ሁለንተናዊ የልጆች እድገት /Holstic Child Development!
የልጆች የእድገት ዘርፎች የምንላቸው:-
አካላዊ እድገት፣ የስሜት እድገት፣ የአእምሮ እድገት፣ የማህበራዊ ግንኙነት እድገት፣ የቋንቋ/ ተግባቦት እና የመንፈሳዊ እድገት ናቸው። እነዚህን የእድገት ዘርፎች ለማጎልበት የወላጆች፣ የቤተሰብ እና የመምህራን ብሎም የማህበረሰቡ ድርሻ ትልቅ ነው።
ስኬታማ፣ ሁለንተናዊ እድገት እንዲኖሩ:-
- ልጆች ሊያደርጉ ስለሚገባቸው ነገሮች ከመንገር ይልቅ አርአያ በመሆን ማሳየት።
- ልጆች የሚያደርጓቸውን ጥረቶች ማበረታታት እና መደገፍ።
- በራስ መተማመን በጣም አስፈላጊ ክህሎት መሆኑን ማሳወቅ እና ክህሎቱን እንዲያጎለብቱ ማገዝ።
- በእለት-ተእለት የሚገጥሟቸውን ችግሮች እንዴት መፍታት እንዳለባቸው እና ካጋጠማቸው ችግር ምን ሊማሩ እንደሚችሉ ማሳየት።
- ችግር የመቋቋም ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት።
- የልጆች ሀላፊነት፣ መብት እና ግዴታ ምንድነው የሚለውን ማሳወቅ።
- ያዪ እና የሰሙትን እንዲያደርጉ ብቻ ሳይሆን የራሳቸው የፈጠራ ክህሎት እንዲኖራቸው ማበረታታት።
- ስለሚሰማቸው ስሜት መግለፅ እና ምን አይነት ስሜት እየተሰማቸው እንደሆነ እንዲገልፁ ማበረታታት።
- ከስህተት እና ከውድቀት መማር እንደሚቻል ማሳወቅ።
- ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት ማድረግ እና መደጋገፍ አስፈላጊነቱን ማስተማር።
- ውሳኔ የመወሰን ክህሎት እንዲያዳብሩ እድል መስጠት።
- ከልጅዎ ጋር እድሜው/ እድሜዋ በሚፈቅደው ጉዳዬች ላይ በግልፅ መወያየት እና ለልጆች ክብር እና ጊዜ መስጠት።
- ጥፋት ሲያጠፉ መቅጣት ብቻ ሳይሆን መልካም ሲያደርጉ ማበረታታት።
- ልጆች በቀለም ትምህርት ጥሩ እንዲሆኑ እንደምንለፋው ሁሉ ጠንካራ መንፈሳዊ መሰረት እንዲኖራቸው ትኩረት እንስጥ። እውቀት ያለሞራል ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል።
- ከምንም በላይ ልጆች የሚያዳምጣቸው፣ የሚረዳቸው እና ባግባቡ የሚመራቸው ሰው ይፈልጋሉ ወላጆች ይህንን አስቀድሙ።
- ውብ እና ድንቅ ሆነው በፈጣሪ አምሳል እንደተፈጠሩ መንገር።
- አቅም በፈቀደ ሁሉ የተመጣጠነ እና እቤት ውስጥ የተዘጋጀ ምግብ እንዲመገቡ እና ንፅህናቸውን እንዲጠብቁ ማድረግ።
- ለአካላዊ፣ ስነልቦናዊ እና አእምሯዊ ጉዳት እና አደጋ ተጋላጭ ከሚያደርጓቸው ነገሮች መጠበቅ እና መከላከል።
በመአዛ መንክር (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት)
@melkam_enaseb
>>Click here to continue<<