"ድህንነት' ነሽ"
የለብን አበሳ፥ የለብን መርገም፤
ቀድሶናልና፥ የክርስቶስ ደም።
አንቺ የኖህ ርግብ፥ አማን በአማን፤
የጥፋቱ ውሀ፥ ጎደለ አሜን፤
አንቺ የዘርዓ ያዕቆብ፥ የዳዊት ሙሽራ፤
ከደረትሽ ያለው፥ መስቀልሽ አበራ።
፡
ባንቺ በናታችን፥ በእመቤታችን፤
ህፃኑ ተሰጠን፥ ዳንን ሁላችን፤
አዳም የተከለው፥ የዘራው ጸደቀ፤
መሬትሽ ነውና፥ በጣም የታወቀ።
፡
የድህነት' አዝመራ፥ ካንቺ እንለቅማለን፤
በመዳኛ ልጅሽ፥ በእርሱ እንድናለን፤
ከእንግዲህ ህመማችን፥ ጭንቃችን አይጥና፤
ክርስቶስ በደሙ፥ ቀድሶናልና።
ድልድዩ ይሰራ ጠማማውም ይቅና።
፡
ተለያይቶ መኖር፥ አጉድሎናልና፥ በድሎናልና።
ጠማማውን መንገድ የቀና አድርገን፤
ጋራ ሸንተረሩን አስተካክለን ፥ሰርተን፤
ሀይማኖት ከምግባር፥ አስተባብረን ይዘን፤
ከድንግል ማርያም ጋር፥ አብረናት ተጉዘን፤
መላ አካላችንን፥ ከሐጥያት አንፅተን፤
የድህንነት' ሰብል፥ እንሰብስብ በርትተን።
++++++
ድህነት' ጠብቆ ይነበብ/መዳን፣መፈወስ/
©ምህረት/Mihert/
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
hottg.com/Menfesawigetmoch
>>Click here to continue<<