ፊታቸው ይቀየራልን?
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
6፥79 *«እኔ ለዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው ቀጥተኛ ስኾን "ፊቴን" አዞርኩ፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም»* አለ፡፡ إِنِّي وَجَّهْتُ وَجْهِيَ لِلَّذِي فَطَرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ حَنِيفًا ۖ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ
የኢሥላምን መሠረትና ውቅር፣ ዋልታና ማገር፣ ጥልቀትና ስፋት፣ ድርና ማግ በቅጡ ያልተረዱ ሚሽነሪዎች፦ በሐዲስ ላይ ለሶላት ሶፍን ያልጠበቁትን አላህ ፊታቸውን ይቀይረዋል ይላል፥ ያልጠበቁ ፊታቸው የተቀየሩ አሁን የት አሉ? ብለው ይጠይቃሉ። በኢሥላም ያሉ የመስኩ ሊሒቃን፦ “ውኃን ከጡሩ፥ ነገርን ከሥሩ” ይላሉና እኛም የኢሥላም ዐቃቢያነ-እምነት እንደመሆናችን መጠን ከሥሩ ስለ "ፊት" በትክክለኛ የአስተላለፍና የአስነዛዘር ሙግት መልስ እንሰጣለን።
"ወጀህ" وَجْه ማለት "ፊት" ማለት ሲሆን በተለያየ ትርጉም ሊመጣ ይችላል። ወጀህ "ቀልብ" قَلْب ማለትም "ልብ" በሚል መጥቷል፦
37፥84 *ወደ ጌታው "በቅን ልብ" በመጣ ጊዜ የኾነውን አስታውስ*፡፡፡ إِذْ جَاءَ رَبَّهُ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ
እነዚህ አናቅጽ ላይ "ቅን" ለሚለው ቃል የገባው "ሠሊም" سَلِيم ሲሆን ይህም ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ተገዢ" "ታዛዥ" የሚለውንም ያስይዛል። ኢብራሂም ወደ አላህ በሠሊም ልብ የመጣው ልቡን ለአላህ በመስጠት ነው፦
6፥79 *«እኔ ለዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው ቀጥተኛ ስኾን "ፊቴን" አዞርኩ፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም»* አለ፡፡ إِنِّي وَجَّهْتُ وَجْهِيَ لِلَّذِي فَطَرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ حَنِيفًا ۖ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ
ኢብራሂም "ፊቴን" አዞርኩኝ ሲል ከአንገት በላይ ያለውን ቅል ማለት ሳይሆን ልቤን ማለቱ ነው፦
26፥89 *ወደ አላህ "በንጹህ ልብ" የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ*፡፡» إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيم
31፥22 እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ *ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥም* ሰው ጠንካራን ገመድ በእርግጥ ጨበጠ፡፡ የነገሩም ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ነው፡፡ وَمَن يُسْلِمْ وَجْهَهُ إِلَى اللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ ۗ وَإِلَى اللَّهِ عَاقِبَةُ الْأُمُورِ
"ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው" ማለት እና "ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥም ሰው" የሚለው ቃል ተለዋዋጭ ቃል ሆኖ መጥቷል። "የሰጠ" ለሚለው ቃል "ዩሥሊም" يُسْلِمْ መሆኑ በራሱ "ሠሊም" سَلِيم ከሚለው ጋር ምን ያህል ዝምድና እንዳለው አንባቢ ያጤነዋልም። እዚህ ድረስ ከተግባባን ሐዲሱ ላይ ያለው ጥያቄ ኢንሻአላህ ይመለሳል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 112
አን'ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ረድፎቻችሁን ቀጥ ታደርጋላችሁ ወይም አላህ በፊቶቻችሁ መሃል ይቀይራል"*። قَالَ سَمِعْتُ النُّعْمَانَ بْنَ بَشِيرٍ، يَقُولُ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم " لَتُسَوُّنَّ صُفُوفَكُمْ أَوْ لَيُخَالِفَنَّ اللَّهُ بَيْنَ وُجُوهِكُمْ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 272
አን'ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ከሰዎች በላይ በፊታቸው እንዲህ ሦስት ጊዜ፦ *"ረድፎቻችሁን ቀጥ አድርጉ! አሉ። "ወላሂ ረድፎቻችሁን ቀጥ ታደርጋላችሁ ወይም አላህ በልቦቻችሁ መሃል ይቀይራል" አሉ*። قَالَ سَمِعْتُ النُّعْمَانَ بْنَ بَشِيرٍ، يَقُولُ أَقْبَلَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَلَى النَّاسِ بِوَجْهِهِ فَقَالَ " أَقِيمُوا صُفُوفَكُمْ " . ثَلاَثًا " وَاللَّهِ لَتُقِيمُنَّ صُفُوفَكُمْ أَوْ لَيُخَالِفَنَّ اللَّهُ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ
"ሶፍ" صَفّ የሚለው ቃል "ሶፈ" صَفَّ ማለትም "ተሰለፈ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሰልፍ" ወይም "ረድፍ" ማለት ነው፥ የሶፍ ብዙ ቁጥር እነዚህ ሐዲሳት ላይ የተቀመጠው "ሱፉፍ" صُفُوف ነው። እዚህ ላይ ዋናው ነጥቡ የሚያሳየው ሶፍን እኩል አድርጎ ሶላት ዉስጥ መቆም ግዴታ መሆኑን ነው። ያለው ምርጫ ሁለት ነው፥ አንዱ ረድፎቻችሁን ቀጥ ታደርጋላችሁ ወይም ሌላው አላህ በልቦቻችሁ መሃል ይቀይራል። እንግዲህ ፊት የሚለው ልብ በሚለው እንደተፈሠረ ከላይ ዘንዳ ለሶላት ሶፍን ያልጠበቀውን ልቡን ይቀይረዋል ማለት እንጂ ከአንገት በላይ ያለው ቅል ይቀይረዋል ማለት አይደለም።
✍ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
ወሠላሙ ዐለይኩም
>>Click here to continue<<