TG Telegram Group & Channel
ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan | United States America (US)
Create: Update:

††† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ተአምረ ማርያም †††

††† ተአምር ማለት "ድንቅ: ምልክት: ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ የሆነ ክዋኔ: በሰብአዊ አቅም ሊሠራ የማይችል ተግባር (ድርጊት)" ነው:: ተአምራት ከባለቤቱ ከጌታችን ሲሆኑ የባሕርዩ ናቸው:: ከቅዱሳኑ ሲሆኑ ደግሞ የጸጋ እንላቸዋለን:: ቅዱስ መጽሐፍ ላይ በእግዚአብሔር ወዳጆች የተሠሩ ተአምራት እጅግ ብዙ ናቸው:: ነገር ግን:-
*ተአምራት ከአጋንንትም ሊሆኑ እንደሚችሉ መረዳት::
*ሁሌ ምልክትን (ተአምርን) አለመፈለግ::
*መመርመርና ማስተዋል ከአንድ ክርስቲያን ይጠበቃል::
*ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በድርሳኑ እንደ ነገረን ተአምር መሥራት ከሲዖል እሳት አያድንም:: ጌታም በዚህ ነገር ተባብሮበታል:: (ማቴ. 7:22, 12:39)

ከጌታችን እግዚአብሔር ቀጥሎ የድንግል ማርያምን ያህል ተአምራትን የሠራ አይገኝም:: እንዲያው ሌላውን ትተን በእያንዳንዳችን ሕይወት ላይ እንኳ ብዙ ድንቅ ነገሮችን አድርጋለችና ምስክሮቹ እኛው ራሳችን ነን:: የእመቤታችን ተአምር የተጀመረው ገና ከፍጥረተ ዓለም ነው::

በእርግጥ ይህንን ለመረዳት ሠፊ አዕምሮና አስተዋይ ልቡናን ይጠይቃል:: ድንግል ማርያም ማለት የእግዚአብሔር የቸርነቱ ግምጃ ቤት: የጸጋው ደጅ ናት:: እርሱ ይህንን መርጦ ወዷልና:: እመ ብርሃን ተጸንሳ ከተወለደች በኋላ ደግሞ እጅግ ብዙ ኃይልን ታደርግ ነበር:: በዚህ ዕለት ከ2007 ዓመታት በፊት ያደረገችው ተአምር ደግሞ ድንቅ ነው::

አጐቷ /ጠባቂዋ/ አገልጋዩዋ አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ከቤተ መቅደስ ተቀብሎ ካመጣት በኋላ እርሱ እንጨትን ይጠርብ ነበር:: ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ (የችግር ዘመን) በመሆኑ ለሥራ ጉዳይ ወደ ሩቅ ሃገር ሒዶ የተመለሰው ከወራት በኋላ ነው::

ዮሐንስ የሚሉት ፈላስፋ ባልንጀራ ነበረውና ሽማግሌው ዮሴፍ ልብ ያላለውን ነገር ነገረው:: "ይህች ብላቴና ጸንሳለችና መርምራት" ብሎ ሔደ:: ቅዱስ ዮሴፍ ግን ደነገጠ:: "እኔ እንዲህ ያለ ነገር እንኳን በገቢር (በሥራ) በሃሳብም አላውቅባት" ብሎት ወደ ቤት ገባ::

ቀጥሎም እመቤታችንን "ልጄ ሆይ! ከማን ጸነስሽ" አላት:: "እመንፈስ ቅዱስ" አለችው:: ግራ ገባው: ምሥጢርም ተሠወረበት:: "እንዴት አንዲት ሴት ያለ ወንድ ዘር ልትጸንስ ትችላለች?" ብሎ ያወጣ: ያወርድ: ይጨነቅም ገባ:: የእኛ እመቤት ግን እንደ ጨነቀው ባወቀች ጊዜ ጠርታ ወደ ውጪ ይዛው ወጣች::

ከረዥም ጊዜ በፊት ጠርቦ የጣለውን እንጨት አንስታ ተከለችውና ጸለየችበት:: በደቂቃም የአረጋዊው ዐይን እያየ ያ ደረቅ እንጨት ለምልሞ: አብቦ አፈራ:: ቅዱስ ዮሴፍ በጣም ደነገጠ::

"አባቴ ተመልከት እስኪ! ይህንን ማን አደረገ?" አለችው:: "ልጄና እመቤቴ! እግዚአብሔር ነው" አላት:: እርሷም "በማሕጸኔ ያለውም ኢሳይያስ ትንቢትን የተናገረለት አምላክ ነውና ሁሉን ይችላል" አለችው:: አረጋዊውም ቅዱስ ኤራቅሊስ በሃይማኖተ አበው እንደ ነገረን "ሰገደ ላቲ" ወደ ምድር ወድቆ በፊቷ ሰገደ::

††† ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ †††

††† ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)

የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር::

እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ ደግሞ 100 ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በኋላ ሰኔ 30 ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

††† የእመቤታችን ልመናዋ: ክብሯ: የልጇ የወዳጇም ቸርነት በእውነት ከሁላችን ጋር ይሁን:: የመጥምቁንም በረከት ያብዛልን::

††† መስከረም 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ድንግል ማርያም
2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
3.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ (ጽንሰቱ)
4.ቅዱሳን ዘካርያስና ኤልሳቤጥ
5.ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት (ፍልሠቱ)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
5.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

††† "ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ጽንሱ በማሕጸኗ ውስጥ ዘለለ:: በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት:: በታላቅ ድምጽም ጮኻ እንዲህ አለች:-
'አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ: የማሕጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው:: የጌታየ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? . . . ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብጽዕት ናት::" †††
(ሉቃ. ፩፥፵፩)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

>>Click here to continue<<

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)