TG Telegram Group & Channel
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ | United States America (US)
Create: Update:

ክፍል 19

ሃዘንን መቋቋም የሚያስችሉ ዘዴዎች

በህወታችን ውስጥ ትልቅ ቦታ የምንሰጣቸው እና መልካም አቀጣጫን በመጠቆም ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱልን ሰዎች አሉ ይኖራሉም፡፡ የቤተሰብ አባል ፤ የልብ ጓደኛ ወይም አርአያ የሆኑን በልባችን አግዝፈን የምናያቸው ምግባራቸው ያስከበራቸው ሰዎችን ለምሳሌ ያህል መጥቀስ ይቻላል፡፡ በመወለድ ወደ ህይወት መምጣት እንዳለ ሁሉ የማይቀረው ህልፈተ ህይወት አለና በሞት ሲለዩን የሚሰማንን የቅስም መሰበር፤ የቁጭት፤ የጥፋተኝነት ፤ የጸጸት፤ የንዴት፤ የናፍቆት አልፎ ተርፎም የመንኮታኮትና የውድቀት ስሜት በግርድፉ ለማጠቃለል ያህል የሃዘን ስሜት ብለን እንጠራዋለን፡፡ የሰው ልጅ እንደ ጸባዩ ይህንን የሃዘን ስሜት የሚያመጡበት ገጠመኞችና ሁኔታዎች የተለያዩ ሲሆኑ የስሜቱም ጥልቀት እና ቆይታ ጊዜ የዚያኑ ያህል ይለያያል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የሃዘን ስሜትን መቋቋም የምንችልባቸውን ጥቂት ዘዴዎችን እንመለከታለን፡፡

1. የሃዘን ስሜትን አለመካድ

የገባንበትን የሃዘን ስሜት መወጣት እንዳንችል ወደኋላ ወጥረው ከሚያሰቃዩን ስሜቶች ውስጥ አንዱ የሃዘን ስሜትን መካድ ነው፡፡ የገባንበትን መጥፎ ስሜት መካድ ከስሜቶቹ ጋር ያለንን ቆይታ ያረዝመው ይሆናል እንጂ እንድንላቀቃቸው አያግደንም፡፡ ስለዚህም ምንም እንኳን ከማንም እና ከምንም በላይ እናፈቅራቸው ነበረ ቢሆንም ላናገኛቸውና ላይመለሱ እንደተለዩን አምነን ባንወደውም የሚደርስብን ሃዘን መቀበል ከስሜቱ መላቀቅ እንድንችል ይረዳናል፡፡

2. ጠንካራ ነኝ እቋቋመዋለው ብሎ እራስን አለማታለል

አብዛኛውን ጊዜ አሉታዊ የሆኑ ስሜቶችን በመቋቋም ለማለፍ “ዋጥ” አድርገን ለማለፍ ስንጣጣር የባሰ እራሳችን ላይ ከሚደርስብን የመንፈስ ስብራት አልፎ የእንቅልፍ ማጣት፤ የምግብ ፍላጎት መዛባት፤ የድብታ ችግር፤ እንዲሁም ሌሎችንም ሊያመጣብን ይችላል፡፡ ስለዚህም ተመራጭ የሚሆነው የሚሰማንን ስሜት ለመቋቋምና ለመከላከል ከመሞከር ይልቅ ስሜቱን እንደ አመጣጡ መቀበል ስላጣነው የህይወት አጋር ስንል እራሳችንን ካለንበት የስሜት ዝቅታ ማንሳት እንድንችል ለእራሳችን ዕድል ልንሰጠው ይገባል፡፡

3. የሃዘን ስሜትን ገልጾ ማውጣት ስለስሜቱ ከሌሎች ጋር መነጋገር

ብዙዎች የወዳጃቸውን የማጣት ስሜት አውጥተው ከመናገር ይልቅ በውስጥ አምቆ መብሰልሰልን እንደ አማራጭ አድርገው ይይዛሉ፡፡ ይህ ግን ስሜቱን ያለረዳት ብቻችንን በጫንቃችን ተሸክመን ለመጓዝ እንደ መሞከር ነውና የመድከምና የመሰላቸት ስሜት ይፈጥርብናል፡፡ የሆዴን በሆዴ ለሃዘን ስሜት አይሰራምና ለትዳር አጋራችን፤ ለቤተሰባችን፤ ለልብ ጓደኞቻችን ወይም ደግሞ ለስነ-ልቦና ባለሞያዎች የተሰማንን ስሜት በመናገር፤ በመጻፍ፤ ስዕል በመሳል ወይም በማንኛውም ችሎታችን በሚፈቅደው መንገድ መተንፈስ የሃዘንን ስሜት ይቀንሳልና ስሜታችንን ገልጾ ማጋራት ጥሩ አማራጭ ነው፡፡

4. ታጋሽ መሆን

የሃዘን ስሜቱ ከባድነት የተነሳ ብዙውን ጊዜ በሞት የተለየንን ግለሰብ የሚያስታውሱንን ነገሮች ለማራቅ እንሞክራለን፡፡ ስሜቱን ያራቅነው እየመሰለን ይጠቀሙበት የነበሩ ንብረቶችን ማራቅ፤ መኖርያ ቤታችንን መቀየር፤ የስራ ቦታችንን መቀየር፤ እንደው በአጠቃላይ እንደ ፎቶ ያሉ ትዝታ የሚቀሰቅሱ ንብረቶችን ለማስወገድ አለመቸኮል ጥሩ አማራጭ ነው፡፡ የሃዘን ስሜቱም ካለፈ በኋላ የእነዚህ ንብረቶች መኖር ያጣናቸውን ግለሰቦች በመልካምነት እንድናስባቸውና እንዳንረሳቸው፤ ለእኛ የነበራቸውን ፍቅር እና አክብሮት እንድናስታውስ ይረዱናል፡፡

5. የጤናችንን ጉዳይ ቸል አለማለት

ሰዎች በሃዘን ጊዜ እራሳቸውን ይጥላሉ፡፡ ለእራሳቸው ያላቸው ክብር፤ እንክብካቤ ከመቀነስም ባለፈ እራሳቸውን በረሃብ ይቀጣሉ፡፡ የምናደርጋቸው ማናቸውም ድርጊቶች ያጣነውን ግለሰብ አይመልሱምና የጤናችንን ጉዳይ ቸል ልንለው አይገባም፡፡ የምናስበውን ያህል የምግብ ፍላጎት ባይኖረን እንኳን ምግብ መመገብ ይገባናል፡፡ ያጣናቸው ሰዎች በህይወት ቢቆዩ እንዲህ እንድንጎሳቆል እንደማይፈልጉ ለእራሳችን ደጋግመን ልንነግረው ይገባል፡፡

6. የሃዘን ስሜትም ያልፋል

በሃዘን ስሜት ውስጥ ስንሆን አብዛኛዎቻችን ስሜቱ የማይላቀቅና ሽሮ የማያልፍ አድርገን እንስለዋለን፤ ይመስለናልም፡፡ የፈጀውን ያህል ቢፈጅ የሃዘን ስሜት ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን እየቀነሰ የሚመጣ ነው፡፡ መዘንጋት የሌለብን መኖር ማለት አሉታዊ ስሜቶችን ሳይሰሙን ተንደላቀን የምንፈላሰስበት ሳይሆን ተጋፍጠንና ተቋቁመን የምናልፍበት ነው፡፡ በህይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙን ማናቸውም ነገሮች የሚያልፉ መሆናቸውንና ህይወት የሚቀጥል መሆኑን ልናስተው ይገባል፡፡

በአጠቃላይ ጊዜ የማይሽረው ነገር የለምና ለማንነታችን ሃቀኛ በመሆን ካጋጠመን የተጠበቀ ይሁን ድንገተኛም የሃዘን ስሜት በመቋቋም ማንነታችንን ልንመልስ ይገባል፡፡

©(በዘመነ ቴዎድሮስ zepsychologist)
@Psychoet

>>Click here to continue<<

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)