TG Telegram Group & Channel
TIKVAH-ETHIOPIA | United States America (US)
Create: Update:

“ የመሪጌታው ሁለቱ ልጆቹ ሲገደሉ የ1 ዓመት ከ5 ወር ህፃን ብቻ ነው የቀረው  ” - የዓይን እማኝ

በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ አርሲ ዞን በዶዶላ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ሁለት የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪ የዓይን እማኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

አንድ ሟቾቹ መቀበራቸውን የተመለከቱ የዓይን እማኝ በሰጡት ቃል፣ “ በአጠቃላይ 7 ሰዎች ናቸው የተገደሉት። የቀብር ስርዓታቸው ዛሬ ተፈጽሟል ” ብለዋል።

“ ትላንት 3 ሰዓት ላይ ነው የተገደሉት። አንድ መሪጌታ ከእነባለቤቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋ፣ አንድ ዲያቆን ከእነባለቤቱና እህቱ ጋር 7 ሰዎች ናቸው የተገደሉት። የመርጌታው ሁለቱ ልጆቹ ሲገደሉ የ1 ዓመት ከ5 ወር ህፃን ብቻ ነው የቀረው ” ሲሉ አክለዋል።

ገዳዮቹ ማን ናቸው ? የት ነው የገደሏቸው ? ሟቾቹ ከዚህ በፊት ዛቻና መስፈራሪያ ደርሷቸው ነበር ? ከግድያው ባሻገር የቆሰሉ አሉ? የሟቾቹ መኖሪያ ልዩ ቦታ ምን ይባላል ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርቧል።

ነዋሪው በሰጡት ምላሽ፣ “ ገዳዮቹ ማን እንደሆኑ አልታወቀም። እቤታቸው ነው የገደሏቸው። በሟቾቹ ላይ ከዚህ በፊት የደረሰ ማስፈራሪያ አልሰማንም። ከህብረተሰቡ ጋር ጤነኛ በሆነ ግንኙነት በሰላማዊ መንገድ ኑሯቸውን ከመምራት ውጪ ምንም ግጭት አልነበራቸውም። ቦታው ዶዶላ 02 ቀበሌ ነው ” ብለዋል።

ከሟቾች ውጪ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እንደሌሉ፣ የቀብር ስርዓታቸው ዛሬ በቅዱስ ገብረ ክስስቶስ ገዳም 8፡30 እንደተፈጸመ፣ ገዳዮቹ እንዳልተያዙ አስረድተው፣ መንግሥትና በተዋረዱ ያሉ አካላት ለእንዲህ አይነት ድርጊት ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቀዋል። 

በቤተክርስቲያኗ ሆነ በመንግሥት ባለስልጣናት በኩል ስለጉዳዩ ምላሽ ለማግኘት ለጊዜው ያልተሳካ ሲሆን፣ የሚሰጥ ምላሽ ካለ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።

መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo

>>Click here to continue<<

TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)