#MoE
ወደመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመግቢያ የመቁረጫ ነጥብን በተመለከተ በርካታ ጥያቄዎችን ልካችኃል።
እኛም ጉዳዩን ችላ አላልነውም።
በዛሬ ዕለት ከመቁረጫ ነጥብ ጋር በተያያዘ ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ ያቀረብን ሲሆን እስካሁን የመቁረጫ ነጥብ እንዳልታወቀና የትንተናው ስራ እየተሰራ መሆኑን አሳውቆናል።
መቼ ይፋ ይሆናል ? ለሚለውን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጥያቄም ሚኒስቴሩ በዚህ ቀን የሚል የተቆረጠ ቀን ባይገልፅም ፤ የትንተና ስራው እየተሰራ በመሆኑ ሲጠናቀቅ እንደሚገለፅ አሳውቋል።
ውድ የቲክቫህ አባላት አዲስ መረጃ ሲደርሰን ወዲያው የምንልክላችሁ ይሆናል።
credit-tikvah
@minesterofeducation
>>Click here to continue<<