TG Telegram Group & Channel
FŰŇ_ŽØÑĘ 😂😱 | United States America (US)
Create: Update:

⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙
.
ደራሲ ሲራክ
.
⚀ ክፍል አስራ ስድስት⚀ 1⃣6⃣

.
ትርሃስ ዘንድሮ የ10 ክፍል የሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ስለሆነች ከእኔም ሆነ ከፍሌም ጋር የመገናኘታችን እድል የጠበበ ነበር።
አንድ ቅዳሜ ጠዋት ህይወታችንን ያመሰቃቀለ ነገር ተፈጠረ።
ቀኑ ቅዳሜ ጠዋት ነበር። እስከ አምስት ሰዓት ተምረን ቤት ስገባ ቤቱ ጭር ብሏል። እየተጣራው ገባሁ። ቤት ስገባ ደስ ብሎኝ ነበር የገባሁት እኔና ፍሌም የሁለተኛ መንፈቅ አመት ከጀመሩ በፊት ባለችው የእረፍት ጊዜ ድሬ እንደምትወስደኝ እና ከእናት አባቷ ጋር እንደምታስተዋውቀኝ ከክፍል ስወጣ ነግራኝ ነበር።
ደስ ብሏታል። ስለእኔም ብዙ ነገር እንደነገረቻቸው ጨምራ አውግታኛለች።
ፍትት ብዬ እናቴን እየጠራዋት ኩሽና ስገባ እናቴ ሽንኩርት እየላጠች ነበር።
" እማ እንዴት ዋልሽ?" አልኳት ጉንጯን አጥብቄ እየሳምኩ።
" እንዴት ዋልክ ጌቱ!" ብላ በተራዋ ግንባሬን ሳመችኝ። (ጌታዬ ጌቱ የኔ ጌታ እያለች ነው የምትጠራኝ።) የኤሌክትሪክ ምድጃውን ለኩሳ ውሃ እስክትጥድ ሽንኩርቱን እከትፍላት ጀመር።
"እማ! ሚሚዬ የት ነች ?" አልኳት ሽንኩርቱ እያቃጠለኝ ከአይኔ የሚወጣውን እምባ በአይበሉባዬ እየጠረግኩ።
"መቼ ከትምህር ቤት መጣች ብለህ ነው ጌታዬ!?" አለች። ለወጥ የሚሆን ቲማቲም እየመረጠች።
"ናፈቀችኝ እኮ እማ ! አይ ትርሃሴ" አልኳት
"ምን ጭቅጭቋ ነው የሚናፍቅህ አይ እናንተ! እንደው ጌታዬ እናንተ ባትኖሩ ምን እሆን ነበር ቸሩ መድሃኒያለም ጥሎ አልጣለኝም ቤቴን በፌሽታ ሞላችሁት እኮ!" አለች በእናታዊ የመንሰፍሰፍ ሀዘኔታ ባለው ድምፅ ቲማቲሙን አምጥታ ከፊት ለፊቴ እያስቀመጠች።
"እማ ዛሬ ደስ ብሎኛል የሆነ የምነግርሽ ነገር አለኝ። አንቺም ደስ እንደሚልሽ አልጠራጠርም!" አልኳት።
"አድርጎት ነው የኔ ጌታ አንተ ብቻ ደስተኛ ሁንልኝ እንጂ ደስ ያለህ ነገር እኔንም ደስ ያሰኘኛል።"ብላ መጥታ በስስት ጉንጬን ሳመችኝ።
ስልኬ ላይ የሆነ ነገር ላሳያት ብዬ ስልኬ እኔ ጋ እንዳልሆነ ኪሴን ዳብሼ ስረዳ ከደብተሬ ጋር ሳሎን እንደተውኩት ገባኝና እናቴን "መጣው እማ!" ብዬያት ወደ ሳሎን አቀናው።
ስልኬን ይዤ ልመጣ ስል ባትሪ ዘግቶል። ከቻርጀር ጋር ኩሽና ሰክቼ ከእናቴ ጋር ማውራቴን ቀጠልኩ።
"እማ ምነው ትርሃሴ ቆየች!? " አልኳት ቻርጀሩ መቀበል አለመቀበሉን እያረጋገጥኩ።

ክፍል አስራ ሰባት ይቀጥላል........

ደራሲ C-ራክ
comment ፦ @Abdsewanted

መልካም ቀን

"SHARE" @ONLYZEGET

>>Click here to continue<<

FŰŇ_ŽØÑĘ 😂😱

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)