TG Telegram Group Link
Channel: TIKVAH-ETHIOPIA
Back to Bottom
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... የቤተሰብ ዋነኛ ፍላጎት ፍትህን ማግኘትና እውነቱን ማወቅ ነው " - የአቶ በቴ ኡርጌሳ ቤተሰብ የአቶ በቴ ኡርጌሳ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈፅሟል። ስርዓተ ቀብራቸው ቤተሰቦቻቸው ፣ ዘመዶቻቸው በርካታ ሰዎች ፣ ወዳጆቻቸው በተገኙበት ዛሬ በመቂ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው የተፈፀመው። አንድ ቀላቸውን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ የሰጡ የቤተሰብ አባል ፤ " ያው እንደ በቴ ከዚህ በላይ ብጠበቅም ብዙ…
የአቶ በቴ ኡርጌሳ ምርመራ ከምን ደረሰ ?

“ ... ምርመራው ተጀምሯል ፤ እየቀጠለ ነው ” - ኢሰመኮ

በኦሮሚያ ክልል፣ መቂ ከተማ ተገደሉትን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር አቶ በቴ ኡርጌሳን ጉዳይ በተመለከተ በርካታ መረጃዎች አድርሰናችሁ ነበር። 

ሰሞኑን ደግሞ ፦

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ላይ የጀመረውን ምርመራ በደረሰበት ጫና ማቆሙን ኮሚሽኑ ወደ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከላከው ደብዳቤ ላይ መመልከቱን " አዲስ ስታንዳርድ " ድረገጽ ዘግቧል።

“ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተሳትፎ መኖሩን የሚያመለክት ምስክሮችን ማሰባሰብ ከጀመረ ከ3 ቀናት በኋላ የምርመራው ቡድን ‘ ምርመራውን እንዲያቆርጥ መገደዱን ’ ” በደብዳቤ መግለጹ ነው የተዘገበው።

“ በዕለቱ ሌሊት ላይ 6 ሰዓት አከባቢ ከከተማዋ ወጣ ብሎ የበቴ አስከሬን በተገኘበት መንገድ ላይ አንድ ባለሁለት ጋቢና ፒክአፕ በፍጥነት በመጓዝ ከዋናው መንገድ ወጣ ብሎ መብራት ሳያጠፋ መቆሙን ” በደብዳቤው መገለጹም ተመላክቷል። 

ደብዳቤው ፥ “ ቀይ መለዮ ኮፊያ እና ዥጉርጉር ወታደራዊ የደንብ ልብስ የለበሱ እና መሳሪያ የታጠቁ አራት (4) ሰዎች ከመኪናዋ በመውረድ ከመኪናዋ ኋላ አንድ (1) ሰው ጎትተው በማውረድ በተደጋጋሚ በመተኮስ ጥለውት ሂደዋል ” ማለቱንም ዘገባው አትቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ ፤ በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ የሚደረገው ምርመራ እውነት ቆሟል ወይስ እንደቀጠለ ነው ? ሲል ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥያቄ አቅርቧል።

የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ በሰጡት ቃል፣ “ ምርመራው ተጀምሯል ፤ እየቀጠለ ነው ” ብለዋል።

የምርመራው ሂደት ምን ይመስላል ? በተጨባጭ የተገኙ ጉዳዮች አሉ ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ “ ምርመራው Ongoing ስለሆነ አስተያየት ለመስጠት ትንሽ ያስቸግራል ” ከማለት ውጪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

“ Ongoing investigation ነው። የተወሰኑ #ቻሌንጆች_አሉ። ግን እየተነጋገርን ነው ከክልሉ ባለስልጣናት ጋር ” ነው ያሉት።

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት አቶ በቴ በተገደሉበት ወቅት ግድያው ' ባልታወቁ ሰዎች መፈጸሙን ' ገልጾ መርምሬ ለህዝብ ውጤቱን ይፋ አደርጋለሁ ማለቱ ይታወሳል። ይህን ካለ ሳምንታት ቢያልፉም እስካሁን ለህዝብ የተሰጠ ግልጽ የሆነ መረጃ / ማብራሪያ የለም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ጠንካራ ሴት ለመሆን የሚከፈለውን ዋጋ በደንብ እንረዳለን፣ ህልምዎና
ፍላጎትዎ እንዲሳካ የአደይ ቁጠባችን
ያግዝዎታል! ባንካችን ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች ያዘጋጀውን አደይ ልዩ የቁጠባ ሂሳብ አቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፍ በመክፈት የልዩ አገልግሎቶቹና ጥቅሞቹ ተጋሪ ይሁኑ።

#BankofAbyssina #WomenSavingAccount #bankinginethiopia #banksinethiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

" መንግሥት የሰውን ሞት ትኩረት እየሰጠው አይደለም " ሲል እናት ፓርቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ለሰጠው ቃል ወቅሷል።

ድርጊቱን ማስቆም እንዳለበትም አጥብቆ ጠይቋል።

እናት ፓርቲ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበረው ቆይታ ምን አለ ?

Q. ፓርቲው አሁናዊ የኢትዮጵያ የጸጥታ እና ደህንነት ሁኔታ እንዴት ይገመግመዋል ? በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ? 

እናት ፓርቲ ፦

" አገራዊ ሁነቱ የውድቀት አፋፍ ላይ ነው ያለው። ኢትዮጵያ ከእግዚአብሔር ጥበቃ በታች የመጨረሻ የሚባለውን ሰቆቃ እያየች ነው።

ሰው በሰላም ወጥቶ የማይገባባት፣ የሰው ሞት የእንስሳትን ሞት ያህል የማያስጨንቅበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።

በሌላ ጎን ሞቱ አለ፤ በሌላ መንገድ ደግሞ ሞቱን የሚንቅ አለ። ‘ይሄ በለውጥ ሂደት ውስጥ የሚያጋጥም ነውና እኔ ትክክለኛ ስራዬን እየሰራሁ ነው ፤ ከእኔ ስንፍናና ጉብዝና የሚገናኝ አይደለም ' ብሎ የሚያምን፣ ለሕዝብ ሞት እውቅና የማይሰጥ ስርዓት ነው ያለው። "

Q. መፍትሄው ምንድን ነው ?

እናት ፓርቲ ፦

" የአማራ ሕዝብ የህልውና አደጋ፣ ከፍተኛ መከፋት ውስጥ ወድቋል። እናም መንግሥት እሰጥ አገባውን አቁሞ ወደ ድርድር መምጣት አለበት። 

ድርድሩ ደግሞ ቄስ፣ ሼይኽ በመላክ አይሆንም። ምክንያቱም ይሄ ስርዓት እንዲህ አይነት እሴቶችን የሚያከብር ይመስላል እንጂ አይቀበልም።

የሚቀበለው ባለዶላር ፤ ባለዩሮዎችን ነው። ስለዚህ እነሱ በተገኙበት ለ “ ሸኔ ” እንደተደረገው ቁጭ ብሎ መነጋገሩ የተሻለ ነው። "

Q. “ መርጦ አልቃሽ ናችሁ ” የሚል አስተያዬት ለፓርቲያችሁ ይሰጣል ፤ ለዚህ ምላሻችሁ ምንድን ነው ?

" በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ ትግራይ፣ በተለይ አማራ፣ በሃይማኖት ደግሞ ኦርቶዶክስ በፍጹም ታርጌት ተደርጎ ይገደላል። ይሄ ማለት ኦሮሞ ውስጥ ያለው ኦሮሞ አይገደልም ማለት አይደለም። 

በእስልምናውም በክርትናውም ነባር በሆኑት ተደጋጋሚ ግድያ ይደረጋል። በዛ ምክንያት ሞቅ ብሎ ተሰምቶ ሊሆን ይችላል።

ሞቅ ብሎ የተሰማው ግን በተግባር የተደረገ ነው። አልተደረገም ብሎ የሞገተን አካል የለም፤ ሊኖርም አይችልም፤ እውነት ነውና። "

Q. እንደ ፓርቲ ደረሰብን የምትሉት ጫና ምንድን ነው ?

እናት ፓርቲ ፦

" በአመራሮች ላይ እስራት እየተፈጸመ ነው። ለአብነትም የወልዲያና አካባቢው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ደርበው ከዋሽ አርባ በእስር እየማቀቀ ይገኛል። 

ምርጫ ቦርድ የተሻለ ነበር በዘመነ ብርቱካን፤ አሁን ‘ለምን’ ብሎ የሚጠይቅ የለም። ስብሰባ መሰብሰብ፣ በአካል ማግኘት አይቻልም።

ፓለቲካ ላይ መስራትን በእሳት እንደ መጫወት ነው ያደረገው ስርዓቱ። "

Q. በቀጣይ ይደረጋል ተብሎ ለሚጠበቀው ሀገራዊ ምርጫ ምን አይነት ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ? ለህዝብ አማራጭ ሆኖ ለመቅረብ እየተዘጋጃችሁ ነው ?

እናት ፓርቲ ፦

" ዝግጅት እያደረግን ነው። እውነትም ምርጫ አለ ወይ ? የሚለው ጥያቄ በሁላችንም አዕምሮ የሚመላለስ ቢሆንም እያደር የምንገልጻቸው ጉዳዮች ይኖራሉ። በምርጫ ተሳትፈን ማሸነፍ ነው በቸኛው አማራጫችን። "

📱 ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተከታታይ የሌሎች #በህጋዊ_መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎችን ሁሉ ሀሳብ ያቀርባል።

በተለይም ፦
- ስለሀገራዊ ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳይ ያላቸውን ግምገማ
- ስለዜጎች የሰብዓዊ መብት ፣
- ስለብልሹ አሰራር
- ስለኑሮ ሁኔታ
- ስለቀጣዩ ምርጫ አማራጭ ሆኖ ለመቅረብ ስላላቸው ዝግጅት በዋነኝነት ያነሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ?

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሲፈጸም እንደቆየ የተነገረለት እጅግ በጣም የለየለት የህዝብ ገንዘብ እና ሀብት ምዝበራን የሚያሳይ የ " ፋና ቴሌቪዥን " የምርመራ ዘገባ ከሰሞኑን ለህዝብ ተሰራጭቶ ነበር።

👉 በአበል መልክ የሚመዘበረው ገንዘብ ፦

የተቋሙ ገንዘብ በአበል መልክ ይመዘበራል።

ለአብነት ሁለት የፋይናንስ ቡድን መሪዎች ከፍተኛ አበል ለራሳቸው ከፍለዋል።

አቶ መሰረት ለማ የተባሉት ግለሰብ በ6 ወራት ብቻ የ1 ሺህ 496 ቀን ይህ ማለት 1 ሚሊዮን 56 ሺህ 854 ብር አበል ተከፏላቸዋል።

አቶ ደስታ ደቦጭ የሚባሉት ደግሞ የ940 ቀን አበል ወስደዋል።

➡️አቶ ደስታ የስንት ቀን አበል ወሰዱ ? ሲባሉ " የ790 ቀን ነው የወሰድኩት " ብለዋል።

ወስደዋል እንዴ ? ተብለው በመርማሪ ጋዜጠኛው ሲጠየቁ " #አልወሰድኩም " ሲሉ ቃላቸውን አጥፈው ተናግረዋል።

➡️አቶ መሰረት የ1 ሺህ 496 ቀን አበል ወደ አካውንቶ ገብቷል ? ተብለው ሲጠየቁ " ይሄ ስህተት ነው የተሰሳሳተ ነው " ሲሉ መልሰዋል።

የተቋሙ ፋይናስ ዳይሬክተር አቶ ማርቆስ ዮሐንስ ፥ " እኔ ለረጅም ወራት ፍቃድ ላይ ነበርኩኝ የህመም ፍቃድ ላይ ከመጣሁ በኃላ ነው እንደዚህ አይነት ነገር እሰማ ነበር " ብለዋል።

አቶ ደስታ ግን በዚህ አይስማሙም፤ አቶ ማርቆስ ታመው ቤት የተቀመጡት 2 ወር ብቻ እንደነበር የወጣው ደግሞ የ5 ወር መረጃ እንደሆነ ገልጸዋል። 3 ወር የሰራው እራሱ ነው ሲሉ አጋልጠዋል።

ቀደም ሲል " እኔ አበል አልወሰድኩም " ያሉት አቶ ደስታ 3 ወር የሰራው እራሱ ነው ሲሉ እሱ እያለ ነው የተከፈሎት ? ተብለው ሲጠየቁ " ምኑን ? እንደ ስራ ባህሪ የተከፈለኝ ነገር ሊኖር ይችላል " ሲሉ መልሰዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ሀብቶሙ አበበ (ዶ/ር) ፥ " በሰነድ የተረጋገጠ ነው ብሎ የውጭ ኦዲት ያመጣውን ያክል አስመልሰናል ሰራተኞቹ ከስራ እንዲታገዱ ተደርጓል፤ በዲስፒሊም እየተጠየቁ ናቸው የኛ ኦዲት ያመጣውን የትራዛክሽኑን ቼክአፕ በህግ እንዲጣራ ክትትል እየተደረገ ነው " ብለዋል።

የፋይናስ ስርአታቹ ክፍተት ያሉት ይመስላል ሲባሉ " በፍጹም በፍጹም !! " ሲሉ መልሰዋል።

👉 ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ስለወጣበት ፕሮጀክት ፦

ለኦክስጅን ማምረቻ በሚል ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ግልጽነት በጎደለው መልኩ ተፈጽሟል።

በዚህ ጉዳይ ፕሬዜዳንቱ እና የፋይናንስ ዳይሬክተሩ እርስ በእርስ የሚያወዛግብ ምላሽ ነው የሰጡት።

የፋይናንስ ዳይሬክተሩ ያለ ሰነድ ከእውቅናቸው ውጭ ገንዘቡ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ይገልጻሉ።

ክፍያ ሲፈጸም ሰነድ እጃቸው ላይ እንደሌለ እና እሳቸውም እንዳልተሳተፉ ተናግረዋል።

የፋይናንስ ዳይሬክተሩ " እኔ እኮ ዝርዝር መረጃ አልተሰጠኝም ፤ እንደሚንቀሳቀስ አያለሁ እሰማለሁ " ብለዋል።

ገንዘቡን እኔ አላንቀሳቅስም ነበር ብለዋል።

ፕሬዜዳንቱ ግን የኦክስጂን ፕሮጀክት በጀቱ ሲመራ የነበረው በፋይናንስ ነው ሲሉ መልሰዋል።

የፋይናንስ ዳይሬክተሩ እኔ ሳላውቅ ነው ክፍያው የተፈጸመው ሲሉ ተናግረዋል።

የቀድሞ ም/ፕሬዜዳንት ፀደቀ ላምቦሬ (ዶክተር) ፤  የአካውንቱ ጉዳይ በዋነኝነት የሚመለከተው ፕሬዜዳንቱን እንደሆነ ገልጸዋል።

▪️ለኦክስጅን ማምረቻው መሳሪያውን ያቀረበው ያለጨረታ ያለፍቃድ ያለውድድር 240 ሚሊዮን 988 ሺህ ብር ተሰጥቶታል። ለድርጁ ሙሉ ክፍያ ቢከፈልም ዝርጋታው ግን አላለቀም ስራውም አልተሰራም። ከተጀመረ 2 ዓመት አልፎታል።

የምርመራ ዘገባውን ይመልከቱ👇
https://youtu.be/wREkP5S8zNM?feature=shared (አዘጋጅ ፦ ጋዜጠኛ አፈወርቅ እያዩ)

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" በሚቀጠለው ዓመት ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች አይኖሩም " - ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ

የትምህርት ሚኒስቴር እና የ22 ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 በጀት ዕቅዳቸው መገምገሙን ገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።

የትምህርት ሚኒስቴር፣ የሚኒስቴሩ ሁለት ተጠሪ ተቀማት፣ የ8 የምርምር እና የ14 የአፕላይድ አጠቃላይ 22 ዩኒቨርስቲዎች የ2017 በጀት እቅድ በገንዘብ ሚኒስቴር በተካሄደ የበጀት ስሚ መርሀ ግብር መገምገሙ ተነግሯል።

በግምገማው ወቅት የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ፤ የመንግስትን በጀት በእቅድ ለተያዘለት አላማ ብቻ በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም ይገባል ብለዋል።

አስፈጻሚ መ/ቤቶች እና የስራ ሀላፊዎች በጀትን በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በበኩላቸው ፤ " በሚቀጠለው ዓመት ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች አይኖሩም " ብለዋል።

ሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱ እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ የበጀት እቅዳቸውን በተቀመጠላቸው የበጀት ጣሪያ መሰረት አስተካክለው በጠቂት ቀናት ውስጥ ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በፕሮጀክት ስም የሚወጣው ገንዘብ ?

በየዩኒቨርሲቲዎች " ለሥራ ኃላፊዎች የሚከፈል ክፍያ " በሚል የሚመዘበረው ገንዘብ  ከፍ ያለ ነው።

ሰዎቹ ከመንግሥት በጀት / አካል ውጭ ተጻጽፈን በሚመጣልን ድጋፍ ፕሮጀክት እየሰራን ብር ይከፈለናል ነው የሚሉት።

ክፍያው ግን እጅግ የተጋነነ ከመሆኑ የተነሳ ግልጽነት የጎደለው፣ ብዙ ጥርጣሬንም የሚያጭር ነው።

መንግሥት ደመወዛቸውን እየከፈላቸው እያለ " ላስተባበሩበት " በሚል እዛው ግቢያቸው ውስጥ ለሚሰራ ስራ የሚከፈላቸው ብር ብዛት የሚገርም ነው።

ለአብነት፦

ሰሞኑን ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ስለሚፈጸም አይን ያፈጠጠ የለየለት የህዝብ ሀብት ምዝበራን በተመለከተ በተሰራጨው የፋና ምርመራ ዘገባ ላይ ዶ/ር ተመስገን ቶማስ በሰኔ ወር 2013 ዓ/ም ብቻ የተከፈላቸው ገንዘብ በርከት ያለ ነው።

ዶክተሩ ምንም እንኳን " ቁጥሩም እኮ ሳይገለጽ መነጋገር እንችላለን " ቢሉም አይገለጽ ያሉት ቁጥር ግን ይህንን ይመስላል።

19,500 ብር (ሰንድ 1)
11,700 ብር (ሰንድ 2)
23,212 ብር (ሰንድ 3)
19,500 ብር (ሰንድ 4)
7,800 ብር (ሰንድ 5)
23,400 ብር (ሰንድ 6)
19,500 ብር (ሰንድ 7)
19,500 ብር (ሰንድ 8)
15,600 ብር (ሰንድ 9)
14,644 ብር (ሰንድ 10)
14,644 ብር (ሰንድ 11)
22,000 ብር (ሰንድ 12)
17,500 ብር (ሰንድ 13)
23,400 ብር (ሰንድ 14)
39,000 ብር (ሰንድ 15)
19,500 ብር (ሰንድ 16)
14,644 ብር (ሰንድ 17)
19,500 ብር (ሰንድ 18)
14,644 ብር (ሰንድ 19)
21,450 ብር (ሰንድ 20)

እኚህ ሁሉ በሰኔ ወር 2013 የተከፈሉ ናቸው።

ዶክተሩ ግን እስቲ ልየው 😳 በሰኔ ወር ነው የተከፈለው ? ብለው ይጠይቃሉ ዶክመቱም ይሰጣቸዋል፤ በኃላም ዶክመንቱን ያገላብጡና " እስቲ 2013 የሚለው የታለ ? " ሲሉ ድጋሜ ይጠይቃሉ " ይኸው ! " ይባላሉ ፤ በዝምታ ከተዋጡ በኃላ " እ ! " ብለው ዶክመንቱን መልሰዋል።

ዶ/ር ተመስገን በተለያየ ጊዜ የተባከ ክፍያ የፋይናንስ ባጀት ስለሌለ በአመቱ መጨረሻ ባጀት ሲያገኝ ገብቶ ነው እንጂ በአንዴ የተላከ አይደለም ብለው ተከራርክረዋል።

ሌላው የዩኒቨርሲቲው የፋይናንስ ዳይሬክተር ማርቆስ ዮሐንስ ብዙ ገንዘብ የተከፈላቸው ሲሆን " እኔ ብዙ ፕሮጀክት ስለምሰራ ነው። ቀንም ማታም ቅዳሜና እሁድም በፕሮጀክት  ላይ ሰራው ከመንግስት ስራ ሰዓት ውጭ ለዛ ነው የተከፈለኝ ባይ ናቸው።

ዳይሬክተሩ በቀን 18 ሰኔ ወር 2013 ዓ/ም 13,650  ብር እንዲገባላቸው የታዘዘበት ዶክመት የተገኘ ሲሆን በቀን 23 / 2013 ዓ/ም 15,600 ብር እንዲገባላቸው ታዟል በተመሳሳይ ቀን 19,600 ብር እንዲገባላቸው ተደርጓል።

ሌሎችም በርካቶች ናቸው ነው ያሉት።

ዶ/ር ተመስገን ጨምሮ አሁን ስልጣን ላይ ያሉትን ዶክተር ሀብታሙ አበበ ጋር የፋይናንስ ዳይሬክተሩ ስም በክፍያ ዶክመት ላይ " ፕሮጀክት " ተብሎ ተገኝቷል።

በአጠቃላይ በዋቸሞም ሆነ በመሰል ተቋማት በፕሮጀክት ስም የሚወጣው ብር እጅግ ብዙ ፣ ከደመወዛቸው እጥፍ፣ ግልጽነት የጎደለው ነው።

ሌሎቹ ዩኒቨርሲቲዎችስ ?

@tikvahethiopia
Forwarded from telebirr
ባልተገደበ የፕሪሚየም ጥቅላችን ከወዳጅ ዘመድ ጋር ግንኙነትዎ ሳይቋረጥ የስራ እንቅስቃሴዎ ሳይገደብ ዘና ብለው ይጠቀሙ !

በሳምንታዊና በወርሃዊ ያልተገደበ ፕሪሚየም አማራጮች የቀረቡትን ጥቅሎች በቴሌብር  ሱፐርአፕ፣ በማይ ኢትዮቴል፣ አርዲ ቻትቦት ወይም በ*999# ያገኟቸዋል!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
HTML Embed Code:
2024/06/11 09:31:42
Back to Top