TG Telegram Group & Channel
አርማጌዶን | United States America (US)
Create: Update:

የተመድ የፍልስጤም አባልነት ውሳኔና ተጠባቂው የፀጥታው ምክር ቤት ምላሽ
ሪፖርተር – Ethiopian Reporter – #1 Best and reliable news source in Ethiopia (RSS)

ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best and reliable news source in Ethiopia

ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ሙሉ አባልነት ተገድባ የኖረችው ፍልስጤም፣ የድርጅቱ አባል እንድትሆን የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ በአብላጫ ድምፅ ድጋፍ ያገኘው ዓርብ ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ነበር፡፡

143 አገሮች የደገፉት፣ ዘጠኝ አገሮች የተቃወሙትና 25 አገሮች በድምፅ ተአቅቦ ያለፉት የፍልስጤም የአባልነት ጥያቄ በአብላጫ ድምፅ ቢያልፍም፣ የአባልነት ጥያቄው ምሉዕ እንዲሆን የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ይጠበቃል፡፡

በተመድ የእስራኤል አምባሳደር ጊላድ ኤርዳን የፍልስጤም የሙሉ አባልነት የውሳኔ ሐሳብ በተመድ በአብላጫ ድምጽ መፅደቁን ተከትሎ ተቃውሟቸውን የድርጅቱን

መተዳደሪያ ደንብ ቅጂ በመቅደድ አሳይተዋል (ኤኤፍፒ)ጋር መክረዋል

(ሮይተርስ)
የፀጥታው ምክር ቤት በቀጣይ በፍልስጤም የተመድ አባልነት ላይ የሚሰጠው ምላሽ አዎንታዊ ከሆነ፣ ፍልስጤም እ.ኤ.አ. ከ2012 ጀምሮ ከተሰጣት የታዛቢነት ወንበር ተሸጋግሯ መምረጥና መመረጥን ጨምሮ ምሉዕ የአባልነት መብት ይኖራታል፡፡

ከ193 የተመድ አባል አገሮች ውስጥ በ139 አገሮች የአገርነት ዕውቅና ያላት ፍልስጤም፣ ከእስራኤል ጋር ባለው የግዛት ይገባኛል ጥያቄ ምክንያት ከሃያላን አገሮች የምታገኘው ድጋፍ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡

በተለይ የፍልስጤም ጋዛን የሚያስተዳድረው ሃማስ ከእስራኤል ጋር በተደጋጋሚ የሚገባበት ግጭትና ጦርነት ለፍስጤምና ፍልስጤማውያን መከራ ሆኗል፡፡

ከሰባት ወራት በፊት በእስራኤልና በጋዛ መካከል በተነሳው ጦርነት ከ34 ሺሕ በላይ ፍልስጤማውያን፣ ከአንድ ሺሕ በላይ እስራኤላውን ሕይወታቸውን ተነጥቀዋል፡፡

በፍልስጤም ግዛቶች ውስጥ እስራኤል መስፋፋቷና ዜጎች ማስፈሯ፣ በየጊዜው በሁለቱ አገሮች መካከል ለሚነሱ ግጭቶች አንዱ ምክንያት ተደርጎ ይነሳል፡፡ የእየሩሳሌም የይገባኛል ጥያቄና ሌሎችም በሁለቱ መካከል የተፈጠሩ ቁርሾዎች፣ ምዕራቡ ዓለምና የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ልዩነት ውስጥ እንዲገቡም አድርጓል፡፡

እስራኤልና ፍልስጤምን ለማስማማት የተደረጉ ውይይቶችም ዘላቂ መፍትሔ አላመጡም፡፡ ከሁለቱ አገሮች በሚመነጭ ሐሳብ በቀጣናው ሰላም ለማስፈን የፍልስጤም የተመድ ሙሉ አባልነት አስተዋጽኦ ቢኖረውም፣ ዛሬም በአሜሪካ ይበልጡኑ የምትደገፈው እስራኤል፣ የፍልስጤምን አገርነትም ሆነ የተመድ አባልነት አትቀበለውም፡፡

የተመድ አባል አገሮች በአብላጫ ድምፅ ውሳኔ ሲያስተላልፉም፣ ‹‹ለፍልስጤም የአባልነት ዕድል መሰጠቱ ሽብርተኝነትን እንደመደገፍ ነው›› ስትል እስራኤል ተቃውማለች፡፡

ፍልስጤም በበኩሏ፣ አባል አገሮቹ በአብላጫ ድምፅ ያሳለፉት ውሳኔ በፀጥታው ምክር ቤት ለሚሰጠው ውሳኔ ማሳያ መሆኑን ገልጻለች፡፡

የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ፣ የፍልስጤምን የሙሉ አባልነት ውሳኔ ሐሳብ የፀጥታው ምክር ቤትም እንዲያፀድቀው ሲጠይቅ፣ በተናጠል አገሮች ምክር ቤቱ ፍልስጤምን እንዲቀበል ጥሪ እያቀረቡ ነው፡፡

ቻይና ፍልስጤም በተመድ ውስጥ ያልተገደበ መብት ሊሰጣት ይገባል ስትል ሐሳቧን ገልጻለች፡፡

ከሰባት ወራት ወዲህ በእስራኤልና ፍልስጤም ጋዛ መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ፣ በአሜሪካ በተለያዩ ግዛቶች እንዲሁም በአውሮፓ አገሮች የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እስራኤል በፍልስጤም ላይ የምታደርውን ወታደራዊ ዕርምጃ እንድታቆም በተቃውሞ እየጠየቁ ባለበት ወቅት፣ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ አብላጫው የተመድ አባል አገሮች ለፍልስጤም አባልነት ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡

የኖርዌይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ አናዶሉ እንዳቀረበው፣ የኖርዌይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፀጥታው ምክር ቤት ለፍስልጤም ሙሉ አባልነት እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡  

ኖርዌይ፣ ፍልስጤም እ.ኤ.አ. በ2012 የታዛቢነት ወንበር እንድታገኝ ከደገፉ አገሮች አንዷ ስትሆን፣ አሁን ላይም የፍልስጤም የተመድ ሙሉ አባል መሆን፣ በቀጣናው ያለውን ችግር ለመፍታት ያስችላል ብላ ታምናለች፡፡

ከወር በፊት ፍልስጤምን የተመድ ሙሉ አባል ለማድረግ ለፀጥታው ምክር ቤት በገባው ማመልከቻ፣ 12 የፀጥታው ምክር ቤት አባላት የፍልስጤምን ሙሉ አባልነት ሲደግፉ፣ አሜሪካ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቷን ተጠቅማ ውድቅ እንዳስደረገችው ይታወሳል፡፡

The post የተመድ የፍልስጤም አባልነት ውሳኔና ተጠባቂው የፀጥታው ምክር ቤት ምላሽ first appear on ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best and reliable news source in Ethiopia and is written by ምሕረት ሞገስ

>>Click here to continue<<

አርማጌዶን

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)