" ከ4 ክልሎች ተጨማሪ 8,080 ተማሪዎች ምደባ ያገኛሉ "
የትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ይፋ ካደረገው ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ይገባሉ ካላቸው 152,014 ተማሪዎች በተጨማሪ 8 ሺህ 80 የሚሆኑ ተማሪዎችን ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲ እንደሚመድብ አሳውቋል።
ምንም እንኳን ጦርነት ሁሉንም ክልሎች በተወሰነ ደረጃ ተፅእኖ ቢያሳድርባቸውም ነገር ግን በተለየ ሁኔታ በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የነበረው ሁኔታ በልዩነት እንዲታይ ተደርጓል።
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተጠቀሱት አራቱ ክልሎች ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያቸው ፥ " የጦርነት ስሜት የፈጠረው ነገር ተማሪዎችን ጎድቷቸው እንደሆነ አስተያየት የሚደረግበት መንገድ እንፈልግ በሚል የክልል ትምህርት ቢሮዎች ተስማምተው ለትምህርት ሚኒስቴር የሰጡት ስራ አስተያየት የሚደረግበት ሁኔታ ካለ እንዲፈለግ " የሚል እንደነበር አስረድተዋል።
በዚህም ፥ በፊት ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ ከተቆረጠው ቁጥር 152 ሺ ተጨማሪ የሚገኝ ቁጥር ካለ ታይቷል ሲሉ ገልፀዋል።
በተለይም ፥ ከትግራይ ክልል መጥተው አራተኛ ዓመት ጨርሰው የሚወጡ ተማሪዎች ስለሚኖሩ የቅበላ ቦታዎችን ማግኘት ይቻላል በሚል ስራ ላይ ያሉት 43 ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን አቅም አሟጠው ወደ 8,080 ተማሪዎች የቅበላ ቦታ እንዳሳወቁ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
የተገኘውን የተማሪ ቅበላ አቅም በፍትሃዊነት ለ4ቱ ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት በተጎዱ ተፈታኞች መጠን እንዲከፋፈል መወሰኑንም አሳውቀዋል።
ምንም እንኳን የተገኘው የቅበላ ቦታ ለ4ቱ ክልሎች ይከፋፈላል ቢባልም በምን አግባብ እና መንገድ ተማሪዎቹ እንደሚለዩ እስካሁን በግልፅ የተብራራ ሆነ የታወቀ ነገር የለም።
@minesterofeducation
>>Click here to continue<<