አውሬው 666
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
3፥78 *ከእነርሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ*፡፡ وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُونَ أَلْسِنَتَهُم بِالْكِتَابِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ الْكِتَابِ وَمَا هُوَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ
ጽዮናዊነትን የሚያራምደው ወሊድ ሹዒባት፦ "ራእይ ላይ ከባሕር የሚወጣው አውሬ መህዲ ሲሆን ከምድር የሚወጣው አውሬ ደግሞ ዒሣ ነው" የሚል የራሱን ዝንባሌ በመከተል የሚተረጉምበት አተረጓጎም አለው። ይህ ትርጓሜ ለቤተክርስቲያንም ሆነ ለታሪክ እንግዳ ትርጓሜ ነው። የክርስትና ዐቃቢያነ-እምነት ሳም ሻሙስ እና ጀምስ ኃይት ይህንን አተረጓጎ ክፉኛ የተሳሳተ እንደሆነ ይሞግታሉ። ራእይ ላይ ስለ አውሬው የሚናገረው ነገር ትንቢት ነው፥ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፦
2 ጴጥሮስ 1፥20 ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ *"በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም"*።
ይህንን ከተረዳን በጥንቃቄ ስለ አውሬው ለማየት እንሞክር። "አውሬ" ማለት "ጨካኝ" "ተናካሽ" "አረመኔ" "ስግብግብ" ማለት ነው። ባይብል ክፉዎችን የምድር መንግሥታትን "አውሬ" ይላቸዋል። ዳንኤል አንበሳ፣ ድብ፣ ነብር እና የምታስፈራ አራት ታላላቅ አራዊት ከባሕር ሲወጡ አይቷል፥ እነዚህ አራዊት በምድር ላይ ኃያላን መንግሥታት የነበሩ ባቢሎን፣ ፋርስ፣ ግሪክ እና ሮም ናቸው፦
ዳንኤል 7፥3 *"አራትም ታላላቅ አራዊት ከባሕር ወጡ፥ እያንዳንዲቱም ልዩ ልዩ ነበረች"*።
ዳንኤል 7፥17 *"እነዚህ አራቱ ታላላቅ አራዊት ከምድር የሚነሡ አራት ነገሥታት ናቸው"*።
ይህ ስለ አውሬ እሳቤው እንዲኖራችሁ ማሟሻ ነው። ይህንን እሳቤ ይዘን ራእይ ላይ ያሉትን አራዊት መረዳት እንችላለን፦
ራእይ 13፥1 *"አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ"*።
ይህ አውሬ በኦርቶዶክስ የትርጓሜ መጽሐፍ ላይ ሐሳዌ መሢሕ ነው፦
ራእይ 13፥1 አንድምታ፦ *"አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ" አለ። ሐሳዌ መሢሕ ነው፥ መንግሥቱም ገና አልተደላደለችምና "እም ባሕር" አለ። ታሪክ የሐሳዌ መሢሕን ትውልድ ከዚህ ይናገሩለታል፦ እናቱ ከዳን ነገድ፥ አባቱ ከኤሳው ነገድ ናቸው"*።
*"አሐቲ ዐይኑ ዘፍስሐት" ይላል፤ -አንድ ዐይኑ የሞተች ናት፥ "ወአሐዱ ዐይኑ ዘስሩር በደም" ይላል። አንድ ዐይኑ ደም የሰረበው ፈጣጣ ነው"*።
አንድ ሰው ኦርቶዶስ ሆኖ "ይህ አውሬ መህዲ ነው" ማለት የጤና ነውን? መህዲ ከነቢያችን"ﷺ" ሥርወ-ግንድ ከዐሊይ እና ከፋጢማ የሚመጣ እንጂ ከአይሁድ ሥርወ-ግንድ የሚመጣ በፍጹም አይደለም። ይህ አንድ ዐይኑ የሞተች ባለ አንድ ዐይን ሐሳዌ መሢሕ ስም አለው፥ ስሙ ቁጥር አለው፦
ራእይ 13፥17-18 *"የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል"*። ጥበብ በዚህ አለ። አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፥ *"ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው"*።
ራእይ 15፥2 *"በአውሬው እና በምስሉም በስሙም ቍጥር"* ላይ ድል ነሥተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጭቆ ባሕር ላይ ሲቆሙ አየሁ።
ስሙ መርምያዋዖስ ሲሆን የስሙ ቁጥር 666 ነው፦
ራእይ 13፥17-18 አንድምታ፦ "ስሙም በዕብራይስጥ "መርምያዋዖስ" በግዕዝ ደግሞ "ፀራዊ" ማለትም "ተቃዋሚ" ወይም "ሐሳዊ" ማለትም "ሐሰተኛ" የሚል ነው። "መርምያዋዖስ" የሚለው ቁጥሩ፦
1. ሜም 40
2. ሬስ 200
3. ሜም 40
4. ዮድ 10
5. ዋው 6
6. ዔ 70
7. ሳን 300
ድምር 666 ይሆናል።
ማሳሰቢያ፦ በፓፒረስ 115 እና ኮዴክድ ኤፍሬማይ 616 ἑξακόσιοι δέκα ἕξ እንጂ 666 ἑξακόσιοι ἑξήκοντα ἕξ አይልም። ኦርጅናሉም 616 ነው የሚል ሙግት አለ፥ ይህ ሌላ ርእስ ነው።
በኦርቶዶክስ ዘንድ አንድም ቀን ይህ አውሬ "በኢሥላም የሚጠበቀው መህዲ ነው" ብሎ ያስተማረ አንድም ሊቅ የለም።
ከባሕር ከወጣው አውሬ ቀጥሎ ደግሞ ከምድር የወጣው ሌላውን አውሬ ሐሰተኛው ነቢይ ይለዋል፦
ራእይ 13፥11 *"ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፥ የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት እንደ ዘንዶም ይናገር ነበር"*።
ራእይ 13፥14 *"በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል"*።
ራእይ 19፥20 አውሬውም ተያዘ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ"*።
ይህ ሐሰተኛው ነቢይ በኦርቶዶክስ አንድምታ "ኤልያስ ነኝ" ብሎ የሚመጣ "ሐሰተኛው ኤልያስ" ነው። እንደ አንድምታው ከሆነ ኤልያስ እንዴት አርጎ ነው ዒሣ የሚሆነው? በኢሥላም ተስተምህሮት ውስጥ ኤልያስ ይመጣል የሚል ትምህርት የለም። በኦርቶዶክስ ዘንድ አንድም ቀን ይህ ሐሰተኛው ኤልያስ "በኢሥላም የሚጠበቀው ዒሣ ነው" ብሎ ያስተማረ አንድም ሊቅ የለም። ይህ ከላይ ያየነው የኦርቶዶክስ አተረጓጎም ነው።
የፕሮቴስታት ትርጓሜ ደግሞ ላይ አውሬው "አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት" በሚል ይነሱና ዳንኤል ላይ ያለውን "አራተኛው አውሬ ነው" ይላሉ፦
ዳንኤል 7፥7 *"ታላላቅም የብረት ጥርሶች የነበሩአት አራተኛ አውሬ ነበረች"*፥ ትበላና ታደቅቅ ነበር፥ የቀረውንም በእግርዋ ትረግጥ ነበር፤ ከእርስዋም በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየች ነበረች *"አሥር ቀንዶችም ነበሩአት"*።
ዳንኤል 7፥23-24 እንዲህም አለ፦ *"አራተኛይቱ አውሬ በምድር ላይ አራተኛ መንግሥት ትሆናለች"*፥ እርሱም ከመንግሥታት ሁሉ የተለየ ይሆናል፥ ምድሪቱንም ሁሉ ይበላል፥ ይረግጣታል ያደቅቃትማል። *"አሥሩም ቀንዶች ከዚያ መንግሥት የሚነሡ አሥር ነገሥታት ናቸው"*።
አራተኛይቱ መንግሥት ከባቢሎን፣ ከፋርስ፣ ከግሪክ በኃላ የተነሳችው የሮም መንግሥት ናት። የሮም መንግሥት አስቀድሞ ነበረ፥ በራእይ ወደ ፊት ሲመለከት የለም። ከዚያ ከጥልቁ ባሕር ከሕዝብ ተመልሶ ይነሳል፦
ራእይ 17፥8 *ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፥ አሁንም የለም፥ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ ያደንቃሉ*"።
>>Click here to continue<<