TG Telegram Group & Channel
Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠 | United States America (US)
Create: Update:

ስሜቶቻችን (Emotions)

ስሜቶቻችን (Emotions) የህይወት ቀለማት ናቸው። ህይወት ውበት እንዲኖራት ያደርጋሉ። ደግሞም ለመኖራችን ምክንያት ናቸው (they have survival value).

ስሜት (Emotions) አንጎላችን ለክስተቶች የሚሰጣቸው ግብረመልሶች ሲሆኑ ለሆነ ክስተት ተገቢውን ምላሽ እንድንሰጥ ያስችሉናል።

ይህም ማለት:-

- አስፈሪ ክስተት ሲያጋጥመን የፍርሃት ስሜት በመፍጠር ወይ እንድንጋፈጥ ወይ ሩጠን እንድናመልጥ ያደርገናል።

- በሚያስደስተው እንድንደሰት እና ሰውነታችን ዘና እንዲል፣ በሚያሳዝነው እንድናዝን፣ በሚያስጠይፈው እንድንጠየፍ እና ራሳችንን ከመጥፎ ነገር እንድናርቅ ያደርገናል፣ በሚያናድደው እንድንናደድ እና ችግሩን እንድንቀርፍ ያስችለናል። ይህ ህይወት እንድትቀጥል ወሳኝ ሚና አለው።

Aristotle, The Nichomachean Ethics በተሰኘ መጽሃፉ እንዲህ ይለናል:-

''Anyone can be angry- that is easy. But to be angry with the right person, to the right degree, at the right time, for the right purpose, and in the right way; that is not easy.''  

ይህን አባባል ዳንኤል ጎልማን 'Emotional intelligence' በተባለ መጽሃፉ እንደ መግቢያ ተጠቅሞበታል።

እኔም ይህን አባባል እመራዋለሁ። ችግሩ መናደዳችን ሳይሆን ንዴታችን አውዱን ያልጠበቀ መሆኑ ላይ ነው፤ ንዴታችንን አውድ እና ጠርዝ እንዲኖረው ማድረግ መቻል አለመቻላችን እንደ አንድ የስነልቦናዊ ብስለት እና ራስን የመግዛት ችሎታ ነው።

ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)

@melkam_enaseb

>>Click here to continue<<

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)