"መንገዴ ነህ"
ተስፋዬ አደረኩህ፥ ሞተህ ስላኖርከኝ፤
በራሴ ላይ ሾምኩህ፥ አዳኝ ስለሆንከኝ።
መሄጃዬ አንተ፥ መደምደሚያ ሆንከኝ፤
ህይወትህን ሰተህ፥ ሞትን አሻገርከኝ።
፥
በመንገዶች ላይ፥ እንቅፋት ኖሮበት፤
ወድቄ እንድቀር፥ጠጠር ዘርተውበት።
እንድመለስ ሽቶ፥ ሆኖ ሁሉ ከንቱ፤
እኔን መጣል ነበር፥ ጠላቴ ምኞቱ ።
፥
በመንገዶችቼ ላይ ፥ አቋራጭ ቢኖርም፤
እኔ አንተን አለቅም፥ እኔ ያላንተ አልኖርም።
አውቀዋለሁ፥ ለኔ አይጠቅምም፤
ትግስቴ እስኪያልቅ፥ ብፈተንም።
አምናለው በእግዚአብሔር፥ አልፋለው ሁሉንም።
፥
ተነሽ በርቺ ፥አይዞሽ ልጄ፤
እኔ ይዤሻለው፥ በበረከት እጄ።
ይለኛል ዘወትር፥ ጠላት እንዳልፈራ፤
አይበቅልም ከርሻዬ ፥እንክርዳድ ቢዘራ፤
እግዚአብሔር አለ፥ የሰማዩ ጌታ፤
ስወድቅ የሚያነሳ፥ ልቤን ያበረታ።
የረታኝን ጠላት፥ በመስቀል የረታ፤
ህይወቴን ፈጠረ፥ በትንፋሹ እፍታ
፥
መንገዴን ጠራጊ፥ የአባቶቼ አምላክ፤
በፈተና እንዳልወድቅ፥ እኔን የጠበክ።
ለአንተ ለዘላለም፥ ይንበርከክ ጉልበቴ፤
አንተን ብቻ እናምልክ፥ እኔና ያ ቤቴ።
፥
ሰቶኝ የማይቀማ፥ታማኝ አምላክ አለኝ፤
ጥሎኝ የማይተኛ፥ጠባቂ ጌታ አለኝ።
ታድያ በዚህ አለም፥ እኔ ምን ጎድሎኛል?
በእርሱ ህያው መንገድ፥ ሁሌም ያኖረኛል።
፥
አሜን ክብር ይሁን፥ መንገዴን ላፀዳ፤
አሜን ምስጋና ይሁን፥ ልጁን ለሚረዳ።
አሜን አምልኮ ይሁን፥ ህይወቴን ለሰራ፤
በልቦናዬ እርሻ፥ የማያልቅ ፍቅሩን ሳይሰስት ለዘራ።
ምስጋና ይድረሰው፥ ክብር ይግባው ጌታዬ፤
መንገዴ ህይወቴ፥ ባለውለታዬ።
+++++++
©ምህረት/Mihert/
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
hottg.com/Menfesawigetmoch
>>Click here to continue<<