ፍምን እፍ ብትላት ትነድዳለች፤ ትፍ ብትልባትም ትጠፋለች፤ ሁለቱም ከአንድ አፍ ይወጣሉ።
ሐሜተኛንና ሁለት አንደበት ያለውን ሰው ይረግሙታል፤ ብዙ ወዳጆችን አጋድሎአልና። ነገረ ሠሪ አንደበት ብዙ ሰዎችን አወካቸው፤ ከሕዝብም ወደ ሕዝብ አሳደዳቸው። የጸኑ ከተሞችንም አፈረሰ፤ የመኳንንቱንም ቤት ጣለ። .…
ንብረትህን በእሾህ ብታጥር፥ ወርቅህንና ብርህንም ብትቈልፍ፥ ነገርህን በሚዛን ብትመዝን፥ ለአፍህም መዝጊያና ቍልፍ ብታደርግ፥ ዳግመኛም በአንደበትህ እንዳትሰነካከል፥ በሚያድንህም ፊት እንዳትጥልህ ተጠበቅ።
መጽሐፈ ሲራክ 28:12 - 14 , 24-26
>>Click here to continue<<