ከ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ ቅሬታ ያቀረቡ ተማሪዎች ተመሳሳይ እና ለቀረበውም ጥያቄ ትክክለኛ ያልሆነ ምላሽ እንደደረሳቸው ገልፀዋል።
ለቲክቫህ መልዕክት የላኩ ተማሪዎች " ቅሬታችንን በአግባቡ ብናቀርብም ምላሹ ግን በፍፁም ከቅሬታችን ጋር የማይገናኝ ነው " ብለዋል።
የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የቅሬታ አመላለሱን በግለፅ እንዲያስረዳቸው ጠይቀዋል።
ኤጀንሲው ጉዳዩን እንዲከታተል እና ድጋሚ እንዲፈትሽም ጠይቀዋል። ተማሪዎቹ ለቀረቡት ቅሬታዎች ተመሳሳይ መልስ በሲስተም እየተላከ ሊሆን ይችላል ብለዋል።
ተማሪዎች ባነሱት ጥያቄ ላይ ቲክቫህ የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የሚመለከታቸውን አካላት በማነጋገር ማብራሪያ ለማቅረብ ይሞክራል።
በሌላ በኩል ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስገባው የመቁረጫ ነጥብ መቼ ይፋ እንደሚደረግ እንዲሁም የተማሪዎች ምደባ መቼ ይፋ እንደሚሆን ጠይቆ ያሳውቃል።
@minesterofeducation
>>Click here to continue<<