TG Telegram Group & Channel
አርማጌዶን | United States America (US)
Create: Update:

ክርክር የለኝም፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) ለአቶ ኃይለ ማርያም ስለተደረገው አሸኛኘትና ስለተሰጠው ሽልማት በሐዋሳ በዚያው ሰሞን ባደረጉት ንግግር ውስጥ ያነሱትንና ያቀረቡትን ምክንያት በሚገባ እረዳለሁ፡፡ የአገራችን የለውጥ መንኮራኩር የሚጠይቀው ግራሶ እንዳለም አውቃለሁ፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት የመንግሥት ወይም የአገር መሪዎች ኒሻንና ሜዳሊያ የመስጠት የአገርን ባለውለታነት በክብር የመግለጽና የማረጋገጥ ትክል ሥልጣን (ሕገ መንግሥቱ ውስጥ ባይኖር እንኳን) እንዳላቸው አውቃለሁ፡፡ ጥያቄው ግን ኢትዮጵያን የመሰለች ከዚህ በላይ አንደተባለው፣ ‹‹… በዓለም ላይ የሚገኙ የሠለጠኑ መንግሥታት እንደሚያደርጉት ሁሉ) ሳይሆን፣ ለእነሱ ጭምር ትምህርት የሰጠች የተቋቋመ የሚያስቀና (Honour System) የነበራት አገር እንዴት አድርጋ ይህን ጎዶሎ ይዛ ትኑር? እንዴትስ ይህን ዝግጁነት የሚያመለክት ባለሥልጣንና ባለ አገር ትጣ? ይህ ጎዶሎ በገዛ ራሱ ምክንያት ካለው አሉታዊ ውጤትና ጉዳት ይልቅ፣ ዛሬ በዚህ ጊዜ የለውጥ ተቀናቃኞች ‹‹ሕገ መንግሥት ተጣሰ›› የሚል ዱላ ሆኖ ሲያገለግልም ዓይተናል፡፡

የዴሞክራሲው ለውጥ በደረሰበት ደረጃ ልክ ቆንጠጥና ጠበብ አድርገን በጥንቃቄ እንድንረማመድ መገደዳችን ሳያንስ፣ እንዲህ ያሉ ክፍተቶችን ዝም ብለን እያየን የለውጡ ተቀናቃኞች የጭቃ ጅራፍ እንዲሆኑ መፍቀድ የለብንም፡፡

የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት በሕግ መሠረት ኒሻኖችንና ሽልማቶችን ይሰጣል (አንቀጽ 71/5)፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደግሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚያወጣው ሕግ ወይም በሚሰጠው ውሳኔ መሠረት ኒሻኖችንና ሽልማቶችን ለፕሬዚዳንቱ አቅርቦ ያሰጣል በማለት ይደነግጋሉ፡፡ ሁለቱም ድንጋጌዎች ውስጥ ‹‹ኒሻኖችና ሽልማቶች››ን በእንግሊዝኛው “Medals, Prizes and Gifts” ብሎ ውንብድብዱን ቢያወጣውም፣ የአገርን ባለውለታነት የማረጋገጥ የክብር ሥራ አስቀድሞ የወጣ ዝርዝር ሕግ የግድ ይፈልጋል፡፡ ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ የውጭ ተሞክሮ መቅሰም ያለባት አገር አይደለችም፡፡ የዓለም ሙዚየሞች የሚያውቁት የተቋቋመ የባለውለታነት ዕዳ መመስከሪያ የሽልማትና የማዕረግ ሥርዓት የነበራት አገር ናት፡፡

አገር በየመስኩ አስተዋጽኦ ላደረጉላትና መስዋዕት ለሆኑላት ወይም ለከፈሉላት ባለውለታነቷን ማረጋገጥ ውለታቸውን ማወቅ፣ ማሰብ፣ ማስታወስና ለወደፊቱም እንዲበረታቱ ማድረግ ያለባት መሆኑ የአገር የውለታ ባለዕዳነት ከሚረጋገጥባቸው መንገዶች፣ ከመስዋዕትነቱና ከአስተዋጽኦው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የሜዳልያና የኒሻን ሽልማት መስጠት እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ ሲወርድ ሲወራረድ የመጣም የመንግሥት አሠራር ነበር፡፡ በዚህ በተያያዝነው የዴሞክራሲና የለውጥ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይም ከአንድ ሁለት ጊዜ ተሰናባች የአገርና የመንግሥት መሪዎችን በሸኙበት ወቅት ተገልግለውበታል፡፡ ወይም የአገልግሎቱን አስፈላጊነት በተግባር አረጋግጠዋል፡፡ በሚያዝያ 2010 ዓ.ም እና በጥቅምት 2011 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) የሚመሩት መንግሥት የአገርን የውለታ ባለዕዳነት ልወጣ ሲል ግን፣ አገር አስቀድሞ የተዘጋጀ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 71(5) እና 74(11) መሠረት ስንዱ ሆኖ የሚጠብቅ፣ በተለይም የሲቪል የሜዳይና የኒሻን ሥርዓት አልነበራትም፡፡ ‹‹የሽልማት፣ የአድናቆትና የአክብሮት ሰርተፊኬት››፣ ‹‹የሻኒን አዋርድና ከፍተኛ የክብር ዲፕሎማ›› ‹‹የአገሪቱ ከፍተኛ የክቡር ዲፕሎማ›› ማለት ዓይነት ‹‹መቀባጠር››ም የመጣው ጉዳዩ የቢሻኝ ውሳኔ በመሆኑ ነው፡፡

የቢሻኝ ውሳኔ የሆነው መሸለሙ አይደለም፡፡ መሸለም የአገርና የመንግሥት ትክል (Inherent) ሥልጣኑ ነው፡፡ ዝርዝሩ ግን በሕግ መደንገግ አለበት፡፡ ከሁሉም በላይ፣ ከሌሎች መካከል በሕግ መደንገግ ያለበት የሽልማት ቅርፅ (በዝርዝር)፣ መጠንና አካል (ወርቅ፣ ወርቃማ፣ ወዘተ) አስቀድሞ በወጣ ሕግ ይወሰናል፡፡ ሜዳሊያና ኒሻን በትዕዛዝ የሚሠራ እንጂ የ‹‹አውርድልኝ›› ዕቃ አይደለም፡፡ መንግሥት ይህን ማስተካከልና ይህንን ጎዶሎ መሙላት አለበት፡፡

መንግሥት ይህን ማድረግ ያለበት ከ‹‹አውርድልኝ›› ዕቃ በዕውቅ የሚሠራ ዕቃ ይሻላል ተብሎ ብቻ አይደለም፡፡ በተሻላሚው ሰው አንገት ላይ በአደባባይ ሲጠለቁ የምናያቸው ሜዳይና ኒሻን መሳይ ቁሳቁሶች መጀመርያ የወንጀል ሕግ ጥበቃ የሚያገኙት (ከመንግሥት ፈቃድ ሳይሰጥ ሜዳይ፣ ኒሻን፣ ዓርማና ሪባን መሥራት፣ መጠቅምና አስመስሎ መሥራት ወንጀል) በሕግ ሲወሰን ነው፡፡ የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ (የመንግሥትና የሃይማኖት መለያዎች ድንጋጌ) ተጣሰ የሚለው ስሞታም ሆነ ክስ የሥር የመሠረት መከላከያም የሜዳዩን ዓይነት፣ ቅርፅና አካል አስቀድሞ በሕግ በመወሰን ነው፡፡

ይህን ጎዶሎ ከመሙላት ጋር ሌላም መፈጸም ያለበት ሌላ ጉዳይ አለ፡፡ በተለያዩ  ዘመናት በየትግል ዘርፉ ባለውለታ ሆነው የተከበሩና የተሾሙ ኢትጵያውያን (የውጭ አገር ዜጎችም አሉ)፣ መንግሥት በተለዋወጠ ቁጥር ባለውለታነታቸው እንደ ቆሻሻ የሚደፋበትና የሚደመሰስበት ያልተጻፈ ባህልና ሕግ አንድ ሊባል ይገባል፡፡     

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊዋን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

The post አገር ባለውለታነቷን የምታረጋግጥበት ሥርዓታችንን እንፈትሽ! first appear on ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best and reliable news source in Ethiopia and is written by አንባቢ

>>Click here to continue<<

አርማጌዶን

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)