የአእምሮ እድገት ውስንነት (Intellectual Developmental Disorder)
=================
የአእምሮ እድገት ውስንነት ማለት አንድ ልጅ ያለው ትምህርት የመቀበልና የማስታወስ አቅም ፣ የማገናዘብ ፣ ውሳኔ የመወሰን ፣ ችግር የመፍታት ፣ ከሌሎች ጋር ያለው የመግባባት እና ራስን የመርዳት ክህሎት ከእድሜው ከሚጠበቀው በታች ሲሆን ነው።
አንድ ሰው ጤናማ የሆነ የአእምሮ አቅም አለው የምንለው የማገናዝብ ፣ ነገሮች የመረዳትና የማስታወስ አቅም IQ=100 ሲሆን የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው IQ ከ 70 በታች ነው::
እነዚህ ምልክቶች መታየት የሚጀምሩት መቼ ነው?
ከልደት እስከ ትምህርት እድሜ ድረስ ሊታይ ይችላል።
ለምሳሌ:
👉መቀመጥ፣መቆም፣መራመድ እና ማውራት ካልጀመሩ
👉 ነገሮችን የማስታወስ አቅማቸው ዝቅተኛ ሲሆን
👉የባህሪ ችግር ሲኖር
👉በየእለቱ የሚያዩት የህይወት እንቅስቃሴ የመረዳት እና የመተግበር ውስንነት ሲኖር
የአእምሮ እድገት ውስነት መንስኤ👇
ምክንያት ሙሉ በሙሉ መንስኤው ይህ ነው ለማለት ቢከብድም አብዛኛዎቹ እንደመንስኤ የሚታዩት የሚከተሉት ናቸው
👉በዘር ሊከሰት ይችላል
👉 በፅንስ ወቅት እናት አልኮል እና በፅንስ ወቅት ሊወሰዱ የማይገባቸው መድሃኒቶች መውሰድ ፣ የምግብ እጥረት እና የተለያዩ ህመሞች በእናት ላይ ከነበሩ.
👉በወሊድ ወቅት የኦክስጂን እጥረት መከሰት እና ሊወለድ #ከሚገባ ጊዜ ቀድሞ መወለድ.
👉ልጅ ከተወለደ በሁዋላ በመውደቅ ወይም በግጭት የአእምሮ ጉዳት ሲያጋጥም.
👉ከፍተኛ የሆነ የምግብ እጥረት ፣ ሜኒጃይተስ በተባለ ህመም መጠቃት ፣ አእምሮን ሊጎዱ በሚችሉ ኢንፌክሽኖች መያዝ እና ለጎጅ ንጥረ ነገሮች ተጋላጭነት .
ይቀጥላል!
#የልጆች_የአእምሮ_ጤና_ግንዛቤ
ዮርዳኖስ ይሁን (የስነ-አእምሮ ባለሙያ)
#ጤናማ_አዕምሮ_ጤናማ_ህይወት!!!"
>>Click here to continue<<