TG Telegram Group & Channel
Sime Tech | United States America (US)
Create: Update:

ለጃፓን አዲስ ደሴት ያስገኘው የገሞራ ፍንዳታ
*****************
- በጃፓን ከውሃ ስር ፈንቅሎ የወጣ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ አዲስ ደሴት አስገኝቷል፡፡ ጃፓን ወደ 6852 የሚደርሱ ደሴቶች እንዳሏት ይነገራል፡፡ በያዝነው ሳምንት የተሰማው መረጃ እንደሚያመለክተው ጃፓን ያሏትን ደሴቶች ቁጥር በአንድ ከፍ የሚያደርግ የውሃ ውስጥ እሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከስቷል፡፡ ፍንዳታው ከቶኪዮ 745 ማይሎች ርቀት ላይ አይዎ ጂማ ከሚባለው ደሴት አቅራቢያ የተከሰተ ነው፡፡

ፍንዳታው በተከሰተበት ወቅት 15 ኪሎ ሜትር ያክል ርቀት ላይ ከፍተኛ የእንፋሎት ጭስ ተስተውሏል፡፡ አሁን ላይ ጨቅላዋ ደሴት አንድ ኪሎ ሜትር መጠነ ዙሪያ ያላት ሲሆን የጃፓን ሜቴዮሮሎጂ ኤጀንሲ ፍንዳታው አሁንም ያልተቋረጠ በመሆኑ መጠኑ ሊጨምር እንደሚችል መረጃ አውጥቷል፡፡

ይህ በገሞራ ፍንዳታ ምክንያት የተፈጠረ አዲስ ደሴት በጃፓን ደቡባዊ ጽንፍ የተፈጠረና ከጃፓኑ ኦጋሳዋራ ደሴትና በቻይናው ቦኒን ደሴት መካከል የተፈጠረ በመሆኑ ጃፓንን የግዛት ማስፋፋት ጥያቄ ውስጥ ሊከታት ይችላል ተብሏል፡፡ በመሆኑም በአካባቢው የሚገኙ ሚዲያዎች ደሴቱን እንደ ጥሩ እድል አልቆጠሩትም፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በ1904፣ 1914 እና 1986 የነበረን የታሪክ አጋጣሚን በመጥቀስ አንዳንዶች አዲሱ ደሴት ከጥቂት ቆይታ በኋላ ሊሰወር ይችላል የሚል ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ በተጠቀሱት አመታት በገሞራ ፍንዳታ ምክንያት አነስተኛ ደሴቶች በጃፓን ተፈጥረው የነበረ ቢሆንም ሁሉም ከቆይታ በኋላ ተሰውረዋል፡፡

መሰወር ብቸኛ ታሪክ እንዳልሆነ ደግሞ በ2013 የተፈጠረውና በአካባቢው ካለው ደረቅ መሬት ጋር በመጋጠም ለአለማችን ስኖፒ የተባለ ደሴትን ያስገኘውን አጋጣሚ ማስታወስ በቂ ነው፡፡

ምንጭ iflscience
════❁✿❁ ═══════ 🎮♦️. @simetube
🎯♦️. @simetube
🚀♦️. @simetube

@simetube
📣 የ Technology ቻናላችንን ለመቀላቀል👇👇
@simetube
@simetube

#ሁሌም_ከኛ_ጋ_ወደ_ፊት 🏃🏃‍♀
══════❁✿❁════════
◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦
◈◂▴△ @simetube▽▴▸◈
🅣🅔🅒🅝🅞🅛🅞🅖🅨

>>Click here to continue<<

Sime Tech

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)