TG Telegram Group & Channel
መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒 | United States America (US)
Create: Update:

ቤትሽ ግድግዳ ላይ
አስቱ✍️
ለእናታቹ 🥰

ቤትሽ ግድግዳ ላይ
ማርያም ልጇን አቅፋ ምትታየው ምስል
ለምን አንደሆነ እንጃ
ቁርጥ እራስሽን አንቺን ስትመስል

[እርግጥ ነው]

እርግጥ ነው ከአናትሽ
የንግስና ተምሳል ዘውድ አልተደፋም
እርግጥ ነው ፀዳልሽ
እንደ እመቤታችን በፍፁም አልፋፋም

ውብ አለባበሷ
ካንቺ ብጫቂ ጨርቅ እየተጣመረ
ድኩም አምሮዬ
ምስጢር ስጦታሽን አየመረመረ
(እአየመዘመረ)

የመለኮት ሀይልሽ
የቱ ጋር እንዳለ ላይገባኝ ቢቀርም
ቤትሽ ግድግዳ ላይ ያለቺውን ማርያም
ሁሌ እንደምትመስይ አልጠራጠርም

ተመልከቻት እሷን
በሀለት እጆቿ ንጉሱን ታቅፋ
ስለክብሩ ብላ አንገቷን ስትደፋ

ተመልከቺ ልጇን
ከበግ ስር እንዳለ ብላቴና ግልገል
ከጡት አፈትልኮ
ከእናት ስር አምልጦ ለመሮጥ ሲታገል

ሁሌም ልሂድ ሲላት አትሂድ ትላለች
እናቱ ናትና ከሄደ በሗላ
ምን እንደሚገጥመው ቀድማ ታውቀዋለች

(አየሽ እኔም ልጅሽ)

የማይጨብጠው ተስፋዬን ጨበጬ
አትሂድ ከሚለኝ ከእቅፍሽ አምልጬ

ግብሬን ሁሉ ስቼ
አንቺን እረስቼ

ያሰርሺልኝ እውነት ማህተመ ከላላ
ስንት ጊዜ ሆነው ስንት ጊዜ ሞላ

አየሽ እኔ ልጅሽ

በኖርኩት ዘመኔ
ልጄ ሆይ ያለችን እንቴን ያልረዳሁ
እምነት የጎደለኝ
ትንቢቴን የፈራሁ ቤቴን ያልተረዳሁ

እዳዬን ፈርቼ
ስቃዬን ፈርቼ መስቀል እየሸሸሁ
በጉብዝናዬ ወር
ቀሽም ቀን ሳሳልፍ ስንት ግዜ አመሸሁ

አየሽ አይደል እማ
ከንቱነት ነው ለካ
እናቱን ማያምን እናቱን ማይሰማ

እውነትም እኔ ነኝ
መንገድም እኔው ነኝ ለራሴ እንዳላልኩኝ
መሄጃው ሲጠፋኝ
አማላጅ ፍለጋ ከእቅፍሽ ላይ ዋልኩኝ

መገመት የሚከብድ ለሀሳብ የረቀቀ
መፍረድ የማይችል ሆድ ክክፋት የራቀ

በዚህ ሁሉ ሽሽት በዚህ ሁሉ ምሽት
እንዴት አልተቆጣ እንዴት አልረገመኝ
እውነት እማማዬ ማርያምን ነው ምልሽ
እቅፍሽ ገረመኝ

ቤትሽ ግድግዳ ላይ
ማርያም ልጇን አቅፋ ምትታየው ምስል
ለምን አነደሆነ እንጃ
ቁርጥ እራስሽን አንቺን ስትመስል

ቤትሽ ግድግዳ ላይ
አስቱ✍️
ለእናታቹ 🥰

ቤትሽ ግድግዳ ላይ
ማርያም ልጇን አቅፋ ምትታየው ምስል
ለምን አንደሆነ እንጃ
ቁርጥ እራስሽን አንቺን ስትመስል

[እርግጥ ነው]

እርግጥ ነው ከአናትሽ
የንግስና ተምሳል ዘውድ አልተደፋም
እርግጥ ነው ፀዳልሽ
እንደ እመቤታችን በፍፁም አልፋፋም

ውብ አለባበሷ
ካንቺ ብጫቂ ጨርቅ እየተጣመረ
ድኩም አምሮዬ
ምስጢር ስጦታሽን አየመረመረ
(እአየመዘመረ)

የመለኮት ሀይልሽ
የቱ ጋር እንዳለ ላይገባኝ ቢቀርም
ቤትሽ ግድግዳ ላይ ያለቺውን ማርያም
ሁሌ እንደምትመስይ አልጠራጠርም

ተመልከቻት እሷን
በሀለት እጆቿ ንጉሱን ታቅፋ
ስለክብሩ ብላ አንገቷን ስትደፋ

ተመልከቺ ልጇን
ከበግ ስር እንዳለ ብላቴና ግልገል
ከጡት አፈትልኮ
ከእናት ስር አምልጦ ለመሮጥ ሲታገል

ሁሌም ልሂድ ሲላት አትሂድ ትላለች
እናቱ ናትና ከሄደ በሗላ
ምን እንደሚገጥመው ቀድማ ታውቀዋለች

(አየሽ እኔም ልጅሽ)

የማይጨብጠው ተስፋዬን ጨበጬ
አትሂድ ከሚለኝ ከእቅፍሽ አምልጬ

ግብሬን ሁሉ ስቼ
አንቺን እረስቼ

ያሰርሺልኝ እውነት ማህተመ ከላላ
ስንት ጊዜ ሆነው ስንት ጊዜ ሞላ

አየሽ እኔ ልጅሽ

በኖርኩት ዘመኔ
ልጄ ሆይ ያለችን እንቴን ያልረዳሁ
እምነት የጎደለኝ
ትንቢቴን የፈራሁ ቤቴን ያልተረዳሁ

እዳዬን ፈርቼ
ስቃዬን ፈርቼ መስቀል እየሸሸሁ
በጉብዝናዬ ወር
ቀሽም ቀን ሳሳልፍ ስንት ግዜ አመሸሁ

አየሽ አይደል እማ
ከንቱነት ነው ለካ
እናቱን ማያምን እናቱን ማይሰማ

እውነትም እኔ ነኝ
መንገድም እኔው ነኝ ለራሴ እንዳላልኩኝ
መሄጃው ሲጠፋኝ
አማላጅ ፍለጋ ከእቅፍሽ ላይ ዋልኩኝ

መገመት የሚከብድ ለሀሳብ የረቀቀ
መፍረድ የማይችል ሆድ ክክፋት የራቀ

በዚህ ሁሉ ሽሽት በዚህ ሁሉ ምሽት
እንዴት አልተቆጣ እንዴት አልረገመኝ
እውነት እማማዬ ማርያምን ነው ምልሽ
እቅፍሽ ገረመኝ

ቤትሽ ግድግዳ ላይ
ማርያም ልጇን አቅፋ ምትታየው ምስል
ለምን አነደሆነ እንጃ
ቁርጥ እራስሽን አንቺን ስትመስል


>>Click here to continue<<

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒




Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)