የመዳን ቀን....
ሀጥያት በደል ቢከበኝም፤
ካንተ በቀር ሰው የለኝም።
ነውሬ በዝቶ ከዘመኔ፥ ከፀጋህ ቢያጎድለኝም፤
ይቅር የሚል የሚያድነኝ ፥ካንተ በቀር ሰው የለኝም።
ሙሉ መስሎ ያለም ደስታ፥ ሞኙን ልቤን ያማለለ፤
ያልወጣሁት የሀጢያት ማጥ፥የጠለቀ ገደል አለ።
(አቤቱ...)
:
ሲጎድልብኝ ላንተ ማልቀስ፥ ሲሞላልኝ ወደ ሀጢያት፤
አንተ ግን አልቸኮልክም፥ ለበደሌ እኔን መቅጣት።
ነብሴን ፀፀት እያወካት፥ ሰውነቴ ሰላም አቶ፤
ተስፋ ከልቤ ተሰዶ፥ መጽናናቴ ውስጤ ሞቶ።
(ማረኝ...)
፥
አይነ ህሊናዬ ታወሮ፥ ልቦናዬ ድንጋይ ሆኗል፤
በህይወቴ ብርሀን የለም፥ የጨለማዬ ዋሻ ገኗል።
ከሀጢያቴ ጉድጓድ እጮሀለሁ፥ ትሰማለህ ስጠራህ፤
እኔን ወዳንተ ሚመመልስ፥ አንድ ቃልስ ታጣለህ?
(ይቅር...)
፥
ያሳየኛል ያ ጠላቴ፥ በምናቤ ከፍታዬን፤
ዛሬን ንዶ አደላድሎ፥ ያሳለፍኩት ያን ደስታዬን።
የቆሮንጦሱ ፈተናህ፥ ዛሬም እኔን ይገጥመኛል፤
ድንጋይ-ዳቦ ስልጣን-ጀብዱ፥ ይሄን ሁሉ ያስመኘኛል።
(በለኝ...)
፥
ጌታዬ ሆይ እባክህን?
አምላኬ ሆይ እባክህን፧
ልብ ስጠኝ፤
ጊዜ ስጠኝ፤
አውጣኝ ከዚህ ከቅዠቱ፥ ከከንቱ አለም፤
ካንተ በቀር ሌላ ማንም፥ እውነት መንገድ ህይወት የለም።
(እግዚአብሔር...)
፥
ልናዘዛት ያቺን ሀጢያት፥ የማፍራትን የዘውትሬን፤
ልናዘዛት ከኔ ትውጣ፥ በንስሐ ልጠብ ነውሬን።
ልናዘዛት ያቺን ሀጢያት፥ ህሊናዬ ነጻ ይውጣ፤
ልናዘዛት እሷን ልተው፥ የመዳን ቀን እንዲመጣ።
(በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥)
፥
በምህረትህ ብዛት፥ ወደ ቤትህ አስገባኝ፤
በተወደደ ጊዜ ስማኝ፥ በማዳንህ ቀን ርዳኝ።
እስክወጣ ጥቂት ታገስ፥ በመአትህ አትቅሰፈኝ፣
እስክናዘዝ ጥቂት ታገስ፥ ይቺን አመት ብቻ ተወኝ።
(ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤)
+++
“በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ
በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤
እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤
እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።”
— 2ኛ ቆሮ 6፥2
+++
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
hottg.com/Menfesawigetmoch
>>Click here to continue<<
