የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ከ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ጋር በተያያዘ በኢፌዲሪ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የቀረበበትን አቤቱታ እንደማይቀበለው ማምሻውን አስታውቋል።
የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ማምሻውን ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ከ12ኛ ክፋል ፈተና ጋር ተያይዞ የፈተናው እርማት ላይ ችግር ተፈጥሯል በሚል የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት የለውም። ይህንንም በተጨባጭ ያረጋገጥነው በመሆኑ አስተራረም ላይ የተፈጠረ ሥህተት የለም ብለዋል።
ስህተት የተፈጠረው ፈተናው በሁለት ዙር የተሰጠ ከመሆኑና የመረጃ ቋቱም አንድ ላይ የተቀመጠ ስለሆነ ውጤት አገላለጽ ላይ መረጃ ሲወሰድ የተወሰነ ሥህተት ተፈጥሯል። ይህንንም በቀረበ ቅሬታ መሰረት ኤጀንሲው ማስተካከሉን ነው አቶ ተፈራ የገለጹት። ከ20 ሺህ በላይ ቅሬታ በኦንላይ እና በአካል ተቀብሎ የማጣራት ሥራ መስራቱን የጠቀሱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ በኦንላይን የቀረቡ አቤቱታዎች አልታዩም የሚለውን ክስም ሥህተት ነው ሲሉ አብራርተዋል።
ከመግቢያ ነጥብ ጋር በተያያዘ ያለው ቅሬታ እንደማይመለከታቸውና ጉዳዩ የትምህርት ሚኒስቴር መሆኑንም አቶ ተፈራ ገልጸዋል።
የኢፌዲሪ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከተማሪዎች የቀረቡ አቤቱታዎችን መሠረት በማድረግ ባደረገው ማጣራት ስህተት መፈጠሩን፤ ቅሬታ አመላለስ ላይም ችግሮች መኖራቸውን ማረጋገጡን አስታውቋል። #ኢትዮመረጃ
@minesterofeducation
>>Click here to continue<<