TG Telegram Group & Channel
Walta Tv ዋልታ ቲቪ | United States America (US)
Create: Update:

የክልል ርዕሠ መስተዳድሮች የ2016 የትንስኤ በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ሚያዝያ 26/2016 (አዲስ ዋልታ) የክልል ርዕሠ መስተዳድሮች የ2016 የትንስኤ በዓልን በማስመልከት ለክርስትና አምነት ተከታዮች የእንከን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሠላምና በጤና አደረሳችሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም የትንሳዔ በዓል መታዘዝን፣ይቅርታንና ምህረትን እንዲሁም አንዱ ለሌላው መተሳሰብ እንዳለበት የሚያስተምረን ነው ብለዋል፡፡

መረዳዳትንና መጠያየቅን ከተለመደው ባህል ባለፈ በፍጹም መንፈሳዊነት ስሜት በጎዳና ላይ የወደቁትን በማሰብ፣በህግ ጥላ ስር ያሉትን በመጠየቅ፣ታመዉ የተኙትን በማጽናናትና ካለን ላይ በማካፈል በአብሮነት ትንሳኤውን የምናከብርበት በዓል ሊሆን ይገባልም ስሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው ለትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው ክርስቶስ የአዳምን ዘር ከበደል ቀንበር ነፃ ያወጣበት፤ ለሰው ልጆች ምሕረትና ድኅነት፤ ሰላምና ፍቅር የተገኘበት በድምቀት የሚከበር ታላቅ በዓል ነው ብለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ አክለውም “በዓለ ትንሣኤው የዕርቅ፤ የይቅርታና የሰላም መገለጫ ነው፡፡ በሰውና በፈጣሪ መካከል የነበረ የጥል ግድግዳ በአምላክ ይቅር ባይነት የፈረሰበት፣ ዕርቅና ሰላም ወርዶ አዲስ የምሕረት ምዕራፍ የተከፈተበት በመሆኑ በዓሉን ስናከብር ቂም፤ ቁርሾና በቀልን በይቅርታ በመሻገር ሊሆን ይገባል” ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

>>Click here to continue<<

Walta Tv ዋልታ ቲቪ

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)