በህይወታችን ከፍ ያለ ቦታ ለመገኘት ትናንሽ ደረጃዎችን መውጣትና መሰናክሎችን ማለፍ ያስፈልጋል!
እሾህ የሌለው መሬት እንቅፋት የሌለው ሂወት የለም እና ሁሉንም በትዕግስት እንለፍ...
የሰውን ልጅ ቀና የሚያደርገው ትራስ ሳይሆን ጊዜ ነው!!! ሁሌም ቢሆን ፈገግ በል ምክንያቱም ለአንተ እንባ ማንም ሰው ግድ የለውምና !
ከፈጣሪህ በቀር በማንም ላይ ተስፋ አታድርግ አብዛኞቹ ሰዎች በምታስፈልጋቸው ስዓት እንጂ በሚያስፈልጉህ ስዓት አይገኙም
መቼም ቢሆን ተስፋ እንዳትቆርጥ በዝግታም ቢሆን ተራመድ እንጂ በፍፁም ወደ ኋላ እንዳትመለስ።
ወድቆ የሚነሳ ወድቆ ከማያውቅ እጅግ ጠንካራ ነው። ትልቁ የጦርነት ሥፍራ አእሞሮ ነው ትልቁ ድል ደሞ ራስን ማሸነፍነው::
ፈጣሪ ለእናንተ የከፈተውን በር ማንም ሰው መዝጋት አይችልም! ካሳለፍነው የሚመጣው የተሻለ ይሆናል !
ይህ የዛሬ መልክቴ ነው ፈጣሪ ለሀገራችን ሰላም ለኛ ጤና ይስጠን። @Teke_Man ነኝ ስትስቁ ዋሉልኝ!!
>>Click here to continue<<