TG Telegram Group & Channel
አርማጌዶን | United States America (US)
Create: Update:

የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አዲስ ሊገነባ ለታቀደው ብሔራዊ የአረጋዊያን ማዕከል ግንባታ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች
Addis Maleda (RSS)

ሐሙስ ጥቅምት 29 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ አምባሳደር ሙሐመድ ሳሬም አልረሺዲ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱም የሴቶችና ማህራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፤ ለአረጋውያን የሕክምና፣ የገቢ ማስገኛና ኹለገብ አገልግሎቶችን መስጠት የሚያስችል ማዕከል ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን ለአምባሳደሩ አብራርተዋል።

ደረጃውን የጠበቀ የአረጋውያን ማዕከል ለመገንባት የዲዛይን ሥራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ያሉት ሚኒስትሯ፤ ለግንባታው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አምባሳደር ሙሐመድ ሳሬም አልረሺዲ የኢትዮጵያ መንግሥት በብሔራዊ ደረጃ ለሚያስገነባው የአረጋውያን ማዕከል ግንባታ የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

አረጋውያንን ጨምሮ በአስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ሕይወት ለመለወጥና ለማሻሻል እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትንም አምባሳደሩ አድንቀዋል።

መንግሥት የአገር ባለውለታ የሆነት አረጋውያን መብት ለማስከበር፣ ማህበራዊ ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ እና የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ የሚረዳ ብሔራዊ የማህበራዊ ጥበቃ ፓሊሲና የማስፈጸሚያ ስትራቴጂ በመንደፍ በሥራ ላይ ማዋሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

>>Click here to continue<<

አርማጌዶን

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)