TG Telegram Group & Channel
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ | United States America (US)
Create: Update:

ክፍል 18

በአዲስ መልክ ስራ ጀምረናል

ብዙውን ጊዜ ይህን ማስታወቂያ የምንመለከተው በምግብ ቤቶች ላይ ነው፡፡ ገበያቸው ሲቀዘቅዝ፤ ደንበኞቻቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ ሲመናመኑና መክሰር ወደሚባለው ደረጃ ላይ ሊደርሱ ሲሉ ለተወሰነ ቀናት ወይም ሳምንታት አገልግሎት መስጠት ያቋርጡና ቤቱን በማደስ አንዳንድ ጭማሪ ነገሮችን በማካተት የቀድሞና አዳዲስ ደንበኞችን ለመሰባብ ሲሉ በአዲስ መልክ ስራ መጀመራቸውን ባነር ወይም የሚታይ ማስታወቂያ ለጥፎ በማብሰር ስራቸውን ይጀምራሉ፡፡

ይህ የሚያመለክተው በህይወት ጉዞ ሁሌ ወደፊት ብቻ ሳይሆን አንዳንዴም ያሳለፍነውን ደስታ፤ መከራና ውጣ ውረድ ዞር ብሎ መመልከት ለዛሬ ማንነት አስተዋጽኦ እንዳለው ለማጠየቅ ነው፡፡

ትናንት ሞክረናቸው ያልሰመሩልን የህይወት ውጥኖችን ተስፋ ባለመቁረጥ በአዲስ ሞራልና ወኔ እንደገና እንሞክረው፡፡ በህይወታችን ውስጥ በአዲስ መልክ መጀመር ያለብን ነገሮች ምንድን ናቸው?

ትዳራችን እንዴት ነው?

አንቺ ትብሽ እኔ እብስ ተብሎ የተጀመረ ነገር ሁሉ በጊዜ እርጅና ይፈዛል አልፎ ትርፎም ቀለሙ ይወይባል፡፡ ትናንትና የነበረው ፍቅር፤ መረዳዳት፤ መከባበር፤ መደማመጥና ትዕግስት በጊዜ ሂደት ጠፍቶ ሊሆን ይችላል፡፡ በተጣማሪዎቹ መካከል አንደኛው ወይም ሁለቱም የመጠቃት ስሜት እየተሰማቸው ሊሆን ይችላል፡፡ እስቲ የቀደመውን ጊዜ ፍቅርና መልካምነት በማሰብ የዛሬ መጠቃትንና የመገፋት ስሜትን ለአንድ አፍታ በመተው ትዳራችሁን/ፍቅራችሁን እንደ ገና በአዲስ ምዕራፍ ለመጀመር ሞክሩት፡፡ በትዝታ ብቻ የቀረው ፍቅራችሁና የትዳራችሁ መልካምነት ወደ ቀደሞ ክብሩ ይመለሳል፡፡ ግድ የላችሁም ከቻላችሁ ሁለታችሁም ይህ የማይቻል ከሆነ አንዳችሁ በመጀመሪያ ኃላፊነት በመውሰድ ትዳራችሁን/ፍቅራችሁን እንደገና ስሩት፤ በውጤቱ ትደነቃላችሁ፡፡

ማኅበራዊ ህይወታችሁ?

ማኅበራዊ ህይወት መልካም እንደሆነ ሁሉ አንዳንዴ ባልተፈለገና ባልተጠበቀ አቅጣጫ ያመራና ከወዳችነት መንፈስ ወደ ጠላትነት የመሸጋገር ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ አንዱ በዳይ ሌላኛው ደግሞ ተበዳይ ሆኖ በአንጀት መቆሳሰል የግንኙነት ሰንሰለቱ ተበጣጥሶ ይሆናል፡፡ የተራራቃችሁትና የተቆራረጣችሁት ሰው ምንም እንኳን ቢያጠፋና ቢበድል በህይወታችሁ አስፈላጊ ነው ብላችሁ የምታምኑት ዓይነት ሰው ከሆነ እስቲ አንድ ዕድል ስጡትና ማኅበራዊ ህይወታችሁን በማደስ እንደገና ሞክሩት፡፡

ስራችሁስ?

በግልም ይሁን ተቀጥራችሁ በምትሰሩት ስራ ውጤታማና ተሸላሚ ለመሆን ብዙ ርቀት ተጉዛችሁ ፤ ለፍታችሁ፤ ወዛችሁን አሟጣችሁ በስተመጨረሻም የልፋታችሁ ውጤት ሲታይ ትርፍና ኪሳራው እንደማይታወቅ ነጋዴ ዓይነት ሆኖባችሁ ይሆናል፡፡ ዛሬ ላይ ቆም በሉና ሌሎቹ ሲሳካላቸው እኔ ያልተሳካልኝ ምክንያት ምንድን ነው ብላችሁ በመጠየቅ በአዲስ መንፈስና ወኔ ጀምሩት፡፡ እስቲ በትናንትናው ጅምርና ልምድ ሳይሆን በሌላ አተያይ ችግራችሁ ምን እንደነበር ለመፈልፈል ጥረት አድርጉ፡፡ ከዚያ በአዲስ መልክ ስራችሁን ጀምሩ በእርግጠኝነት ይሳካላችዋል፡፡

አመለካከታችሁ?

ለዘመናት ሰው ለምን ይጠላኛል ብላችሁ እራሳችሁን በሃዘን፤ በትካዜ እንዲሁም እራስን ከማኅበራዊ ህይወት እስከ ማግለል ደርሳችሁ በብቸኝነት ስሜት እየተገረፋችሁ ሊሆን ይችላል፡፡ ግድ የለም ሰው ለምን ይጠላኛል ሳይሆን የሚጠላብኝ ነገር ምንድን ነው ብላችሁ እራሳችሁን ፈትሹ፡፡ አንዳንዴም ሌላው ሰው ምንም ሳይለን እኛው እራሳችን በምንፈጥረው ምክንያት የለሽ አስተሳሰብ ሌሎች እንደሚጠሉን ልናስብ እንችላለን፡፡ አእምሮአችሁን በአወንታዊ አስተሳብ በመገንባት ስለእራሳችሁ ጥሩ ምልከታ ይኑራችሁ፡፡ ከዚያ ሁኔታዎችን እንደ አመጣጣቸው በአዲስ መልክ ለመመለስ ሞክሩ ፤ ደስታንም ታገኛላችሁ፡፡

ተስፋ መቁረጥ ይታይባችዋል?

ሁሉም ነገር በእናንተ ተቃራኒ የሚሄድ ከሆነ እናንተ እራሳችሁ የተሳሳታችሁት ነገር ሊኖር ስለሚችል ቆም ብላችሁ እራሳችሁን መርምሩ፡፡ ትናንት ብትወድቁና ባይሳካላችሁ ዛሬ ደግሞ ሌላ ቀን ነው እንደገና ሞክሩት፡፡ ከአይሳካልኝም፤ ይሳካልኛል፤ ከአልችልም እችላለሁ፤ ሁሉም ነገር ጨለማ ነው ብሎ ከማሰብ ከጨለማው በኋላ ጽልመቱ በብርሃን ጸዳል ይገፈፋል ብሎ ማሰብና አዲስ ተስፋ መሰነቅ፡፡ ህይወት ሎተሪ ናት ደጋግመህ ሞክራት ይባል የለ፤ ተስፋ ባለመቁረጥ ጉዞአችሁን አንድ በማለት እንደገና ጀምሩት፡፡

ሱሰኝነት?

አዲስ ዓመትና አዲስ ቀን በመጣ ቁጥር ከሱስ ለመገላገል ለእራስችሁ ቃል በመግባትና ምሎ በመገዘት ጥራችሁ ጥራችሁ ወደ ምትጠሉት ወጥመድ ትብታብ ውስጥ ወድቃችሁ ይሆናል፡፡ ትናንትና ሱስን ለመተው በመጀመሪያ አእምሮአችሁን ሳታሳምኑ ቀጥታ ድርጊቱን በመተው ጀምራችሁ ይሆናል፡፡ ዛሬ ግን መጀመሪያ እንደምትችሉ  አእምሮችሁን አሳምኑ ከዚያ ድርጊቱን በአንዴ ሳይሆን ቀስ በቀስ ለመተው በአዲስ አስተሳሰብና መንገድ ጀምሩት፡፡ በእርግጠኝነት መድረስ ወደ የምትፈልጉበት ቦታ ላይ እንዳትደርሱ እንቅፋት ሆኖ የሚይዛችሁ ነገር የለም፡፡ ከእናንተ የሚጠበቀው ቁርጠኛ መሆን ብቻ ነው፡፡

በአጠቃላይ በህይወት መንገድ ሁሌ ወደ ፊት ብቻ መሄድ ሳይሆን አንዳንድ ጊዜ ከተነሱበት የህይወት አቅጣጫ እራስን ዞር ብሎ በመመልከት እንደገና እንደ አዲስ የሚጀመሩ ምዕራፎች አሉ፡፡ ስለዚህ በህይወቴ ይህንና ያንን አጥቻለው ብላችሁ የምታምኑትንና እንደገና ለማግኘት የምትመኙት ነገር ካለ ያለማቅማማት ህይወትን በአዲስ መልክ ጀምሯት ይሳካላችዋል፡፡

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)
©Zepsychology
@psychoet

>>Click here to continue<<

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)