የስድስተኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት በዛሬው እለት ይፋ እንደሚደረግ የመዲናዋ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ
ዕለተ ረቡዕ ሰኔ 25 - 2017 | ሙሐረም 6 -1447
የአዲስአበባ ትምህርት ቢሮ፤ የ2017 የስድስተኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 25/2017 ከሰዓት ይፋ እንደሚደረግ አስታውቋል፡፡ የፈተናው ውጤት ይፋ የሚደረገው የትምህርትቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ነጥቡ ላይ ውይይት ካደረጉ በኋላ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
ቢሮው ከተማ አቀፍ የመልቀቂያ ፈተናው በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ የሚደረገው ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ለማስቻል እንደሆነም ገልጿል፡፡
የ2017 የትምህርት ዘመን የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የተሰጠው ከሰኔ 10 እስከ 12/2017 እንደነበር ይታወሳል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)
★ ★ ★ Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
>>Click here to continue<<