ከስሜት ቀውስ ጋር የሚታገሉ ሰዎች . . .
- እርዳታ እየፈለጉ እንኳን እርዳታ መጠየቅ ስለሚያስቸግራቸው ሁል ጊዜ ሁኔታቸው በራሳቸው ለመፍታት ይታገላሉ፡፡
- ፈታ የማለት (relax የማድረግ) ስሜት ስለሌላቸው ሁል ጊዜ የሆነ ነገር እንደጎደለ አይነት ስሜት ይዘው በተጠንቀቅ ነው የሚኖሩት፡፡
- ላጠፉትም ላላጠፉትም ነገር ይቅርታ የመጠየቅ ዝንባሌ አላቸው፡፡
- ከሰዎች ጋር ካሳለፉ ወይም ከተነጋገሩ በኋላ ሁኔታውን በሃሳባቸው በማውጣትና በማውረድ “ምነው እንዲህ ባልኩኝ” እና “ምነው እንዲህ ባላልኩኝ” የሚሉት ነገር ብዙ ነው፡፡
- እነሱ በውል ምክንያቱን አያውቁትም እንጂ ገና ለገና ሰዎች ይገፉኛል በማለት ቀድሞኑ ሲቀርቧቸው ራሳቸውን ክፍት ማድረግ ያታግላቸዋል፡፡
- ሁል ጊዜ ከሰዎች መደነቅንና ጎሽ መባልን (approval and validation) ይፈልጋሉ፡፡
- በምንም ሁኔታ ውስጥ ሰዎችን ቅር ማሰኘት ስለማይፈልጉ ሰዎች ለሚሰማቸው ስሜት እነሱ ሃላፊነትን የመውሰድ ዝንባሌ አላቸው፡፡
(ዶ/ር እዮብ ማሞ)
@melkam_enaseb
>>Click here to continue<<
