#PHYTON 🔍(part - one)🔍
ሠላም ሠላም ውድ የ ethio tech ቤተሠቦች ዛሬ ይዘንላቹ የመጣነው ከ Programming language ሥለ ፓይተንን (phyton)
በተመለከተ የመጀመርያውን ክፍል ይዘንለቹ መተናል ተከታተሉን እውቀት እንደምታገኙበት ተሥፋ አናደርጋለን።
ፓይተን(phyton)
ፓይተን ብዙ ግልጋሎት ያለው ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ ሢሆን ልክ እንደ ጃቫሥክሪፕት ተፋላጊ እና በጣም በማደግ 📈ላይ ካሉ ፕሮግራሚን ላንጉጅኦች አንዱ ነው።
ፓይተንን በአሁኑ ሠአት⏱ በአለማችን🌐 ላይ ብዙ ሠዎች ይጠቀሙታል ።ሦፍት ዌር ኢንጂንየርኦች፣ሣይንቲሥትዎች ፤
አካውንታትኦች እንዲሁም ታዳጊህፃናት እነዚህ ሁሉ ፓይተንን ይጠቀማሉ። ምክንያቱም ፓይተን ጀማሪዎች እንኳን በቀለሉ ሊረዱት የሚችሉት በመሆኑ ነው። ሥለዚህ የተለያዩ ሠዎች ማለትም የተለያየ ሥራ ላይ የሚገኙ ሠዎች ለሥራቸው ፓይተንን ይጠቀማሉ።
ተከታታይ (ተደጋጋሞሽ) ያላቸው ነገሮች መሥራት
like ፦
📍 ፋይል ኮፒ ማድረግ
📍 ማህደር (ፎልደር ) ክሬት ማድረግ
📍 ሥሙን መቀየር
📍 ወደ ሠርቨር መጫን just የሚያሠለች ነገር ነው ። ነገር ግን ፓይተን ሥክሪፕት በመፃፍ ሁሉንም ነገር በቀለሉ መሥራት እና ጊዜአችንን መቆጠብ ይሥችለናል።
ፓይተንን በመጠቀም
🔌፦ዌብ አፕሊኬሽን 🔎
🔌፦ ዴሥክቶፕ አፕሊኬሽን🖥
🔌፦ ለሦፍትዌር ሙከራ
🔌፦ለሃኪንግ ወዘተ...ሥለዚህ ፓይትን ብዙግልጋሎት
ያለው ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ ነው።ነገር ግን ከላይ የተጠቀሡትን ነገሮች ሌላ ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ በመጠቀም መሥራት አንችልም እንዴ?🤔 ብላቹ ልትጠይቁ ትችላላቹ ። መልሡ እንችላለን ነው።
ሆኖም ግን ፓይተንን ሥንጠቀም
1 📌ውሥብሥብ ( complex) ነገሮች በአጭር ጊዜ እና በጥቂት መሥመር ኮድ መፃፍ ያሥችለናል።
🖍ለምሣሌ 'hello world' ከሚለው ቃል ውሥጥ ሦስቱን(hel) ብቻ ፕሪንት ለማድረግ
🔹C# str.substring(0, 3)
🔹phyton(py) str[ 0,3 ]
ከዚህም ፓይተን(phyton) ምን ይህል እጭር እና ግልፅ እንደሆነ መረዳት እንችላለን።
2📌 አፃፃፋ (syntax)ቀላል በመሆኑ
ፓይተን ለመማርም ሆነ በራሣችን አንብቦ ለመረዳት ቀላል ነው።ፓይተንን ከሌሎች ጋር ብናነፃፅር like ከC++,C#,Php,java etc... ከሁሉም በላይ ግልፅ እና እጭር ኮድ መጠቀም ያሥችለናል።
🖍ለምሣሌ
🔹በጃቫ(java)
public class ethio technology {public static void main(String [ ]args)}
💻
🔹በፓይተን (phyton)
print ('hello members')
hello members 💻
በምሣሌው እንደተጠቀሠው በጃቫ 3 መሥመር ሢሆን በፓይተን ደግሞ አንድ መሥመር ብቻ በቂ ነው።በመጨረሻም ፓይተንን ለመማር ሶፍት ዌር ዴቨሎፐር መሆን አይጠበቅብንም።ፓይተንን ለመማር ጊዜው አሁን ነው።
ለዛሬ በእዚህ እናበቃለን በቀጣይ በሚኖረን ቆይታ ቀጣዩን ክፍል ይዘንላቹ እንመጣለን እሥከዛው ግን መልካም ጊዜ።
@techzone_ethio
@techzone_ethio
>>Click here to continue<<