸው፤ ብዙዎች ከሁዋላ ሀይሎጋ እየጨፈሩ ያጅቧቸዋል።

እኔ እና አጎቴ(የሙሽራዋ  አባት) አዳራሹ መግቢያ ላይ ተሰይመናል፤ በትንሹ እያጨበጨብን፤ በፍቅር አይን ሙሽሮቹን እናያቸዋለን።

ሁለታችንም ተመሳሳይ ሱፍ ነው የለበስነው፤ እንደወጣትነቴም፤ እንደ ቁመና ባለቤትነቴም፤ እኔ ላይ ይበልጥ ሳያምርብኝ አይቀርም።
በቃ ተውኩት፤ 'ስለ ራስ አይወራም!' ያለኝ ማን ነበር?...ብቻ ማንም ይሁን ማን ልክ ሳይሆን አይቀርም።

በአሁኑ ሰአት ግን ሙሽሮቹን ማጀብ ሲገባኝ፤ እዚ ፈዝዤ የቆምኩበት ምክንያት አልገባኝም፤ በርግጥ ሜሪ ቀድማኝ በማግባቷ ትንሽ ደብሮኝ ነበር፤
«አትቀድመኝም!»
«አትቀድሚኝም!» የሚል የፌዝ ውርርድ ስለነበረን፤ በመሸነፌ ትንሽ ቅር ብሎኛል። ግን የሷ ደስታ ደስታዬ አይደለም እንዴ?...ይሄን ያክል ፋራ ሆኛለሁ?...ሳምንቱን ሙሉ ጠብ እርገፍ ስል የነበር፤ ዛሬ እንዲ ለመሆን ነው?
ራሴን ተቆጣሁት፤ደሞስ የሷ ሰርግ ያልጨፈርኩ የማን ልጨፍር ነው?

ከሰመመኑ እንደ ነቃ ሰው ደንገጥ አልኩና ፤ወደ አጃቢዋች ሄጄ ተቀላቀልኩኣቸው። ሜሪ አስተውላኝ ነበር፤ ዲምፕሎቿን አስከትላ  ፈገግ አለችልኝ። ደስ ስላላት፤ ደስ አለኝ። ድምፄን አጠብድዬ እኔ እመራቸው ጀመር፤ የጭፈራውውን ዙር አከረርኩት...።

* * *

ልጅ እያለሁ ነው ፤ ወደ አስራዎቹ መግቢያ ላይ። ከእናቴጋ ለመጀመሪያ ጊዜ መነሀሪያ ሄድኩ፤ ተገድጄ ነው እንጂ፤ የመምጣቱ ፍላጎት አልነበረኝም። ቆይቶ ግን አብዛኛውን የማየው ነገር አዲስ ስለሆነብኝ፤በሆድ ማማረሬን አቆምኩ።

ገና ከመግባታችን አንድ ሱቅ በደረቴ አዟሪ ልጅ መጥቶ እናቴን ይለማመጣት ጀመር፤
«እናት ሶፍት ይፈልጋሉ?..ማስቲካም አለ ጦር..ባናና..» ምንም እንደማትፈልግ ከይቅርታ ጋር ነግራው፤ መቀመጫ ወዳለበት ሄደን ተቀመጥን። ሲመስለኝ የምንቀበለው ሰውዬ ገና አልደረሰም።

ከጥቂት ደቂቃዎች በሁዋላ፤ እናቴ ሁለት ባሶች ተከታትለው መግባታቸውን አስተውላ፤ ባለሁበት እንድጠብቃት አስጠንቅቃኝ ሄደች።

የግቢው(የመነሃሪያው) ስፋትና የመኪኖቹ ብዛት አስገርሞኝ፤ አይኔን ወዲያና ወዲ እያቅበዘበዝኩ ትንሽ እንደቆየሁ፤ ውሃ ሰማያዊ ቀሚስ ያደረገች ሴት ወደ እኔ አቅጣጫ ስትመጣ ተመለከትኩ። ይሄኔ ነው እንግዲህ ጉዴ የሚጀምር።

እድሜዋ ከኔ ጋ ተመጣጣኝ ይሆናል፤ አልያ ደሞ በትንሽ ትበልጠኛለች። ከሩቅ እንዳየኋት ቆንጆ መስላኝ ነበር፤ እየቀረበች ስትመጣ ግን እጅግ በጣም ቆንጆ ሆነችብኝ። ከላይ እስከ ታች ባይኔ አላመጥኩኣት፤ ስጋ እንዳየ ውሻ ምላሴን አውጥቼ ለሀጬን ማዝረክረክ ነው የቀረኝ።

አፌን እንደከፈትኩ እርምጃዋን ስቆጥር ከአይኗጋ ገጠምኩኝ፤ በጣም ማፍጠጤ ታወቀኝና አይኔን ሰበርኩ፤ ዝቅ አልኩ።

ወዲያው የየሆነ ሰው ጥላ እየቀረበኝ መጥቶ ካጠገቤ ሲቀመጥ ተሰማኝ። እሷ መሆኗን ላረጋግጥ ቀና ስል፤ በድጋሚ ካይኖቿጋ ተጋጨሁ፤ እዛው ስብር። ሆ! በምን ሃቅሜ፤ ልቋቋማቸው?

ልቤ በፍጥነት እየመታ ነው፤ ሰውነቴም በላብ ተጠምቋል፤ ወደሷ መዞር አቃተኝ፤ የተሸከምኩኣት ያክል ከብዳኛለች።
በእርግጥ በጣም የተቀራረብን መስሎ ተሰማኝ እንጂ በመሀከላችን ያለው ርቀት አምስት ሰው ያስቀምጥ ነበር።

ከትንሽ መንቀጥቀጦች በኋላ አላስችለኝ ሲል፤ እንደምንም ሰረቅ አድርጌ አየሁአት፤ 'ተመስገን'! አልኩ ከአይኖቿ ጋ ስላልተጋጨሁ መሆኑ ነው ሂሂሂ!!።

እንደዚህ አይቼ የደነገጥኩላቸው ሴቶች ጥቂት ነበሩ፤ ግን አንዳቸውንም አውርቼአቸው አላውቅም። ይህቺን ልዕልት መሳይ ግን ዝም ብሎ ያልፋት ዘንድ ልቤ አልቻለም፤ ውስጤ 'አናግራት!..አናግራት!' በሚል የድምፅ ማእበል ተናወጠ።

እሷን የማናገር ፍላጎቴ ናረብኝ፤ ከዚህ የፍርሀት አዘቅት ወጥቼ እንዴት እንደማወራት ግራ ቢገባኝም፤ ውሳኔ ላይ ደረስኩ።

ቀረብ ብዬ ልተዋወቃት፤ የተሰማኝን ሙሉውን ባልነግራትም፤ የመጣልኝን ብዬ ከበኋላ የህሊና ፀፀቴ ለመዳን ወሰንኩ። ራሴን በራሴ motivate ማድረግ ጀመርኩ፤ እንደሚችል ነገርኩት፤ ተቀበለኝ (ማለቴ ተቀበልኩት)።

መመለሷን ስጠብቅ የነበረውን እናቴን ከነ እንግዳው በዛው እንዲቀሩ እየተመኘሁ ፤እግሬን አዘጋጀሁ፤ ጉሮሮዬን ጠረኩ፤ ልብሴን አስተካከልኩ በስተመጨረሻ ብድግ ስል፤ እናቴ ሻንጣ እየጎተተች ካንድ ሰውዬጋ ወደ እኔ ስትመጣ አየኋት።

በእውነቱ ያን ጊዜ የተሰማኝን የመንፈስ ስብራት ልገልፅላችሁ አልችልም። ክው ነው ያልኩት፤ እዛው በቆምኩበት ክርር፤ ድርቅ፤ ዝም፤ ምንም። እንባዬን እየታገልኩ መለስኩት፤ ዋጥ!።

ደረሱ። እናቴ አጎትህ ነው ብላኝ ከሰውየውጋ አስተቃቀፈችኝ።
ሰላም ብዬው አብቅቼ ዞር ስል፤
« አልተዋወቃችሁም እንዴ? » እናቴ ነበረች።

« ከማንጋ? » መቼም አጎትየውን እንደማይሆን አውቄ ጠየኳት።

« ከ ሷ'ጋ ነዋ! » ጎኔ ተቀምጣ ስታስጨልለኝ ወደነበረችው እንስት በግንጭሏ እየጠቆመች። ይሄኔ ነበር ከቅድሙ በበለጠ በላብ የተዘፈቅሁት። ጉልበቴ ይርበተበት፤ ሰውነቴ ይንቀጠቀጥ ጀመር፤
እንዴት የልቤን አወቀችብኝ?

ግራ ግብት አለኝ። የምለው ባጣ፤ አናቴን በአሉታ ግራ ቀኝ ወዘወዝኩላት «በፍፁም!» እንደማለት። ወዲያው ልጅቱን እጅዋን ይዛ አስነሳቻትና..
« እስከዛ ተዋወቂው ብለን ነበርኮ ወዳንተ የላክናት... ለማንኛውም ያጎትህ የሙሌ ልጁ ነች...በሉ ሰላም ተባባሉ »

ፈዘዝኩ፤ ህልም ህልም መሰለኝ፤ ስሜቴ ድብልቅልቅ አለ፤ ልደሰት ወይስ ልዘን?

እጇን ዘረጋችልኝ፤ ከበድን አካሌ በድን እጄን ልኬ ጨበጥኩዋት፤ እጇ ይለሰልሳል፤
« ሜሪ እባላለሁ! » ፈገግ ብላ ስሟን አከለችልኝ፤ ፈገግ ስትል ጉንጮቿ ሰርጎድ አሉ። ደስ የምትል ልጅ ደስ የሚል ስም አላት።
እኔ ግን ስሜን የምናገርበት አቅም አጣሁ፤ ምላሴ ተሳስሯል፤ አንደበቴ ተዘግቷል፤ ዝም አልኩኝ ፤ ዝም።

ምናልባት ብዬ ከህልሜ እስኪያባንነኝ፤ ሳምንታትን ጠበቅሁ...ልነቃ ግን አልቻልኩም...እውን ነበር።



By BINIAM EJIGU

@wegoch
@wegoch
@wegoch
በእድሜ የገፉ አዛውንት ባልና ሚስት በወጣትነት ዘመናቸው ያሳለፉትን የፍቅር ግዜያት ለማስታወስ ይፈልጉና ባልየው
" ነስሩ ሱቅ አጠገብ ያለው ጎረምሶቹ የሚቀመጡበት ድንጋይ ላይ ቁጭ ብዬ እጠብቅሻለሁ ... አንቺም ተሽሞንሙነሽ በአጠገቤ ስታልፊ ለክፌ አስቆምሽና እጅሽን ይዤ እያሽኮረመምኩ አዋራሻለሁ " ይላታል ሚስትም በደስታ ተውጣ ትስማማለች ።
.
ባል ድድ ማስጫው ላይ ለሁለት ሰዓታት ተቀምጦ ቢጠብቅም ሚስት የውሃ ሽታ ትሆናለች ። ይሄኔ " ምን አጋጥሟት ይሆን ?" በማለት ወደ ቤቱ ያዘግማል....
ቤቱ ሲደርስም ያልጠበቀውን ነገር ተመለከተ ሚስት አቀርቅራ ትንሰቀሰቃለች፣
ጠጋ ብሎ ምን እንደሆነች ሲጠይቃት
" እናቴ ከቤት መውጣት ከለከለችኝ "😂

@wegoch
@wegoch
@paappii

By lulit Tadesse
በነገራቹ ላይ መልክ ብቻ ሳይሆን ድምፅም ስታድጉ ይለወጣል:: እኔና ወንድሜ ድምፃችን አንድ አይነት ነበር::

ክፍለሃገር ለዘመድ ጥየቃ የሄደው አባቴ : በጠዋት በቤት ስልክ ደውሎ አነሳሁ:: (እስካሁን በህይወቴ ከነበሩ ትዛዞች ዝንፍ ሳልል ያከበርኩት ስልክ ሚነሳው 3ጊዜ ሲጠራ ነው ሚለውን ብቻ ይመስለኛል)😂😂😂

ከዛ አባቴ ሄሎ ስል የወንድሜ ስም ጠራ:: ልክ ወንድሜን እንደሚያዋራ: ደህና ነህ ምናምን አለኝና.... እናቴ እንደሌለች ጠይቆኝ ስነግረው.....የአንድ ዘመዳችንን ስም ጠርቶ አባቱ እንደሞቱ እና እሱ ቅዳሜ ስለሚመለስ እሁድ መርዶ ስለሚነገረው እንድትዘጋጅ እንድነግራትና ለማንም እንዳልናገር አስጠንቅቆ ነገረኝ::

ስልኩን እንደዘጋው እኛ ሰፈር አካባቢ ካለ ጋራዥ የሚሰራው አባቱ የሞቱበት ልጅ ጋ ሄድኩና... አባቱ እንደሞቱ እና እሁድ ሊነግሩት እንደሆነ ነገርኩት:: ልጁ ተንፈራፈረ :አለቀሰ ምናምን:: እናቴ የግድያ ሙከራ ስታደርግብኝ.... አያቶች ከለላ ሰጥተውኝ እዛ ተወሰድኩ::

እሁድ ለታ...አባባ ሲመጣ ወንድሜን ካልገደልኩ አለ.... ወንድሜ ምንም እንዳላደረገ : በስልክ እንዳላወሩ እየደጋገመ እየማለ ይናገራል::

አባቴ ወንድሜን እየተማታ "ጭራሽ ውሸትም ጀምረህልኛል?.... የሷን እና ያንተን ድምፅ መለየት ያቅተኛል? አንተም አድገህ ልትሸውደኝ? ....."
"ሂጂ ንገሪ ብለሃት እንጂ....." አባቴ ጥፍጥፍ አደረገው::

አባቴ በሌለበት ምግቤን ይቀማኝና: ይመታኝ ስለነበር ደስስስ አለኝ::

By ma hi

@wegoch
@wegoch
@paappii
Radric Davis ( ጉቺ ሜን ) አሜሪካዊ ራፐር ነው ። ከጎኑ ያለችው ደሞ Keyshia Ka'Oir ትባላለች ፡ ሞዴሊስት ፡ ጎበዝ አክትረስና ፡ ኢንተርፕረነር ነች ።

እና ፡ ከአመታት በፊት ፍቅረኛዋ ጉቺ ሜን ፡ በአንድ ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀረበና ፡ የሶስት አመት እስር ተፈረደበት ።
.....
ጉቺ ሜን ፡ ይህን የዳኞቹን ውሳኔ እንደሰማም ፡ ፍቅረኛውን ኬይሽያን ፡ ወደ እስር ቤት እንድትመጣ ላከባት ።
....
እየውልሽ ፡ በእስር ቤት ቆይታ ምን እንደሚፈጠር አላውቅም ። ስለዚህ በስሜ ያለውን ሁለት ሚሊየን ዶላር ፡ ወደ አንቺ ባንክ እንዲዛወር እፈልጋለሁ አላት ።
...
እና በባንክ ያለውን ብር በሙሉ ለፍቅረኛው ኬይሽያ ሰጣት ።
ጓደኞቹ ቀለዱበት ። ታስረህ ስትፈታ ጎዳና ልትወድቅ ነው ? ይህን ሁሉ አመት ትጠብቀኛለች ብለህ አታስብ አሉት ።
.....
Keyshia Ka'Oir ፍቅረኛዋ የሰጣትን ገንዘብ ከባንክ ያወጣችው ብዙም ሳይቆይ ነበር ። እናም በገንዘቡ የራሷን Ka'Oir የሚባል የኮስሞቲክስ ማምረቻ ከፍታ መንቀሳቀስ ጀመረች ።
....
ጊዜው ሳይታወቅ ሄዶ ፡ ፍርደኛው ራፐር ጉቺ ሜን የእስር ጊዜውን ጨርሶ ወጣ ። ጓደኛው ኬይሺያ ፡ በስራ ምክንያት ቢዚ ብትሆንም ፡ አልፎ አልፎ እየመጣች ትጠይቀው ነበር ። እና እንደተፈታ በዘመናዊ መኪና መጥታ ፡ ወደ አዲስ ቤት ይዛው ሄደች ። ከዚህ ሁሉ አመት መለያየት በኋላ ትጠብቀኛለች ብሎ ባያስብም ፡ እሷ ግን ከአመታት በኋላም ሳትቀየር ነበር ያገኛት ።

እና ቤት ደርሰው አረፍ ካሉ በኋላ ፡
" ጉቺ እስር ቤት ስትገባ ፡ በወቅቱ ሚስትህ ሳልሆን ፡ ትክደኛለች ሳትል ፡ ሁለት ሚሊየን ዶላር ሰጠኸኝ ነበር አይደል የገባኸው ? " አለችው ።
አዎ አላት ።
ይኸው ስድስት ሚሊየን ዶላር ሆኖ ጠብቆሀል አለችና ፡ የባንክ ቡኳን እንዲያየው ሰጠችው ።
.....
ዛሬ ላይ ፡ ጉቺ ሜን ፡ ከዛች ፍቅሩን ብቻ ሳይሆን የሰጣትንም ገንዘብ በእጥፍ አሳድጋ ከጠበቀችው Keyshia Ka'Oir ፡ ጋር ተጋብተው ፡ ትዳራቸው በልጅ ደምቆ , አብረው ይኖራሉ ።
.....
መታመን !

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Wasihun Tesfaye
አንድ - ፩

ሶስት ግዜ  ነው በጣም የፈራሁት ።

ጎበዝ ተማሪ ነበርኩ ።አምቦ  university economics   ነበር የምማረው አያይ  አሞታል ና አለቺኝ ታላቅ እህቴ ። አያይ ልጆቹ ያወጣንለት የአባቴ ስም ነው ።

ቅዳሜ ነበር አራት ሰአት አካባቢ  ቁምጣ እና ቲሸርት አድርጌ ደራራ ሆቴል ጋ ነበርኩ የህቴ ድምፅ ጥሩ ስላልነበር አብራኝ ከነበረችው ቤዛ ሁለት መቶ ብር ተቀብዬ ግቢ ሳልገባ በዛው ቤት ሄድኩ

አባቴ ሞቶ ነበር ። ከመሰላል ላይ ወድቆ ግማሽ ቀን ታሞ ነው የሞተው አሉ ።ስምህን ሲጠራ ነበር አሉ ። ይበርታልኝ አለ አሉ ። ምንም ሳላደርግለት አለ አሉ ።እሱ የኔ ነገር አይሆንለትም አለ አሉ .... ብዙ ነገር አለ አሉ

ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ እንኳን ይፈልገኛል ። ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ያላረገልኝ ነገር ነው የሚቆጨው፣ ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ እንዳልሰንፍ ያሳስበዋል ፣ ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ እንደምወደው ያውቃል ፣ ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ይጠራኛል ።

እውነት እንዳይሆን ፈለኩ ከቅዠት እንድነቃ ከዚ ቀደም ሲናፍቀኝ ሞቶ አይቼ ስባንን ውሸት ሆኖ ሲለሚያቅ እንደዛ ፈለኩ አልሆነልኝም ።

አንገቴን እንደደፋው እንዳላዛር ከሞት አስነሳልኝ አልኩት እግዜርን። እግዚአብሔርም ምላሽ አልሰጠኝም ።

ከሶስት ቀን በኃላ የአባቴ ገላ የሚመስለኝን ኮት ለብሼ ካምፓስ ተመለስኩ ። 

ማታ ማታ ሁሌ እፈራ ነበር ። አባቴን ሳስበው ልቤ በሃይል ይመታል ። ኮቱን ሳልቀይርለት ጠጅ ሳልጋብዘው የተሸከመኝን ኢምንት  ሳልሸከመው አይነት ድብርት  ።  አለመኖሩን የማመን ፍርሃት ተጫወተብኝ ።
   
By Adhanom Mitiku

@wegoch
@wegoch
@paappii
ወደ ስራ ስሄድ አንድ የስልክ እንጨት ላይ የተለጠፈ ወረቀት አየሁኝ: ጽሁፉ እንዲህ ይላል

“እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር ጠፍቶብኛል: ያገኘ ሰው ካለ እባካችህን አድራሻዬ በሚቀጥለው መንገድ በቀኝ በኩል ስትታጠፉ ያለው አሮጌ ቤት ነው:: አይኔ እንደፈለግኩኝ አያይም: እድሜዬም ገፍቷል: ልጆችም የሉኝም"

ይህንኑ ጽሁፍ ተከትዬ ወደ አሮጌው ቤት ስሄድ አንዲት ሴትዮ ደጃፍ ላይ ተቀምጠዋል: የእግር ኮቴየን ሰምተው "ማነው? ማን ልበል?" አሉኝ

"እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነው: እሱን ልሰጥ ነው የመጣሁት" ብዬ መለኩላቸው

አሮጊቷ እንባ ቀደማቸው - "ልጄ! እስካሁን ድረስ ከ40 በላይ ሰዎች 50 ብር መንገድ ላይ ወድቆ አገኘን ብለውኝ መጥተዋል"

ቀጠሉ አሮጊቷ - "እኔ ይህንን ጽሁፍ አልጻፍኩኝም: ጽሁፍ ለመጻፍም ሆነ ለማንበብም አይኔ እሺ አይለኝም"

50 ብሩን በእጃቸው አስጨበጥኳቸው

ጽሁፉን ከስልክ እንጨቱ ላይ እንድቀደው ቢነግሩኝም አላደረግኩም: የመጣውን ሰው ሁሉ ይህንኑ ነበር የሚሉት

ይህንን ጽሁፍ የጻፈውን ሰው እንዴት እንዳደነቅኩት : እኚህን ሴትዮ ለመርዳት የሄደበት ርቀት በጣም ነው ያደነቅኩት

ከሴትዮዋ ቤት ስወጣ አንዲት ወጣት ልጅ አስቆመቺኝ

"ወንድሜ! እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነበር: የቤቱ አቅጣጫ በየት በኩል እንደሆነ ታውቃለህ እንዴ?"

በልቤ እየሳቅኩኝ ቤቱን ጠቆምኳት


ሰው መሆኛ መንገዱ ብዙ ነው


By zemelak endrias

@wegoch
@wegoch
@paappii
አንድ ወጣትና ሽማግሌ አይሁድ በባቡር ይጓዛሉ።

ወ፤ ስንት ሰዓት ነው?
ሽ፤ ዝም።
ወ፤ ይቅርታ ጌታዬ፣ ስንት ሰዓት ነው?
ሽ፤ ጭጭ።
ወ፤ ይቅርታ ጌታዬ እያናገርኩዎትኮ ነው፣ ለምንድነው የማይመልሱልኝ!! ስንት ሰዓት ሆኗል?
ሽ፤ ስማ አንት ጉብል። የሚቀጥለው ፌርማታ በዚህ መስመር የመጨረሻው ነው። አታውቀኝም አላውቅህም። ለሀገሩ እንግዳ ለሰዉ ባዳ ትመስላለህ። ለጥያቄህ መልስ ከሰጠሁ፣ ጨዋታ ልንጀምርና በዚያው ልንግባባ ነው። ስንወርድ "ወደቤት ጎራ በል" ማለቴ አይቀርም። እንደማይህ መልከመልካም ነህ፤ እኔ ደግሞ ቆንጆ ልጃገረድ ልጅ አለችኝ። ኋላ ፍቅር ውስጥ ትገቡና የመጋባት ፍላጎት ያድርባችኋል። እስቲ አንድ ነገር ንገረኝ፤ ምን ቆርጦኝ ነው የእጅ ሰዓት እንኳን መግዛት ለማይችል ሞሳ ልጄን የምድረው😊

By mengedenga

@wegoch
@wegoch
@paappii
ምን ጊዜም ከልክ ያለፈ ጨዋነት ጀርባ የሆነች እየተካሄደች ያለች ጨዋታ አለች ብለን እንጠርጥር እንዴ !?
.
አያቴ እንዲህ ይል ነበር "ስቲንጃ ሲበዛ ትርፉ መነጀስ !" ነው።
የሆነ ግዜ እንዲህ ሆነ ባል ስራ ውሎ ወደ ቤቱ ሲመለስ ሚስቱ ስታለቅስ ያገኛታል። ይሄኔ ይደነግጥና ለምን እንደምታለቅስ ይጠይቃታል።

እሷም "እዚህ ዛፍ ላይ ያለው አሞራ ያለ ሂጃብ ሆኜ ሲያየኝ ጊዜ ወንጅል ሆኖ ታየኝ። ለዛ ነው ማለቅሰው..." ስትል ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች መለሰችለት።

ባልም በዚህ ቁጥብነቷ ተደስቶ እቅፍ አደረጋትና ግንባሯን
ሳማት። ወዲያውም መፍለጫ ይዞ ወጣ'ና አሞራው ሚያርፍበትን ዛፍ እንዳልነበረ አድርጎ ቆረጠው !

እናላችሁ ከዕለታት አንድ ቀን ባል ስራ በግዜ ጨርሶ ቤት ከች ሲል....
ያችን ቁጥቧን ሚስቱን ፣ ያችን አሞራ አየኝ ብላ ቂያማ
ምታቆመውን ሚስቱን ከውሽማዋ ጋር
ተኝታ ያገኛታል።

ምንም አላደረገም ትቶ ወጣ። ወደ ሩቅ ሀገርም ሄደ።
እና የሆነ ከተማ ሲገባ በጣም ብዙ ሰዎች ቤተ መንግስት በር ላይ ተሰብስበው ያገኛቸው'ና ለምን እንደተሰበሰቡ ይጠይቃቸዋል።

ሰዎቹም "የንጉሱ ወርቅ ማስቀመጫ ተዘርፎ ነው" ሲሉ ይመልሱለታል።
በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ የሆነ ሰውዬ ጤነኛ ሆኖ
በእንብርክኩ ሲንፏቀቅ ያየው'ና....
"ይህ ሰው ለምን ቆሞ አይራመድም?" ብሎ ይጠይቃቸዋል።
እነሱም "አይ ይህማ የከተማችን ትልቅ ሸይኽ ነው ! .. በእግሩ ማይራመደው ምናልባት ሳያውቅ በእግሩ ጉንዳን እንዳይገድል ሰግቶ ነው" ብለው ይመልሱልታል።

አአአዎ በቃ እዝች'ጋ ተነቃቁ.....

ሰውየውም በፍጥነት "ወላሂ ሌባውን አገኘውት...."ብሎ ጮኸ።
ንጉሱም ጋር በፍጥበት ገባ'ና "ያኛው ሸይኽ ተብዬ ነው
ንብረትህን የሰረቀህ ከፈለግክ አስፈትሸው'ና ውሸቴን ከሆነ አንገቴን ቁረጠው...." አለ።

ወታደሮችም በንጉሱ ትዕዛዝ ሸይኽ ተብዬውን ፈትሸው የተሰረቀውን የወርቅ ማስቀመጫ ተቀምጦበት አገኙት። ሁሉም ተገረሙ ፣ ደነገጡ።
ንጉሱም ለሰውዬው "እንዴት እሱ እንደሰረቀ ልታውቅ ቻልክ?" አለው ግራ በመጋባት። ሰውዬውም ሚስቱን እያስታወሰ "ቁጥብነት እና መልካምነትን እንዲህ {ድንበር
ባለፈ ሁኔታ} ስታገኘው
ከጀርባው ትልቅ ክህደት እንዳለ ያመላክታል" ብሎ መለሰለት ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

By mustejan
ሶስት ሆነን አንድ ሪል ስቴት ውስጥ እንኖር ነበር:: ከእረፍት ቀናቶች ውጪ ማታ ገብተን ጠዋት የምንወጣ አይነት ሰዎች ነበርን:: ከኮሚቴው በስተቀር ግቢው ውስጥ ከሚኖረው ማህበረሰብ ጋር ከሰላምታ የዘለለ እምብዛም ንግግር የለንም

የሆነ ጊዜ ላይ ለሶስት ሳምንታት ያህል ለስራ ጉዳይ ወደ ክፍለ ሀገር ወጥተን ቆይተን ስንመለስ ከአንዱ ህንጻ አራተኛ ፎቅ ላይ የአንዲት አሮጊት ድምጽ ሰማን

👇🏾

"ልጆች! አይቻችሁ አላውቅም የት ጠፍታችሁ ነው?" ድርብብ ያሉ ሴት ናቸው

"ለስራ ጉዳይ ወደ ክፍለ ሀገር ወጥተን ነበር እማማ"

"እኔማ ጊዜው ክፉ ስለሆነ እና የሚሰማው ሁሉ ስለሚያስፈራ ልጆቼ ምን ሆነው ጠፉ ስል ነበር"

ደነገጥን

"ልጆቼ?"🤔

"እሺ እማማ አንጠፋም"

ጏደኛዬ ጣልቃ ገባ

"እማማ ምናልባት ተሳስተው እንዳይሆን: አውቀውናል ግን ማን እንደሆንን?"

"ልጄ አውቂያቸዋለሁኝ: ከሱቁ ቀጥሎ ያለው ብሎክ ላይ ስትገቡ ስትወጡ እዚህ በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ ትታዩኛላችሁ"

ተገረምን

"ነጭ መኪና የምትይዘው አንተ አይደለህም እንዴ?"

"አዎን እኔ ነኝ እማማ"

"አንደኛው ጠቆር የሚለው ጏደኛችሁ ልጄን ያስታውሰኛል: ቦቸራ ልጄ እንደ እሱ ወፍራም ቦጅቧጃ ግን ደግሞ የዋህ ልጄ ነበር: መኪና ቀጠፈብኝ እንጂ" ብለው ተከዙ

ዝም አልን !

"በሉ ሂዱ አላቆያችሁ! ሁሌም እፀልይላችኃለሁ"

"ይፀልዩልናል እማማ?"

"አዎን ልጆቼ: ለሁሉም እፀልያለሁኝ ለእናንተም ጭምር"

*

ምሽት ላይ ወደ ሰፈር ስንመጣ ነጠላ: ጥሬ ቡና: እጃቸውን የሚያፍታቱበት እንዝርት እና ጥጥ: የፀጉር ቅባት: ሻሽ እና አንዳንድ ነገሮች ይዘንላቸው መጣን



በስውር ለሚከታተሉን አይኖች እና በቅንነት ለሚፀልዩልን ልቦች ሁሉ - ሰላም ለእናንተ ይሁን❤️

@getem
@getem
@paappii

By Zemelak endrias
መምህርት ሊያ የ5ኛ ክፍል አስተማሪ ነች

ሊያ ተማሪዎቿን አንድ በአንድ የምትከታተል ብርቱ መምህር ነች

ከተማሪዎቿ አንዱ ኒክ ይባላል
ኒክ አያወራም: ከተማሪዎች ጋር አይጫወትም: ልብሱ ዝብርቅርቅ ያለ ነው: ክፍል ውስጥ አይሳተፍም - መምህር ሊያ በኒክ ደስተኛ አይደለችም

መምህር ሊያ የተማሪዎችን የቤት ስራ እና ፈተና ባረመች ጊዜ ሁሉ የኒክን ፈተና በትልቁ ኤክስ (X) የምታደርግ እና በብስጭት ስንፍናውን የምትፅፍ ሆነች - አልወደደችውም



በትምህርት ቤቱ ህግ ደግሞ የእያንዳንዱን ተማሪ የቀድሞ አመታት የውጤት ፋይሎችን ማየት ግዴታ ስለሆነ መምህርት ሊያም ይህንኑ ስታደርግ የሁሉንም ፋይል አይታ የኒክ መጨረሻ ላይ ቀረ

አነበበችው : ተገረመች : ደነገጠች !

****

የአንደኛ ክፍል መምህሩ "ኒክ በጣም ጎበዝ ተማሪ ነው! ፀባዩም ሸጋ ነው: ንፁህ እና ብሩህ ተማሪ ነው"

የሁለተኛ ክፍል መምህሩ "ኒክ ጎበዝ ተማሪ ነው: ነገር ግን በዚህ አመት እናቱ በጠና ስለታመመች በውጤቱ ቀንሷል"

የሶስተኛ ክፍል መምህሩ "ኒክ በእናቱ ሞት ተጎድቷል: አባቱም በሀዘን ተጎድቶ ትኩረት የሚሰጠው ሰው የለም"

የአራተኛ ክፍል መምህሩ "አባቱን በሞት የተነጠቀው ኒክ በዚህ አመት ብሶበታል: ብቸኛ ነው: ከማንም ጋር አያወራም: ውጤቱም ወርዷል"

***

እለቱ የገና ዋዜማ ነው: ተማሪዎች ለመህራኖቻቸው ስጦታ የሚሰጡበት እለት ነው - ሁሉም ተማሪዎች ለመምህርት ሊያ የሚያምሩ ስጦታዎችን እየሰጡ ነበር

ኒክ በስተመጨረሻ መጣ - በእጁ ጌጣቸው የረገፈ አምባር እና ሊያልቅ ቂጡ ላይ የደረሰ ሽቶ ይዟል: የእናቱ የእጅ አምባር እና ሽቶ ነበር - ተማሪዎች ይህንን አይተው ሳቁ : መምህሯ ግን ተማሪዎቹን ፀጥ አሰኝታ አምባሩን አጠለቀችው : ሽቶውን ተቀባች : ኒክን አቀፈችው

"ዛሬ እናቴን ትመስያለሽ : እናቴን እናቴን ትሸቻለሽ" አላት :

ተማሪዎች ከሄዱ በኃላ ለሰአታት ብቻዋን አለቀሰች

**

ከዚያ ጀምሮ መምህርት ሊያ ኒክን ተከታተለችው: ኒክ ጎበዘ: አመቱ መጨረሻ ላይ ጥሩ ውጤት አመጣ

በትምህርት ቤቱ ውስጥ "የመምህራን ምርጫ" ተብሎ ለመጠራት የበቃው ኒክ በትምህርቱ ጎበዝ: በፀባዩ ምስጉን እና በባህሪው ደግሞ ተግባቢ እና ደስተኛ ሆነ

ብዙ አመታት አለፉ: በእነዚህ አመታቶች ሁሉ በገና እለት ዋዜማ መምህርት ሊያ የቤቷ በራፍ ላይ "በህይወቴ ሁሌም ምርጧ አስተማሪ ነሽ! ኒክ" የሚል ፅሁፍ ታገኛለች

ኒክ ተመረቀ: ዶክተር ሆነ: በስራው የታወቀ ሀኪም ሆነ

ከእለታት በአንዱ ቀን "መምህርት ሆይ! ጥሩ እጮኛ አገኘሁኝ! እናት እና አባት እንደሌለኝ ታውቂያለሽ:: ስለዚህ የሰርጌ ቀን ከጎኔ ቁሚልኝ! ኒክ" የሚል ደብዳቤ ደረሳት

**

በሰርጉ ቀን የእናቱን አምባር አድርጋ እና ሽቶውን ተቀብታ ከጎኑ ቆመች : ዳረችው

በሰርጉ መሃል እጁን ይዛ ወደ አዳራሹ ሲገቡ

"መምህርት ሊያ ህይወቴን በተለየ መልኩ እንድረዳ እና እንድመለከት ስላደረግሽ አመሰግንሻለሁኝ" አላት

መምህርት ሊያ እንዲህ አለች

“ዶ/ር ኒክ! አንተ ነህ ሰዎችን እና ይህችን አለም የማይበትን መነጽር እንድቀይር ያደረግከኝ: አመሰግንሃለሁ!"❤️

@wegoch
@wegoch
@paappii
በተለያየ መንገድ ሲዘዋወሩ የሚያዙት የአደንዛዥ እፆች አወጋገድ ሁኔት ያሳስበናል ።

ባለፈው ፡ በኩንታል የሚቆጠር ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ እፅ ተይዞ ፡ ሜዳ ላይ ሲቃጠል አይተናል ። ይሄ ብዙ ኩንታል እፅ ሲቃጠል ስንቶች በጭሱ ሊጦዙ እንደሚችሉ ቤት ይቁጠረው ።
በተጨማሪም .... በአብዛኛው በውጭ ሀገር ዜጎች በኩል ሲገቡ የሚያዙት ሄሮይንን የመሳሰሉ እፆች ፡ ሲያዙ እንጂ በምን መልኩ እንደሚወገዱ ግልፅ አይደለም ።

እና. .. ይህ ነገር እስካልታወቀ ድረስ ፡ አንዳንድ አጓጉል ደንብና ህጎችን የሚያወጡ ሰወች ላይ መፍረድ ያስቸግራል ።

ለምሳሌ ፡ በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰአት ላይ ፡ የቤት መኪና እንዲቆም ይደረጋል ብለው ያሰቡት ሰወች ፡ ይህንን ነገር በደህነኛ አእምሮ ያሰቡት ነው ማለት አይቻልም ።
ሲጀመር አብዛኛው ሰው መኪና የሚገዛው የስራ ቦታ ለመሄድ ፡ ልጆቹን ትምህርት ቤት ለማድረስ ፡ እና ከስራ ወጥቶ ወደቤቱ ለመግባት ነው ። በአጠቃላይ 90% የቤት መኪና የሚገዛ ሰው ከስራ ጋር በተገናኘ መልኩ ይጠቅመኛል ብሎ ነው ።
....
አስቡት .... አደለም የቤት መኪና ተከልክሎ ፡ አሁን እንኳን በስራ መግቢያና መውጫ ሰአት ላይ. .. የትራንስፖርት ነገር የማይታሰብ ሆኗል ። እንግዲህ ይህ በሆነበት ሁኔታ ነው ፡ የቤት መኪና ለመከልከል ያሰቡት ።

ስለዚህ. . ይህን መሳይ አስቂኝና አስገራሚ ህግና ደንቦች ፡ በኖርማል አእምሮ ታስቦ የሚወጣ አይመስለንምና. .ይሄ የአደንዛዥ እፅ አወጋገድ ሁኔታ ይታሰብበት እንላለን ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

By wasihun tesfaye
Sister ነበር ያሳደገችኝ።

አራት ወይ አምስት አመት እያለሁ ነበር ወላጆቻችን ወደ ሞት የሄዱብን ። ሁለት ብቻ ነበር የወለዱት : እኔን እና እህቴን ። ስምንት አመት ትበልጠኝ ነበር ። መቼ ወደ አባትነት ፣ መቼ ወደ እናትነት እንደተቀየረች አላውቅም ።

ቤታችን ውስጥ አባትና እናት የሚወጣውን ሃላፊነት ተሸከመች ። ሸክሙ አላስጠናትም መሰለኝ ትምህርት አልገፋችም። አስረኛ ክፍል የሙያ ውጤት መቶላት ነበር፤ እሱንም ተወችው ።

አልምልም : ከማልኩ ኤልዱ ትሙት እላለሁ በቃ ። ምድር ላይ ሞት መጥቶ ቻው ማለት የምትፈልገው ሰው ብባል፣ ዘመድ ጥራ ብባል ፣ አንደኛ ማን ያስብልሃል ብባል ፣ የማን ወዝ እና ህልም አልፎብሃል ብባል መልሴ ኤልዳና የሚል ብቻ ነው ።

ተሰብስበን ህልም ስንናገር ኤልዳና ህልሟ እኔ ነበርኩ ። እንደዚህ ሰው ይወደዳል እንዴ? እንደዚህ በፍቃድ ህልም ይሰዋል ? የሆነ ቀን ከስራ ስመጣ ኤልዳ ታማ ጠበቀችኝ ። ክሊኒክ ወሰድኳት ቀላል አይደለም ብለው ሪፈር ላኩን ።

ፊቷ ችፍፍፍ ፣ ቁስልስል አለ ። ቀኝ እግሯ እምቢ አልራመድ አለ ፣ ምግብ አልበላ አላት ። ብዙ ቦታ ሄድን መፍትሄ አጣን ።

ኢ- አማኝ ነበርኩ ፤ እንዲ አደረክብኝ ብዬ የምጠይቀው ፣ እንዲ አድርግልኝ ብዬ የምለምነው አካል የለም ። ነፍስ ካወኩ እንዲ ሀዘን ተጣብቶኝ አያውቅም ። የመኖር ፍላጎት እና ህልሜ ከሰመ። ህመሟን አለምደው አልኩ ። ሃኪሞች ተስፋ የላችሁም አሉን ።

የሆነ ቀን አስራ አንድ ሰዓት ለሊት ቀስቅሳኝ
"በዓታ ማርያም ሶስት ቀን ፀበል ተጠመቂ ትድኛለሽ ተባልኩ" አለችኝ ። ማመን የማይደክማት ልጅ ፤ መሞኘት የማይሰለቻት ልጅ ።
"እሺ እንሂድ" አልኳት ።

አማራጭ የሌለው ሰው ምንም አይፈላሰፍም። እንኳን ቤተክርስቲያን ስምጥ ሸለቆ እሄዳለሁ ። በርግጥ እኔ ከ 'Bible' የ Sigmund Freud - ' The future of an illusion' የተሻለ ያሳምነኛል።

ግን፤ ኤልዱ እድናለሁ ካለች የት አልሄድም ??

ሄድኩ : ተጠበለች ወደቤት መጣን ። እሷ በህልሟ፣ እሷ በበኣታ ፣እሷ በፀበል ያላት እምነት ትልቅ ነበር እና ውጤት ጠበቀች በርግጥ እኔ የምጠብቀው ነገር የለም ።

በነጋታው ጠዋት ፊቷ ለውጥ ያለው መስሎኝ ነበር እሷ አረጋገጠችልኝ ። በሁለተኛው ቀን ሄድን "እግሬ ቀለለኝ" እያለች ነበር ። የዛ ቀን በነጋታው "እግሬ ሰራ " አለች ።

የሆነ ነገር ማለት ፈልጌ ነበር ደስታ፣ እምባ አላናግር አለኝ እና ዝም አልኩ። ሶስተኛ ቀን ተጠመቀች ፊቷ፣ እግሯ ፣የምግብ ፍላጎቷ እንደነበረ ሆነ ።

ሶስተኛ ቀን እሷ ተጠምቃ ስትጨርስ "ወደቤት እንሂድ ወይ?" አለችኝ።

"እኔ ልጠመቅ እና እንሄዳለን" አልኳት። ስትድን ደስ ያላትን ያህል ደስ አላት። ሆድ ብሶኝ ነበር ፣ደስ ብሎኝ ነበር ፣ ማመን አቅቶኝ ነበር። እያለቀስኩ እያመሰገንኩ እየተደሰትኩ ተጠመኩ አመንኩ ።

ሄሌ ሉያ

By Adhanom Mitiku

@getem
@getem
@paappii
ዘመኑ አልቋል እና ሌሎችም
(አሌክስ አብርሃም)

አብርሽ ወደኢትዮጵያ እንዳትሄድ! ፤አገሩ እንደድሮው እንዳይመስልህ ተበለሻሽቷል! አለችኝ ኢትዮጵያ ከርማ የመጣች ወዳጀ!

"እንዴት ማለት?" አልኩ ወዳዘጋጀሁት ሻንጣ በስጋት እያየሁ!

እየውልህ አንድ ቀን ለገሀር አካባቢ የሚገኝ ሆቴል ምሳ በልቸ ስወጣ የሆነ ጥቁር መነፀር ያደረገ ሰው በሞተር ሳይክል በሚያስፈራ ፍጥነት መጣብኝ ! አመጣጡ አስፈርቶኝ መንገድ ስቀይር ሌላ ባለሞተር ከፊት ለፊቴ መጣ ፣ ከረቫት እና ሙሉ ልብስ ለብሷል! የሆነ የውሃ መውረጃ ተሻግሬ ላመልጥ ስል ሌላ ሴት ልክ እንደሆሊውድ አክተር ፀጉሯን ነፋስ እየበታተነው እሷም ሞተር እያስጓራች መንገድ ዘግታብኝ ቆመች! ሶስቱም ከበውኝ ቆሙና ከሞተሮቻቸው ወርደው መነፅራቸውን አወለቁ! ሲጠጉኝ ቦርሳየን ከፍ አድርጌ "እባካችው አትጉዱኝ ፤ ይሄው ቦርሳየን ውሰዱ ስልኬንም ውሰዱ" አልኩ !

የመጀመሪያው ጠጋ አለኝና ከጀርባው የሆነ ነገር መዞ ሲያወጣ ጨላለመብኝ ! እሱ ግን "እህቴ እኔ ሌባ አይደለሁም ፤ጌታን እንደግል አዳኝሽ እንድትቀበይ ምድራዊ ቤትና ብር እንዳያታልልሽ የምስራች ልነግርሽ ነው የመጣሁት! ሞተር የምጠቀመው ዘመኑ ስላለቀ ለመፍጠን ነው ፤ ጌታ በደጅ ነው ጊዜ የለንም" አለኝ የመዘዘው የሚታደል ወረቀት ነበር!

ሁለተኛው ባለከረቫት ጠጋ ብሎኝ " የኔ እህት የባንካችን ደንበኛ እንድትሆኝ ነበር፤ ቡክ አውጥተሻል? ራምዛ ቃርዛ ፖርዛ ዳንሳ የሚባሉ አገልግሎቶች ለዲያስፖራዎች አሉን! ባንካችን በሚሰጠው ከ 10-20 ዓመት ዘና ብሎ የሚከፈል የረዢም ጊዜ ብድር በገዛሁት ሞተር ተጠቅሜ የመጣሁት ማየት ማመን ስለሆነ እድሉን እንድትጠቀሚ ነው " አለኝ!

ሶስተኛዋ ልጅ "አትደንግጭ የኔ ቆንጆ ! ሃያ ፐርሰንት ብቻ ቅድሚዬያ ቀሪው በ30 ዓመት የሚከፈል ፤ ለልጅ ልጅ የሚተርፍ እፎይ የምትይበት አፓርትመንት ባለቤት እንድትሆኝ ልነግርሽ ነው አመጣጤ!እኔ ራሱ መኪናየን ሸጨ ከፍየ በሞተር ነው የምንቀሳቀሰው መጀመሪያ መቀመጫየን ብሏል የአፍሪካ ህብረት ... ሪል ስቴት ኤጀንት ነኝ ! " ወዲያው ግራ ገብቶኝ ሳያቸው አንድ ፀጉሩ የተንጨበረረ ጥርሱ የበለዘ ወጣት ሳይክል እየነዳ ደረሰና " እስቲ አታጨናንቋት "ብሎ በታተናቸው ከዛ "እናት ምንዛሬ ከፈለግሽ አለ ! ስንት ይዘሻል? ነይ ላፈናጥሽ😀 አለኝ! ተበሳጭቸ ራይድ እንደተሳፈርኩ ሹፌሩ "ይሄ መንግስት ግን አይገርምሽም? " አለኝ! መልሴን ሳይጠብቅ "ለአምሳ አመት ኪራይ ወደብ ተከራየሁ ይላል እንዴ? "

@wegoch
@wegoch
@paappii
"ሴቶች በምንም አይማልሉም አትድከሙ!"
(አሌክስ አብርሃም)

በነገራችን ላይ እንደምታስቡት ሴት"መጀንጀን" ላይ አሪፍ አይደለሁም! ስለመጨረሻ ጅንጀናየ ላውጋችሁ! የሆነ ጊዜ አምስት መንገዶች አስር ማሳለጫዎች ምናምን የሚል የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ሴት ልጅ በራሱ የሚተማመን ወንዳወንድ ወንድ ትወዳለች የሚል ነገር ሰማሁ! እና አንዲት በዛ ሰሞን የወደድኳትን ልጅ ማማለል ፈለኩ! ተቀጣጥረን ተገናኘን ምሳ አብረን በላን (በድሮሮሮሮሮሮሮ ጊዜ የዛሬ ስድስት ዓመት ሰዎች ምሳ ይገባበዙ ነበር) እና ከመሬት ተነስቸ ጀብዱ ነገር ማውራት ጀመርኩ!

"ይገርምሻል የሆነ ጊዜ አንድ ዳይኖሰር የሚያክል በሬ ከቄራ አመለጠ ፤ እና ከቄራ ቡልጋሪያ ድረስ ሰባት ወንዶች ሶስት ሴቶች ሁለት መኪና በቀንዱ እየወጋ አተረማመሰው! ፖሊስ ሁሉ ማስቆም አልቻለም! እና እኔ ስደርስ ወደሆኑ አሮጊት ቀንዱን አሹሎ እየሮጠ ነበር ... በባልቴቷና በበሬው መካከል ሶስት የበሬ እርምጃ ሲቀር ተፈትልኬ ሮጥኩና መሀላቸው ገብቸ ስቆም ጫማየ እንደመኪና ጎማ ፉጭጭጭጭጭጭ አለ! በሬው ደንግጦ ቆመና ተፋጠን እንደቆምን በቀስታ ቀረብኩት .... በእግሩ አስፋልቱን እየቆፈረ ሊወጋኝ ሲሞክር ሸወድኩትና አንገቱ ላይ የታሰረውን ገመድ ቀጨም አድርጌ ለባለቤቱ አስረከብኩ! ይገርምሻል በተፈጥሮየ አልፈራም!

ልጅቱ ስትሰማኝ ቆየችና የበሬውን ነገር እንዳልሰማ ሰው " ዳይኖሰር ስትል አስታወስከኝ! ለምን ዛሬ ኤድናሞል ሙቪ አናይም? አሪፍ የዳይኖሰር ሙቪ አላቸው" ብላ በሚያማምሩ አይኖቿ አየችኝ! ጀብዱየን ውሃ ቸለሰችበት! ቅር እንዳለኝ ወደኤድናሞል የሚወስደን ታክሲ ስንጠብቅ አስገራሚ ነገር ተፈጠረ .... በሬ! የፈረጠጠ በሬ መንገዱን እያመሰው ከፊት ለፊታችን መጣ ... በእርግጥ ነፍሴን ለማትረፍ ባደረኩት ሩጫ ከበሬው የበለጠ ብዙ ሰው እየገፋሁ ሳልጥል አልቀረሁም! ልጅቱ ጋር በተፈጠረው ግር ግር እንደተጠፋፋን ከዛ በኋላ አልተገናኘንም! በእርግጥ ትዝ ያለችኝም የሆነ ካፌ ገብቸ ሁለት ሊትሩን ውሃ ከጠጣሁ በኋላ ነው!

@wegoch
@wegoch
@paappii
"የተኛህበትን ሳታመላክተኝ
ስታዞረኝ አደርክ ስታንከራትተኝ።"
.
.
.
ሄዷል። ድንገት። ድንገቴው ለኔ ነው። የት እንደሄደ፣ ለምን እንደሄደ ምኑም አልገባኝም። ሳይገባኝ ልፈልገው ጣርኩ። እየኖረ እንዴት ይሄዳል ሰው? መኖርም መሄድም እንዴት በኩል አፍታ ይገለጣሉ? ባንድ ሰውነት ላይ እኩል? ስሄድ ጭልጥ፣ ግንጥል ብሎ መሄድን፤ ስኖር ጥግት፣ ጥብቅ ብዬ መኖርን ነው የማውቅና ግራ ገባኝ።

አስራ አምስት አመታት የጎነጎነው በሱ በኩል ለቆት ኖሮ ያለመልኩ ብትንትን፣ ጭብርር፣ ስብርብር አለ። ልብና አይምሮዬ ላይ አለ እና ሄደ ተደራረበ። እንኖራለን እያልኩ መኖርን ስሸምን መለያዬት ተከናነብኩ። ደህና መሆኔን፣ ሰላሜን፣ ቀጥና ቀና ብዬ መራመዴን የሄደ ቀን ይዞት ሄደ። ቀነጣጥሶኝ። እኔ እኔን አልሰማ አለች። አይቻት የማላውቃት ሌላ ሴትዮ ተፈለቀቀች። ያለመድኳትን ሴት ተሸከምኩ። የጎበጠች፣ አንገቷን የደፋች፣ ሰው የፈራች፣ ችላ ብትጠጋም የማትላተም። መውደድ የሚያስበረግጋት። መጠጋት እንዳያፍነከንካት በዛው አፍታ የመለየት ሃሳብ የሚያስፈራት ፈሪ ተፈጠረች።

መሄዱን ሂድ ግን እኔን መልስልኝ አልኩት የሆነ ቀን ሳወራው። ሌላ አላለም፣ ሙቭ ኦን እናድርግ ለሁለታችንም እሱ ነው የሚሻለን አለኝ። ቀድሞኝ ትቶኝ ተሻግሯል አውቃለሁ። እኔ ግን ወዴት እንደምሻገር ማወቅ ተሳነኝ። ድልድዬን ሰብረኸዋልኮ ልለው ነበር ይከፋዋል ብዬ ዝም አልኩ።

"እህህ ጠዋት ማታ እህህ ሌሊት
ይሄ ሆኗል ትርፌ ካንተ ያገኘሁት"
.
.
.
ሁሉም ይሄዳልኮ። መሄድ ሰውኛ ነው ማንም የሚሄደው። ልንሄድ ነው የመጣነው። የሚለዬው አካሄዱ ነው። የሄደው ሰው ዓይነት ነው። የቀረብን፣ ያጣነው ነገር ነው። ለዛ ነው የከበደኝ። ለዛ ነው እንዳዲስ ጉዳይ እያደር መሄዱን የማያምን ልቤ። ለዚሁ ነው እረሳሁት ባልኩ ማግስት ከሲናፍቀኝ ስሜት ጋር ግብ ግብ ገጥሜ ከራሴ የምጣላ።

ስነቃ ከሄደበት አፍታ መገረምና አለማመን ጋር እነቃለሁ። እውነት ሄዷል? በእህህታ ሳብሰለስል እውልና እንቅልፍ ዓይኔን ከመክደኑ ፊት በህቅታ እንዲወጣልኝ ከእንባዬ ጋር እንዳንገዋለልኩት ሽፋሽፍቴ እንደራሰ እንቅልፍ ይጥለኛል። ስነቃም ሃሳቤ ውስጥ ይኖራል። እንዲያ ሆነ የኑሮዬ ድግግሞሹ። በሆነ ባልሆነው ተነጫነጭኩ። ራሴ ላይ፣ ሃሳቤ ላይ፣ እቅዴ ላይ፣ ህልሜ ላይ፣ ቁጭቴ ላይ፣ ትላንቴ ላይ፣ ዛሬዬ ላይ፣ ነገዬ ላይ፣ ህይወት ላይ፣ እግዜሩ ላይ።

ለምን እንደሄደ፣ ለምን እንደበቃሁት፣ ባይለውም ለምን እንደጠላኝ እንዲገባኝ ስዳክር ስድስት አመታት ተሻገርኩ ከህመሜ ጋር። እሱ እንዳለውም ተሻግሯል። አስራአምስት አመት የቆዬ አብሮነታችንን እንደዋዛ ጥሎ፣ ከራሱ ጋር ከነፍሱ ጋር ይደልቃል፣ በዝምታ።

በነዚህ ሁሉ ጊዜያት ለምን ግን እለዋለሁ እግዜሩን። በአካል የተገለጠ ሰው ሲያምረኝ። የሚያወራኝ፣ ምኑንም ምኑንም የሚቀባጥርልኝ። ያለመስመር፣ ያለመጠንቀቅ ሁሉን። ሳቅ የሚወልድልኝ። ወሬ አልቆብንም ዝም ብለን የምንቆይ። ዝምታችንም የሚያወራ። እንደገና የምንቀጥል። እሱን የሚያስረሳኝ። ሰው በሰው ነው የሚረሳው ይሉ የለ? የምረሳበትንም ባይሆን የሚተካልኝን ሰው አምጣው እንጂ እያልኩ ንጭንጭ እግዜሩ ላይ። ከትላንቴ ተጣብቄ አረጀሁኮ፣ አዲስ ዛሬ ስጠኝ እንጂ ንትርክ። ለምን እኔ ማንም የሌለኝ? ለምን እኔ ፍቅሬን የተነጠኩ? ለምን እኔን ከሰው አጥንት አልፈለቀከኝም? ከሰው ግራ ጎን አልሸለቀከኝም? ናፍቀሽኛል መባል አያምረኝም? አውሪኝ ትንሽ አትሂጂ መባል አይጎበኘኝም? ለምን እኔ? መች ነው የኔ ወረፋ? መች ነው ልቤ የሚሞላ ዳግም?

"ስሄድ ስሄድ ውዬ ስሄድ ስሄድ ነጋ
ጅብ አይበላም ብዬ የናፋቂን ስጋ"
.
.
.
ዛሬ ሌሊት በጣም ናፈቅኸኝ። ሁሌም ነው የምትናፍቀኝ፣ ሄዷል በቃ ብዬ አልተውኩህም። ትቶኛል በቃ ብዬ አልተቀየምኩህም። ትናፍቀኛለህ። እያለህ እንደምናደርገው በእኩለ ሌሊት ንፋስ ስልክ ጎዳና ላይ እንራመድ ብዬ ወጣሁ። አብረኸኝ ነበርክ። እያወራኸኝ፣ እያሳቅኸኝ፣ ያቺን ምላስህን አውጥተህ ትልልቅ ዓይንህን ለማጥበብ የምትታገልባትን ፊትህን እያሳየኸኝ። እየተራመድን ትተኸኝ ሮጥክ ልይዝህ ተከተልኩህ። አጥሩ የፈረሰው ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ተከትዬ ዘልዬ ገባሁ።

" እስኪ እናንተ ተኙ እኔ ስራ አለብኝ
ግንብ እገነባለሁ ፍቅር ተንዶብኝ"
.
.
.
አቅፌህ ካሸለብኩበት የጎረነነ ድምጽ ቀሰቀሰኝ። 'የኔ እህት እባክሽ ትለከፊያለሽ በዚህ ሌሊት አትምጪ፣ ብርዱም አይቻልም' መቃብር የሚቆፍር ጎልማሳ ቁልቁል እየተመለከተኝ። አያውቅም ቤቴ አንተ እንደሆንክ። አያውቅም የተናደ ፍቅሬን እዚህ እየመጣሁ ልገነባ እንደምጥር። አያውቅም ማንም እንደሌለኝ። አያውቅም ልክፍቴ ወዳንተ መምጣት እንደሆነ። አያውቅም የሚሞቀኝ እዚህ እንደሆነ። አያውቅም ምንም። ናፍቀኸኛል......

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Martha Haileyesus
HTML Embed Code:
2024/05/08 18:37:15
Back to Top