TG Telegram Group & Channel
FŰŇ_ŽØÑĘ 😂😱 | United States America (US)
Create: Update:

⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙
.
ደራሲ ሲራክ
.
⚀ ክፍል አስራ አምስት ⚀ 1⃣5⃣

"ብቻሽን ነበርሻ! ይህን ሁሉ ጊዜ?..."አልኳት።
" ታዲያ ምን ምርጫ አለኝ ደጋግሜ ቤት አንተጋ ብመጣ የለም ይሉኛል። መሄጃ ሲጠፋኝ ተኝቼ እውላለሁ!" አለች ትክዝ እንዳለች።
በነገረችኝ ነገር በእራሴ አዘንኩ የራሴን ስሜት እየሰማሁ ለካስ ፍሌሜን ጎድቻታለሁ ብዬ ተፀፀትኩ። ግን ፍሌም ይህን ያህል አድርጌያትም አልተለወጠችብኝም።
ምንም በልቧ የለም። ንፁህ ነች። ልቧን አደነቅኩላት ፤ ይበልጥ ስወዳት ተሰማኝ።
ይህቺ ፍካት ህይወቴን አጥርታ እኔነቴን አፈካችው። ልቤ ወገግ ሲል ይሰማኛል።
ፍሌም የሰው ወርቅ!
በድብስብስ ቀን ያገኘዋት ፀሀይ በድብስብስ አለም የታደልኳት ጎህ ፍሌም።
የብቻዬ ነች ብዬ ለልቤ ነገርኩት።
ሰማይና ምድሬ ነች።
ቀኑ ደንገዝገዝ እያለ ነበር በአዌቱ ውሃ እንደ ህፃን ልጅ ፊቷን አጥቤ ወደቤት ወሰድኳት።
................. #########..................
እንደዋዛ ትምህርት ተጀምሮ መንፈቅ አመት ሊሆነው ምንም አልቀረም። እኔና ፍሌም ያለውን ነገር ተነጋግረን እዚህ ለመማር ከወሰነች ወዲህ መንቲና በሚገኘው የጅማ ሁለተኛ ደረጃ መሰናዶ ት/ቤት እሷ 11ኛ እኔ የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪ ሆነን እየተማርን ነው።
ዘውትር ተሳስበን እና ተዋደን ነው የምንኖረው። ትምህርት ቤት ስንሄድም ሆነ ስንመጣ አብረን ነን ተነጣጥለን አናውቅም።
እሁድ እሁድ ሁሌም ማምሻውን በጀምበር መጥለቂያ ደርብ ላይ ወጥተን ጀምበርን እያጠለቅን እናወጋለን።
በየካፌውና ሬስቶራንቶች ላይ እየተዟዟርን በትምህርት በኑሮ የተጨናነቀ መንፈሳችንን እናድሳለን። እኔም ሆንኩኝ ፍሌም በእጅጉ ደስተኞች ነን።
ትርሃስ ዘንድሮ የ10 ክፍል የሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ስለሆነች ከእኔም ሆነ ከፍሌም ጋር የመገናኘታችን እድል የጠበበ ነበር።

ክፍል አስራ ስድስት ይቀጥላል........

ደራሲ C-ራክ
comment ፦ @abdsewanted

"SHARE" @onlyzeget

>>Click here to continue<<

FŰŇ_ŽØÑĘ 😂😱

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)