TG Telegram Group Link
Channel: Walta Tv ዋልታ ቲቪ
Back to Bottom
እንኳን ለ2016 ዓ.ም የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
የክልል ርዕሠ መስተዳድሮች የ2016 የትንስኤ በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ሚያዝያ 26/2016 (አዲስ ዋልታ) የክልል ርዕሠ መስተዳድሮች የ2016 የትንስኤ በዓልን በማስመልከት ለክርስትና አምነት ተከታዮች የእንከን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሠላምና በጤና አደረሳችሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም የትንሳዔ በዓል መታዘዝን፣ይቅርታንና ምህረትን እንዲሁም አንዱ ለሌላው መተሳሰብ እንዳለበት የሚያስተምረን ነው ብለዋል፡፡

መረዳዳትንና መጠያየቅን ከተለመደው ባህል ባለፈ በፍጹም መንፈሳዊነት ስሜት በጎዳና ላይ የወደቁትን በማሰብ፣በህግ ጥላ ስር ያሉትን በመጠየቅ፣ታመዉ የተኙትን በማጽናናትና ካለን ላይ በማካፈል በአብሮነት ትንሳኤውን የምናከብርበት በዓል ሊሆን ይገባልም ስሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው ለትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው ክርስቶስ የአዳምን ዘር ከበደል ቀንበር ነፃ ያወጣበት፤ ለሰው ልጆች ምሕረትና ድኅነት፤ ሰላምና ፍቅር የተገኘበት በድምቀት የሚከበር ታላቅ በዓል ነው ብለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ አክለውም “በዓለ ትንሣኤው የዕርቅ፤ የይቅርታና የሰላም መገለጫ ነው፡፡ በሰውና በፈጣሪ መካከል የነበረ የጥል ግድግዳ በአምላክ ይቅር ባይነት የፈረሰበት፣ ዕርቅና ሰላም ወርዶ አዲስ የምሕረት ምዕራፍ የተከፈተበት በመሆኑ በዓሉን ስናከብር ቂም፤ ቁርሾና በቀልን በይቅርታ በመሻገር ሊሆን ይገባል” ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር የትንስኤ በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
ኤፕሲዊች ታዉን ወደ ፕሪሚዬር ሊግ ማደጉን አረጋገጠ

ሚያዚያ 26/2016 (አዲስ ዋልታ) ኤፕስዊች ታዉን ከ22 ዓመታት በኋላ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ተመለሰ።

በቅፅል ስማቸው ዘትራክተር ቦይስ የሚባሉት ኤፕስዊቾች ዛሬ ከሃደርስፊልድ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፉቸውን ተከትሎ ወደ ታላቁ ፕሪሚዬር ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል።

የቡድኑ ማደግ አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ ባለፈው ዓመት ከሶስተኛ ዲቪዚዮን ወደ ሻምፒዮንሽፑ አድጎ ባመቱ ደግሞ ወደ ፕሪሚዬር ሊጉ መመለሱ ነው የተገለጸው።

ይህም ሳውዝሃምፕተን እ.ኤ.አ 2012 ካስመዘገበው ታሪክ ጋር እንዲጋራ አስችሎታል።

በሻምፒዮንሽፑ 24 ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን በደረጃ ሰንጠረዥ አንደኛና ሁለተኛዎቹ ቡድኖች በቀጥታ ወደ ፕሪሚዬር ሊጉ ያድጋሉ። ሌስተር ሲቲ በኬራን ማኬና ከሚሰለጥነው ኤፕስዊች ታዉን ቀደም ብሎ ወደ ፕሪሚዬር ሊጉ መመለሱ ይታወሳል።

ቀጣዮቹ አራት ቡድኖች የደርሶ መልስ ጨዋታ አድርገው አንደኛ የወጣው ቡድን በሶስተኝነት ፕሪሚዬር ሊጉን ይቀላቀላል፡
"ዛሬ ማልደን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙ አቅመ ደካሞች እና የሃገር ባለውለታ የከተማችን ነዋሪዎችን በአብረሆት ቤተ መጽሃፍትፆም አስፈትተናል::

ትንሳኤ የፍቅር እና የርህራሄ ተምሳሌት በመሆኑ እኛም ጎብኚ እና ጠያቂ ከሌላቸው ነዋሪዎቻችን ጋር ምግብን ብቻ ሳይሆን ፍቅርን ተጋርተናል:: ሁላችንም በያለንበት አቅመ ደካሞችን እና ጠያቂ የሌላቸውን እያሰብን በዓሉን በፍቅርና በአብሮነት እናሳልፍ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!"

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጫካ ፕሮጀክት ላይ እየሠሩ ላሉ ሠራተኞችን፣ ለበዓል በተዘጋጀ የምሳ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው፣ የእንኳን አደረሳችሁ መልክት አስተላልፈዋል::
ዛሬ የማክሮኢኮኖሚ ኮሚቴ ከአገርበቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ አፈፃፀም ጋር የተያያዙ ሰፋ ያለ መጠነርዕይ ያላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል። - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
HTML Embed Code:
2024/05/08 18:51:01
Back to Top