ሐዲድ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
57፥25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችን እና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን፥ *"ብረትንም በውስጡ ብርቱ ኀይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያሉበት ሲኾን አወረድን"*፡፡لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِالْبَيِّنَاتِ وَأَنزَلْنَا مَعَهُمُ الْكِتَابَ وَالْمِيزَانَ لِيَقُومَ النَّاسُ بِالْقِسْطِ ۖ وَأَنزَلْنَا الْحَدِيدَ فِيهِ بَأْسٌ شَدِيدٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ
አምላካችን አላህ"ﷻ" ወደ ነቢያችን"ﷺ" መጽሐፍ እና ሚዛን አውርዷል፦
42፥17 አላህ ያ *”መጽሐፉን በእውነት ያወረደ ነው፡፡ ሚዛንንም እንደዚሁ*”፡፡ ሰዓቲቱ ምንአልባት ቅርብ መኾንዋን ምን ያሳውቅሃል? ٱللَّهُ ٱلَّذِىٓ أَنزَلَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ وَٱلْمِيزَانَ ۗ وَمَا يُدْرِيكَ لَعَلَّ ٱلسَّاعَةَ قَرِيبٌۭ
ይህም መጽሐፍ እና ሚዛን ቁርኣን ነው፥ መጽሐፍ እና ሚዛን የቁርኣን ስሞች ናቸው። ለምሳሌ ተውራት መጽሐፍ እና ፉርቃንን ተብሏል፦
2፥53 ሙሳንም *”መጽሐፍን እና ፉርቃንንም”* ትመሩ ዘንድ በሰጠነው ጊዜ አስታውሱ፡፡ وَإِذْ ءَاتَيْنَا مُوسَى ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْفُرْقَانَ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ
“ሚዛን” مِيزَان እውነትን ከሐሰት፣ ትክክለኛውን ከስህተት፣ ሰናዩን ከእኩይ የምንለይበት መመዘኛ ነው። ይህ መመዘኛ አምላካችን አላህ"ﷻ" ወደ መልእክኞቹ አውርዷል፦
57፥25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ *"መጽሐፎችን እና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን፥ ብረትንም በውስጡ ብርቱ ኀይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያሉበት ሲኾን አወረድን"*፡፡لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِالْبَيِّنَاتِ وَأَنزَلْنَا مَعَهُمُ الْكِتَابَ وَالْمِيزَانَ لِيَقُومَ النَّاسُ بِالْقِسْطِ ۖ وَأَنزَلْنَا الْحَدِيدَ فِيهِ بَأْسٌ شَدِيدٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ
"ሐዲድ" حَدِيد የሚለው ቃል በቁርኣን 6 ጊዜ የመጣ ሲሆን "ብረት"Iron" ማለት ነው። "ሐዲድ" የ 57ኛው ሱራ ስም ነው፥ ይህ ሱራ ላይ አምላካችን አላህ"ﷻ"፦ "ብረትንም በውስጡ ብርቱ ኀይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያሉበት ሲኾን አወረድን" በማለት ይናገራል። ታዲያ ይህ ብረት ከየት ነው የወረደው? ስንል "አንዘልና" َأَنزَلْنَا ማለትም "አወረድን" የሚለው ቃል "ገለጥን" ወይም "ሰጠን" በሚል ይመጣል፦
7፥26 የአዳም ልጆች ሆይ! *"ኀፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስ ጌጥንም በእርግጥ በእናንተ ላይ አወረድን"*፡፡ አላህን የመፍራትም ልብስ ይህ የተሻለ ነው፡፡ ይህ ከአላህ ታምራቶች ነው፡፡ ይገሠጹ ዘንድ አወረደላቸው፡፡ يَا بَنِي آدَمَ قَدْ أَنزَلْنَا عَلَيْكُمْ لِبَاسًا يُوَارِي سَوْآتِكُمْ وَرِيشًا ۖ وَلِبَاسُ التَّقْوَىٰ ذَٰلِكَ خَيْرٌ ۚ ذَٰلِكَ مِنْ آيَاتِ اللَّهِ لَعَلَّهُمْ يَذَّكَّرُونَ
16፥14 *እርሱም ያ ባሕርን ከእርሱ እርጥብ ስጋን ልትበሉና ከእርሱም "የምትለብሱትን ጌጣጌጥ" ታወጡ ዘንድ የገራ ነው*፡፡ وَهُوَ الَّذِي سَخَّرَ الْبَحْرَ لِتَأْكُلُوا مِنْهُ لَحْمًا طَرِيًّا وَتَسْتَخْرِجُوا مِنْهُ حِلْيَةً تَلْبَسُونَهَا وَتَرَى الْفُلْكَ مَوَاخِرَ فِيهِ وَلِتَبْتَغُوا مِن فَضْلِهِ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
ልብ አድርግ "ጌጣጌጥ" ከባሕር የሚወጣ ነገር ሲሆን አላህ ለእኛ ስላገራው "አወረድን" ብሎታል እንጂ ከሰማይ መውረድን አያመለክትም፥ እንዲሁ ብረትንም በውስጡ ብርቱ ኀይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያሉበት ሲኾን አውርዶታል። የቤት እንስሳ ግመል፣ ከብት፣ ፍየል እና በግ ከእነ ጥንዳቸው ስምንት ሲሆኑ ወርደዋል ይላል፦
39፥6 ከአንዲት ነፍስ ፈጠራችሁ፡፡ ከዚያም ከእርሷ መቀናጆዋን አደረገ፡፡ *"ለእናንተም ከግመልና ከከብት፣ ከፍየል፣ ከበግ ስምንት ዓይነቶችን ወንድና ሴት "አወረደ"*፡፡ خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ ثُمَّ جَعَلَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَأَنزَلَ لَكُم مِّنَ الْأَنْعَامِ ثَمَانِيَةَ أَزْوَاجٍ
"አንዘለ" أَنزَلَ ማለት "አወረደ" ማለት ሲሆን ስምንቱ ጥንድ እንስሳ ወርደዋል ማለት ለሰው ልጆች አገልግሎት ተሰጥተዋል ማለት ከሆነ ብረትም ወረደ ማለት መጠቃቀሚያ ያለበት ሲኾን ለሰው ልጆች አገልግሎት ተሰቷል ማለት ነው። "አንዘለ" أَنزَلَ የሚለው ቃል ደመና ከተሸከመው ሰማይ ዝናብን ለማውረድ ተጠቅሞበታል፦
6፥99 *"እርሱም ያ ከሰማይ ውኃን ያወረደ ነው፡፡ በእርሱም የነገሩን ሁሉ በቃይ አወጣን*፡፡ وَهُوَ الَّذِي أَنزَلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَأَخْرَجْنَا بِهِ نَبَاتَ كُلِّ شَيْءٍ
"ሠማእ" سَّمَاء ማለትም "ሰማይ" ከላይ ያለውን "ጠፈር"Space" ለማመልከት ከገባ ብረት እራሱ ከጠፈር ሥነ-ፈለካዊ ክስተት"supernova" የመጣ በውስጡ ብርቱ ኀይል እና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያሉበት ነው። የብረት ዑደት"cycle" ከአየር ክልል"atmo-sphere" ወደ ውኃ ክልል"hydro-sphere" ከዚያ ወደ ሕይወት ክልል"bio-sphere" በመቀጠል ወደ ዐለት ክልል"litho-sphere" አርጎ በተለያየ ሁኔታ ያልፋል።
ብርቱ ኀይል እና ለሰዎች መጠቃቀሚያ መባሉ ብረት ካርበን ሲገባበት አስተኔ ብረት"steel" ይሆንና ለመሠረተ-ልማት፣ ለግንባታ፣ ለኤሌትሪክ ወዘተ ይሆናል። በሰውነታችን ውስጥ ፕሮቲንን ለቀይ የደም ሕዋስ የሚያጓጉዘው ይህ የብረት ክምሽት"hemoglobin" ነው፥ በዚህም የአንድ ጎልማሳ አካል 4 ግራም ወይም 0.005% ክብደት ብረት አለው። በሰማያትና በምድር ውስጥ ለምእምናን ሁሉ እርገጠኛ ምልክቶች አሉ፥ ይህንን በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም ውስጥ ያሉትን ምልክቶች ቆመው፣ ተቀምጠውም፣ በጎኖቻቸው ተጋድመውም የሚያስተነትኑ ምንኛ የታደሉ ናቸው? አላህ ከሚያስተነትኑ ባሮቹ ያርገን! አሚን፦
45፥3 *"በሰማያትና በምድር ውስጥ ለምእምናን ሁሉ እርገጠኛ ምልክቶች አሉ"*፡፡ إِنَّ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ لَآيَاتٍ لِّلْمُؤْمِنِينَ
3፥19 እነርሱም እነዚያ ቆመው፣ ተቀምጠውም፣ በጎኖቻቸው ተጋድመውም አላህን የሚያወሱ በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑ፡- «ጌታችን ሆይ! ይኸን በከንቱ አልፈጠርከውም፤ ጥራት ይገባህ፤ ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው፡፡ الَّذِينَ يَذْكُرُونَ اللَّهَ قِيَامًا وَقُعُودًا وَعَلَىٰ جُنُوبِهِمْ وَيَتَفَكَّرُونَ فِي خَلْقِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ رَبَّنَا مَا خَلَقْتَ هَـٰذَا بَاطِلًا سُبْحَانَكَ فَقِنَا عَذَابَ النَّارِ
✍ ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
>>Click here to continue<<