TG Telegram Group & Channel
ᴇᴛʜɪᴏ ᴛᴇᴄʜ ᴢᴏɴᴇ | United States America (US)
Create: Update:

ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ክፍያ አገልግሎት በቅርቡ ሊጀምር ነው
=======================
ኢትዮ ቴሌኮም በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ደንበኞች ስልካቸውን በመጠቀም ብቻ ገንዘብ እንዲልኩ፣ እንዲቀበሉና ግዢ እንዲፈፅሙ የሚያስችል የሞባይል ክፍያ አገልግሎት ሊጀምር መሆኑ ተነገረ፡፡ ቴሌብር የተሰኘው የክፍያ ስርዓቱ ደንበኞች ካሽ ወይም ቼክ ሳያስፈልጋቸው ዘርፈ ብዙ ክፍያዎችን እንዲፈፅሙ የሚያደርግ ነው፡፡
ቴሌብር ደንበኞች በሀገር ውስጥም ሆነ ዓለም አቀፍ ደረጃ በሁሉም የትስስር መንገዶች ላይ ገንዘብ መላላክን፣ ለዕቃና አገልግሎቶች ግዢ የሚደረጉ ክፍያዎችን መፈፀም እንዲያስችል ተደርጎ መሰራቱ ተገልጿል፡፡ በዚህም ደንበኞች ለምሳሌ የትምህርት ቤት፣ የውሃና ኤሌክትሪክ እንዲሁም ሌሎች መሰል ክፍያዎችን በስልካቸው እንዲፈፅሙ ያስችላቸዋል፡፡ በተጨማሪም በኢትዮ ቴሌኮም ለሚቀርቡ እንደ አየር ሰዓት ግዢ ላሉ አገልግሎቶች ክፍያን እንዲፈፅሙ ያመቻቸ ነው፡፡ በሌላ መልኩ አገልግሎቱ የኩባንያው ደንበኞች ከሀገር ውጪ ካለው ዲያስቦራ ገንዘብ እንዲቀበሉ፣ ገንዘባቸውን እንዲቆጥቡ፣ ብድር እንዲያገኙና የባንክ አካውንታቸውን ከቴሌብር ጋራ እንዲያስተሳስሩ የሚፈቅድ ይሆናል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቱን ያስጀምር ዘንድ ከአንድ ዓመት በፊት ለዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ፍቀድ ለሚሰጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጥያቄውን አቅርቦ ነበር፡፡ ባንኩም ለአገልግሎቱ አረንጓዴ መብራት ከሰጠ በኋላ ነው ኩባንያው እንቅስቃሴውን የጀመረው፡፡
ደንበኞች ለቴሌብር ለመመዝገብ የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ ያለበት ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን እና ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ይዘው ወደ ቴሌብር ወኪሎች አልያም የኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከላት በማምራት መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

>>Click here to continue<<

ᴇᴛʜɪᴏ ᴛᴇᴄʜ ᴢᴏɴᴇ

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)