ይህ የሮም መንግሥት 666 "ኖሮ ቄሳር" ነው" ተብሎ ይታመናል። "ኔሮውን ቅስር" נרון קסר በዕብራይስ ቁጥር፦
1. ኖን 50
2. ሬስ 200
3. ዋው 6
4. ኖን 50
5. ቆፍ 100
6. ሳምኬት 60
7. ሬስ 200
ድምር 666 ይሆናል።
ይህ አውሬ አሁን የለም። ተመልሶ የኔሮ ቄሳር የሮሙ መንግሥት ሆኖ ከባሕር ማለትም ከሕዝብ ይነሳል። ይህ የፕሮቴስታንት ትርጓሜ ነው። ስመ ጥርና ዝነኛ ከሆኑትን የፕሮቴስታንት ምሁራን አንዳቸውም ይህ አውሬ "በኢሥላም የሚጠበቀው መህዲ ነው" ብለው አላስተማሩም።
ከባሕር ከወጣው አውሬን ቀጥሎ ደግሞ ከምድር የወጣው ሌላውን አውሬ ሐሰተኛው ነቢይን ደግሞ ዳንኤል ላይ ካለው ጋር ያዛምዱታል፦
ዳንኤል 7፥8 *"ቀንዶችንም ተመለከትሁ፤ እነሆም፥ በመካከላቸው ሌላ ትንሽ ቀንድ ወጣ፥ በፊቱም ከቀደሙት ቀንዶች ሦስት ተነቃቀሉ፤ እነሆም፥ በዚያ ቀንድ እንደ ሰው ዓይኖች የነበሩ ዓይኖች በትዕቢትም የሚናገር አፍ ነበሩበት"*።
ዳንኤል 7፥24-25 *"ከእነርሱም በኋላ ሌላ ይነሣል፥ እርሱም ከፊተኞች የተለየ ይሆናል፥ ሦስቱንም ነገሥታት ያዋርዳል። በልዑሉም ላይ ቃልን ይናገራል፥ የልዑልንም ቅዱሳን ይሰባብራል፥ ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል፤ እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኵሌታ ዘመንም በእጁ ይሰጣሉ"*።
ሐሰተኛ ነቢይ ከእውነተኛው ነቢይ ከኢየሱስ በተቃራኒው የሚያሳስት ሐሳዌ መሢሕ ነው ብለው ያብራራሉ። ይህ ሐሳዌ መሢሕ "በኢሥላም የሚጠበቀው ዒሣ ነው" ብለው አላስተማሩም።
እንግዲህ ሁለቱም ማለት የኦርቶዶክስ እና የፕሮቴስታንት አተረጓጎም ቢለያይም፥ ቅሉ ግን ጽዮናዊነትን የሚያራምደው የወሊድ ሹዒባት ቅጥፈት ድባቅ ያስገባዋል። እርሱ ይህንን አተረጓጎም ያመጣው ለኢሥላም ካለው ጥላቻ የመነጨ እንጂ የሥነ-አፈታትን ጥናት ያማከለ አይደለም። መጽሐፉን በምላስ አጣሞ ትርጉሙ ከፈጣሪ ዘንድ ነው ማለት ዋሾዎች ጋር የተለመደ ነው፡፡ እነደነዚህ ያሉ ቀልማዳዎች ዕያወቁ በፈጣሪ ላይ ውሸትን ይናገራሉ፦
3፥78 *ከእነርሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ*፡፡ وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُونَ أَلْسِنَتَهُم بِالْكِتَابِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ الْكِتَابِ وَمَا هُوَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ
በራእይ ላይ የተተነበየው ሐሳዌ መሢሕ በኢሥላም መሢሑ አድ-ደጃል ነው። “አል-መሢሑ አድ-ደጃል” الْمَسِيحَ الدَّجَّال የሁለት ስም ውቅር ነው፥ የመሢሕ እና የደጃል የሚሉ ሁለት ስም ውቅር ነው። “አል-መሢሕ” الْمَسِيح የሚለው የዐረቢኛው ቃል “መሠሐ” مَسَحَ ማለትም “አበሰ” አሸ” “ቀባ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “የቀባ” አሊያም “የተቀባ” ወይንም “የሚያብስ” አሊያም “የታበሰ” ወይንም “የሚያሽ” አሊያም “የሚታሽ” የሚል ፍቺ አለው። ዒሣ ኢብኑ መርየም በሽተኞችን፣ ህሙማንን እና ሙታንን በማበስ፣ በማሸት እና በመቀባት ከበሽታቸው በአላህ ፈቃድ ያሽራቸው ስለነበረ እና በአላህ የተሾመ(የተቀባ) ነቢይ ስለሆነ “አል-መሢሕ” ተብሏል። አምላካችን አላህ በተከበረው ቃሉ በዘጠኝ አንቀፆች 11 ጊዜ ኢየሱስ መሢሕ መሆኑን ነግሮናል፤ ለናሙና ያክል አንዱን አንቀጽ ብንመለከት በቂ ነው፦
3፥45 መላእክት ያሉትን አስታዉስ፡- መርየም ሆይ አላህ ከእርሱ በሆነዉ ቃል ስሙ *አል-መሢሕ* ዒሣ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለምና በመጨረሻዉም ዓለም የተከበረ፣ ከባለማሎችም በሆነ ያበስረሻል። إِذْ قَالَتِ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ يَٰمَرْيَمُ إِنَّ ٱللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍۢ مِّنْهُ ٱسْمُهُ ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًۭا فِى ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةِ وَمِنَ ٱلْمُقَرَّبِينَ
መርየም ከአላህ በሆነው ቃል የተበሰረችው ልጇ፦ ስሙ አልመሲሕ ዒሣ መሆኑን፣ የመርየም ልጅ መሆኑን፣ በዚህ ዓለምና በመጨረሻዉም ዓለም የተከበረ መሆኑን እና ከባለማሎችም አንዱ መሆኑን ነው።
ይህንን ካየን ዘንዳ ወደ መሢሑል ደጃል መሄድ እንችላለን፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 129
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ደጃል ዓይኑ የታበሰ ነው፤ በዓይኖቹ መካከል “ካፊር” የሚል ጽሑፍ አለ፤ ከዚያም “ከፈረ” የሚል አነባነብ ሁሉም ሙሥሊም ያነበዋል”*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ” الدَّجَّالُ مَمْسُوحُ الْعَيْنِ مَكْتُوبٌ بَيْنَ عَيْنَيْهِ كَافِرٌ ” . ثُمَّ تَهَجَّاهَا ك ف ر ” يَقْرَؤُهُ كُلُّ مُسْلِمٍ ”
“የታበሰ” ለሚለው ቃል የገባው “መምሡሑ” مَمْسُوحُ ሲሆን ቁርኣን ላይ “ማበስ” ለሚለው የስም መደብ “መሥሕ” مَسْح በሚል መጥቷል፦
38፥33 «በእኔ ላይ መልሷት» አለ አጋዶችዋንና አንገቶችዋንም *ማበስ* ያዘ፡፡ رُدُّوهَا عَلَىَّ ۖ فَطَفِقَ مَسْحًۢا بِٱلسُّوقِ وَٱلْأَعْنَاقِ
በዓይኖቹ መካከል “ካፊር” የሚል ጽሑፍ አለ፤ “ካፊር” كَافِر ማለት “ከሃዲ” ማለት ሲሆን “ከፈረ” የሚል አነባነብ ሁሉም ሙሥሊም ያነበዋል፤ “ከፈረ” كَفَرَ ማለት “ካደ” ማለት ነው፤ “ፋ” ف በሸዳ ተሽዲድ ስናረጋት ደግሞ “ከፍፈረ” كَفَّرَ ሲሆን “ሸፈነ” ማለት ነው፤ “ካፉር” كَافُور ማለት “የተሸፈነ” ማለት ነው፤ ለምሳሌ በጀነት ለበጎ አድራጊዎች መበረዣዋ “ካፉር” ተብላለች፦
76፥5 በጎ አድራጊዎች መበረዣዋ *ካፉር* ከኾነች ጠጅ ይጠጣሉ፡፡ إِنَّ ٱلْأَبْرَارَ يَشْرَبُونَ مِن كَأْسٍۢ كَانَ مِزَاجُهَا كَافُورًا
“አድ-ደጃል” الدَّجَّال የሚለው ቃል “ደጀለ” دَجَلَ ማለትም “አጭበረበረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “አጭበርባሪ” ወይም "ሐሳዌ" ማለት ነው። ዋናው ደጃል “መሢሑ አድ-ደጃል” ማለትም “ሐሳዌ መሢሕ” ሲሆን እርሱ ከመምጣቱ በፊት የሚመጡ ሠላሳ ደጃሎች አሉ።
“ደጃሉን” دَجَّالُونَ የሚለው ቃል “ደጃል” دَجَّال ለሚለው ነጠላ ቃል ብዜት ነው። እነዚህ ወደ ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ወይም “እኔ የአላህ ነብይ ነኝ” ብለው ይነሳሉ፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 108
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“የመጨረሻይቱ ሰአት አትቆምም ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች ቀጣፊዎች ተነስተውስ፦ “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ብለው ቢናገሩ ቢሆን እንጂ”*። عَنْ أَبِي، هُرَيْرَةَ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يُبْعَثَ دَجَّالُونَ كَذَّابُونَ قَرِيبٌ مِنْ ثَلاَثِينَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ
>>Click here to continue<<