Graphics/Display/Video Card
ወይም በትክክለኛ ስሙ GPU /Graphics Process Unit/
አሁን አሁን የምንሸምታቸውን ላፕቶፖች Graphics card አለው ወይስ የለውም ብሎ ማጣራት የተለመደ ሆኗል። በነገራችን ላይ መጠኑ እና ጠቀሜታው ይለያይ እንጂ ኮምፒውተር የተባለ ነገር ሁሉ በኛ አጠራር ግራፊክስ ካርድ አለው።
Graphics Card ማለት ከ ፎቶ እና ቪዲዮ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ነገሮች በምንጠቀምበት ሰአት ፈጣን እና ከፍተኛ ጥራት ባለው መንገድ አቀናብሮ መስራት የሚያስችል የ ማትስ ቀመር የሚጠቀም Hardware Device ነው።
♦️ በተለይም አዳዲስ ጌሞች እና ለ Rendering የሚያገለግሉ ሶፍትዌሮች ለመጠቀም( Photo Shop , Revit...) በጣም አስፈላጊ ናቸው። በተለይ ለ Architecture ተማሪዎች ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው። በአሁን ጊዜ በስፋት የሚታወቁት Nividia እና AMD ናቸው።
♦️ ሁለት አይነት ካርዶች ሲኖሩ የመጀመርያዎቹ ከ mother board ጋር ተጣብቆ / integrated ሆነው የሚመጡ ሲሆኑ intel በስፋት ይታወቅበታል። ሁለተኛው ደግሞ ለብቻ የሚሸጡ dedicated ናቸው።
እኛ ሀገር በስፋት ከ ላፕቶፖች ጋር integrated ሆነው የሚመጡ ሲሆኑ መጨመርም ሆነ መቀየር የማንችላቸው ናቸው።
፨፨ከ Nividia እና ከ AMD የትኛው ይሻላል?፨፨
AMD( Advanced Micro Device) ረዘም ያለ ዕድሜ ያስቆጠረ ሲሆን ግራፊክስ ብቻ ሳይሆን CPU ም ያመርታል። በተለይም የግራፊክስ ካርዶችን በ Radeon Brand የሚወጣ ነው። Nividia ባንጻራዊነት በቅርቡ የተመሰረተ ሲሆን ዋና አላማውም ግራፊክስ ካርዶችን ማምረት ነው። በ Geforce Brand የሚወጣ ሲሆን በብቃትም ሆነ በፍጥነት ከ AMD እንደሚሻል ብዙዎቹ ይስማማሉ።
እስካሁን እንደ ባለሞያ እንዳየነው ብዙ ጊዜ fail እያረገ የሚመጣው AMD የተገጠመላቸው ቦርዶች ናቸው።
፨፨ ኮምፒዩተራችን Graphics card
እንዳለው እና እንደሌለው እንዴት ማወቅ እንችላለን?፨፨
♦️ የ window 10 ተጠቃሚ ከሆናቹ Task Manager ላይ ገብታቹ performance ላይ side bar ላይ ያለውን GPU በመጫን ማየት የምትችሉ ሲሆን
♦️ የ window 7 ተጠቃሚዎች ደግሞ Run ( window key + R ) ላይ dxdiag ብላቹ ከጻፋቹ በኻላ በሚመጣላቹ window ላይ display በመጫን ማግኘት ትችላላቹ!
♦️ ብዙ ጊዜ ካልተላጠ ደግሞ keyboard አከባቢ ተለጥፎ ይገኛል።
!!ማሳሰብያ!!
♦️ Driver ያልተጫነበት ኮምፒዩተር በጣም ቀርፋፋ እና graphics ካርዱን ማግኘት አይችልም!
♦️ አንዳንድ ላፕቶፖች ደግሞ ለመሰረታዊ አግልግሎት የሚሆኑ intel graphics እና ከዛ ለበለጡ አገልግሎቶች የሚሆኑ AMD አልያም Nividia geforce graphics ካርዶችን አንድ ላይ ሊይዝ ይችላል።
~© Ethio tech zone
@techzone_ethio
>>Click here to continue<<