TG Telegram Group & Channel
አርማጌዶን | United States America (US)
Create: Update:

ሳንዶካን ደበበ የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተሾሙ
Addis Maleda (RSS)

ረቡዕ ጥቅምት 28 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ላለፈው አንድ ዓመት በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሲሰሩ የቆዩትሳንዶካን ደበበ፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ (chief of staff) ሆነው ተሾሙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የልዩ ጽህፈት ቤታቸውን እንዲመሩ ሳንዶካንን የሾሟቸው፤ ከሦስት ሳምንት በፊት መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ልዩ ጽህፈት ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሥር ካሉ ስድስት መዋቅሮች አንዱ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሥር ያሉ ሌሎች መዋቅሮች የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት፣ የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት፣ የፕሬስ ሴክሪተሪያት፣ የፖሊሲ እና የአፈጻጸም ክትትል ክፍል እንዲሁም የሪፐብሊኩ ጠባቂ ናቸው።

ሳንዶካን ልዩ ጽህፈት ቤቱን እንዲመሩ ከተሾሙ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር የመጀመሪያ የውጭ ጉዟቸውን ወደ ቻይና ማድረጋቸውንም ምንጮች ገልጸዋል። ሹመቱንም ሆነ የቻይናውን ጉዞ ሳንዶካን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ስልጣን እንደመጡ የልዩ ጽህፈት ቤታቸው ኃላፊ አድርገው በመጀመሪያ የሾሟቸው አሁን በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑትን ፍጹም አረጋን ነው። እርሳቸውን በመተካት የጽህፈቱ ቤት ኃላፊ የሆኑት በአሁኑ ወቅት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሆኑት ሽመልስ አብዲሳ ናቸው። ሽመልስ በሚያዝያ 2011 ለማ መገርሳን በመተካት የኦሮሚያ ክልልን እንዲመሩ ከመሾማቸው በፊት፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት በኃላፊነት ለሰባት ወራት ሰርተዋል።

ከግንቦት 2011 ጀምሮ ልዩ ጽህፈት ቤቱን ለስምንት ወራት በኃላፊነት ሲመሩ የቆዩት፤ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ሲሆን፤ ዶ/ር ሹመቴ ከልዩ ጽህፈት ቤት ኃላፊነታቸው ተነስተው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳን) በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ በጥር 2012 ሲሾሙ በምትካቸው በቦታው የተመደቡት መስፍን መላኩ ናቸው።

መስፍን በየካቲት 2015በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ክላስተር አስተባባሪ ሆነው ከተሾሙ በኋላ የኃላፊነት ቦታውን ተረክበው የነበሩት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ አማካሪነት ሲሰሩ የነበሩት መሐመድ ራፊ አባራያ መሆናቸውን ምንጮች ገልጸዋል። አዲሱ ተሿሚ ሳንዶካን ወደ ልዩ ጽህፈት ቤት ኃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት፤ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት ላለፉት 12 ዓመታት ሰርተዋል።

ሳንዶካን በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የነበራቸው ኃላፊነት፤ በአካባቢ ጥበቃ፣ የአየር ንብረት እና የስነ ህዝብ ጉዳዮች ላይ “ፖለቲካዊ አመራር” መስጠት መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል። ሳንዶካን በሚኒስቴሩ በነበራቸው ቆይታ የአየር ንብረትን በተመለከቱ ዓለም አቀፋዊ ስብሰባዎች ላይ ኢትዮጵያን በመወከል በተደጋጋሚ ተገኝተዋል።

>>Click here to continue<<

አርማጌዶን

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)