TG Telegram Group & Channel
አርማጌዶን | United States America (US)
Create: Update:

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ “ፍርድ ቤቱ የሰጠኝ ውሳኔ ገጽ ጎድሎታል” አለ
Addis Maleda (RSS)

ሐሙስ ጥቅምት 29 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ “የመከላከያ ሠራዊቱን ምስጢር ማውጣት” እና ሠራዊቱን መከፋፈል” በሚሉ ክሶች ነፃ መባሉን በመቃወም ዐቃቢ ሕግ የግባኝ መጠየቁን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ የሰጠው ውሳኔው እና ቅሬታው ሲደርሰው የጎደሉ ገጾች እንዳሉት ገልጿል።

በዚህም “ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአቃቤ ሕግን 16 ገጽ የይግባኝ ማመልከቻ ሲሰጠኝ፣ ከፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ጋር በተያያዘ የእኔን ምላሽ የሚሹ ገጾች ጎድለውታል” ብሏል።

“ክስተቱ አጋጣሚ ነው ብዬ አላምንም” ያለው ተመስገን ለዛሬ ጥቅምት 29/ 2016 በዋለው ችሎት የመልስ ማሻሻያ እንዲፈቀድለት በማመልከቻ ጠይቋል።

ይህንን ተከትሎ ዐቃቢ ሕግ በጉዳዩ ላይ አስተያየት መስጠት እንደሚፈልግ በመናገሩ፣ የጋዜጠኛው ጠበቆች “እኛ ስህተት ሰርቷል ያልነው ፍርድ ቤቱን እንጂ ዐቃቢ ሕግን አይደለም። ስለዚህም ዐቃቢ ሕግ በማይመለከተው ጉዳይ አስተያየት ሊሰጥ አይገባም” ሲሉ መቃወማቸውን አዲስ ማለዳ ለማወቅ ችላለች።

በዚህም ምክንያት በ2 ዳኞች የተሰየመው ፍርድ ቤት በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት አንድ ዳኛ ስለሚጎድል በሚል ለሕዳር 11/2016 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ዛሬ ጥቅምት 29/2016 ማለዳ የተካሄደውን ችሎት አስመልክቶ አስተያየቱን የሰጠው ጋዜጠኛው፤ “ፍርድ ቤቱ አቃቤ ሕግ ከብይን በኋላ እጠይቃለሁ ያለውን ይግባኝ ሳይጠይቅ መፍቀዱ፣ አስገራሚ ብቻ ሳይሆን ትልቅ የሕግ ጥሰትም ነው” ሲል ቅሬታውን ገልጿል።

“የመከላከያ ሠራዊቱን ምስጢር አውጥተሃል”፣ “ሠራዊቱ እንዲከፋፈል አድርገሃል” እንዲሁም “የተቋሙን ሥም አጥፍተሃል” በሚሉ ሦስት ክሶች ከግንቦት 18/2013 እስከ ህዳር 7/2014 ድረስ እስር ቤት የቆየው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ ክሱን ሲመለከት በነበረው የከፍተኛው ፍርድ ቤት የካቲት 29/2015 ባስተላለፈው ውሳኔ በሙሉ ድምጽ በነጻ መሰናበቱ ይታወሳል፡፡

ሆኖም ዐቃቢ ሕግ ክሱ ሳይቋጭ ጥቅምት 21/2015 ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በብይኑ ላይ ያቀረበው ይግባኝ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ፤ “ያስቀርባል” ሲል በመወሰኑ ይግባኙ በቀረበ በዓመቱ ጥቅምት 5/2016 ጉዳዩን ያየው ፍርድ ቤቱ ለውሳኔ ለዛሬ ጥቅምት 29/2016 ቀጥሮ ነበር፡፡

>>Click here to continue<<

አርማጌዶን

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)