TG Telegram Group & Channel
FŰŇ_ŽØÑĘ 😂😱 | United States America (US)
Create: Update:

⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙
.
ደራሲ ሲራክ

⚀ ክፍል አስራ አራት ⚀ 1⃣4⃣

🔅 ከእሷ በቀር በወጉ የሚረዳኝ ሰው እንደሌለ ውስጤ ያውቃል።
"ግሩሜ ፍሌም እኮ ነኝ ለምን የሆንከውን አትነግረኝም"አለችኝ ወደ አንገቷ ስር ጎትታ እያቀፈችኝ።
"የኔ ጌታ ከምልህ በላይ ናፍቀኸኛል። እየሸሸከኝ እንደሆነ ይሰማኛል። ግሩሜ እንደምታፈቅረኝ አልጠራጠርም። እኔ በጣም ነው የምወድህ። እኔ የማስበው ፍቅር ለመስጠት እንጂ ለመቀበል ቦታ እንደሌለው ነው። ለዚህም ነው አንተን አጥሮ ያገደኝን የስሜትህን ኬላ አፍርሼ የምወተውትህ። አንተን ስለማፍቀሬ እንጂ አንተ ለእኔ ስለምትሆንልኝ ነገር እየተነበይኩ ልረብሽህ አልሻም። ዛሬ ይህን ያህል ጊዜ ስንራራቅ ለምን አልፈለግከኝም ብዬ ማኩረፍ ነበረብኝ። ግን ማፍቀሬ ስለመስጠት እንጂ ስለመቀበል አላደላም።

ግሩሜ የኔ የፍቅር ስሌት
1+1 = 2 ሳይሆን 1+1= 1ነው።

ምክኒያቱም የኔ እና የአንተ ፍቅር ተደምሮ ሁለት የሚባል ፍቅርን አይሰጠንም። ግሩሜ መቀበልን ስታስብ ነው 1+1=2 የሚሆነው።
አንተ እንዲደመር መስጠት እንጂ ድምሩ ሁለት ሆኖ ካላየሁ ብለህ ግብግብ መግጠም የለብህም። አንድ ቀን ሳታስበው በውጤቱ ትደሰታለህ።"
አለችኝ ይህን ስትለኝ አልቻልኩም ሆድ ባሰኝ ከእቅፏ ውስጥ ተሸሽጌ ተንሰቀሰቅኩኝ። ገና ልነግራት የፈለግኩትን ነገር ቀድማ ትነግረኛለች። በግልፅነቷ ብቸኝነቴን ታሸሽብኛለች። ከሰው በቀደመ አድማስ ሰፊነቷ ጭንቀቴን ታባርልኛለች። ፍሌም የሰው ወርቅ! ሰው የመሆን ልክ!
ለፍሌም የሆንኩትን ሁሉ ፍርሃቴን ሳይቀር በግልፅ ምንም ሳልደብቅ ሁሉንም ነገር ነገርኳት ፍሌም ደስ አላት። ከቁዘማ አለሟ ወጥታ ተፍነከነከች።
ይሄ ደስታዋን እናቴ እንድታይ ተመኘሁ።"ፍሌሜ ለምን እናቴ ጋ ቤት ሄደን ትንሽ ተጫውተን አትሄጂም?" አልኳት የአፍንጫዋን ጫፍ በእጄ ጎተት ጎተት እያደረግኩ።
"እሺ እዛ ቤት ሁሉም ሰው ነው የናፈቀኝ። በተለይ የትርሃስ ንጭንጭ።" አለች "እሺ አላቆይሽም ቶሎ እሸኝሻለሁ" አልኳት።
"ፈቅደውልኝ እንኳን አብሬያችሁ ባደርኩ!"
"እ..ህ አጎትሽስ?" አልኳት
"ፊልድ ከወጣ ሁለት ሳምንቱ ነው። እኔ እና አንተ ከተጠፋፋን ጀምሮ እንደሄደ አልመጣም" አለች ቅር እያላት። "ብቻሽን ነበርሻ! ይህን ሁሉ ጊዜ?"አልኳት።
ታዲያ ምን ምርጫ አለኝ ደጋግሜ ቤት አንተጋ ብመጣ የለም ይሉኛል።መሄጃ ሲጠፋኝ ተኝቼ እውላለሁ!" አለች ትክዝ እንዳለች።

ክፍል አስራ አምስት ይቀጥላል........

ደራሲ C-ራክ
comment ፦ @ABDSEwAnTED

"SHARE" @ONLYZEGET

>>Click here to continue<<

FŰŇ_ŽØÑĘ 😂😱

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)