TG Telegram Group & Channel
እልመስጦአግያ+++ | United States America (US)
Create: Update:

+ ተአምረ ማርያምና አንዳንድ ጉዳዮች +
(ክፍል ሁለት)

መጋቤ ሐዲስ የኔታ እሸቱ በአንድ ወቅት ‘ልጅ አባቱን ሳይመስል ከቀረ በዲኤንኤ ይመረመራል፡፡ አዋልድ መጻሕፍት የመጽሐፍ ቅዱስ ልጆች ናቸው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ዲኤናኤ የሚገኘው አዋልድ መጻሕፍት ላይ ነው’ ብለው ነበር፡፡ ሰሞኑን በነበሩ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ መድረኮች ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃምና ሌሎችም አባቶች ያደረጓቸውን ንግግሮች አስተውሎ ለሰማ ሰው ሊያስተውለው የሚችለው ይህንኑ ቁም ነገር ነው፡፡

ከሰሞነኛው ውዥንብር በፊትም በአንድ ቃለ መጠይቅ ላይ ብፁዕ አቡነ በርናባስ ይህንኑ ሃሳብ ሲናገሩ የነበረ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኒቱ በገድላትና ድርሳናት ላይ የተደረጉ የመቀሰጥ ሥራዎች ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዘላቂ መፍትሔ ለመሥጠት እየተሠራች መሆኑን ያሳያል፡፡ አዋልድ መጻሕፍት አባታቸውን መጽሐፍ ቅዱስንና የቤተ ክርስቲያኒቱን መሠረተ እምነት የማይመስሉ ሆነው እንዳይገኙና ቤተ ክርስቲያን በማትቀበለው ይዘት የታተሙና የተሰራጩትም በቤተ ክርስቲያኒቱ ማእከላዊ አሠራር መፍትሔ እንደሚያገኙ አባቶች በአንድ ቃልና በአንድ ልብ ተናግረዋል፡፡ ይህም የቤተ ክርስቲያኒቱን ልዕልና ከማስከበር ጋር በዘላቂነት መፍትሔ የሚሠጥ መንገድ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስም ካሉበት አስተዳደራዊ ጫናዎች ጋር እንደ መጀመሪያው የሐዋርያት ሲኖዶስ ‘የእግዚአብሔርን ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ አይደለም’ ብሎ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማጥራት ፣ ሃይማኖትን ማቅናቱ የኖረ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልማድ ነው፡፡

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ከቀናት በፊት እንዲህ አሉ፦

‘በገድሎቻችን ፣ በተአምረ ማርያም ፣ በተአምረ ኢየሱስ እየተሠራ ያለውን [ደባ?] በዚህ አጋጣሚ ሳንጠቁም አናልፍም፡፡ የሊቃውንት ጉባኤ ብዙ ሓላፊነት አለበት፡፡ ወደፊት ሥራዬ ብሎ የሚሠራው ፣ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱም ልዩ ትኩረት ሠጥቶ የሚያሠራው ይሆናል፡፡ በየመንደሩ ማተሚያ ቤቶች አሉ፡፡ በየመንደሩ ያለ ምንም ፈቃድ የጸሎት መጻሕፍት በጸሎት ስም ፣ ቤተ ክርስቲያኒቷ ስማቸውን የማታውቃቸውን መጻሕፍት ሳይቀር ሲፈልጉ ግርማ ሞገስ ይሉታል ፣ ሲፈልጉ ሌላም ሌላም ይሉታል፡፡ ይሄንን ብትገዙ ይህንን ብታነቡ ፣ ይሄንን በአንገታችሁ ብታሥሩ ፣ በትራሳችሁ ብታደርጉት የሚሉ ብዙ ማደናገሪያ ፣ ማወናበጃዎች ኅትመቶችም አሉ፡፡

በገድሎቻችንም ውስጥ ደግሞ አዳዲስ ... ትናንትና በዘመናቸው የተጻፉ ገድላትን በታላላቅ ገዳማትና አድባራት ውስጥ በየሙዝየሙ በየቤተ መዘክሩ ገብተን ብናነጻጽራቸው ምንም ግንኙነት ፣ ዝምድና የሌላቸውን ደራስያን እየደረሱ ፣ ሥርዋጽ እያስገቡ ‘ይሄ ነው እንግዲህ’ ብለው ስም የሚያጠፉበትም አስቀድመው የሠሩትም ሥራ መኖሩን ሳንጠቁም አናልፍም፡፡ በተፈለገው ገድል ላይ ፣ ተአምረ ማርያም ላይ ፣ ተአምረ ኢየሱስ ላይ ብዙ የምንጠቅሰው ስላለን ነው፡፡ ምክንያቱም ተቆጣጣሪ የለም፡፡ እኛ ያለንበትንም [ሁኔታ] ‘አካሔዱን አይቶ ስንቁን ይቀሙታል’ እንደሚባለው [ነው] የእኛ አካሔድ ጊዜያዊ ነገር ላይ ተጠምደናል፡፡ ሹመት ላይ ፣ ሥልጣን ላይ ፣ ጥቅማ ጥቅም ፍለጋ ላይ ፣ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ላይ ፣ በጎጡ በጎሣው ወዘተ እንደተጠመድን ስላዩን እነርሱ ሥራቸውን እየሠሩ ፣ ከንጹሑ ስንዴ ላይ እንክርዳድ እየዘሩ እያበቀሉ ያንን ደግሞ ለደፋሮች ፣ ኀፊረ ገጽ የሌላቸው ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ማንነት ለማያውቁ በድፍረት እንዲናገሩ ጋባዦች መኖራቸውን ሳንጠቁም አናልፍም፡፡

እነዚህ ሁሉ ዓይናማ ሊቃውንት ያሏት ቤተ ክርስቲያን የትኛው ገድል ፣ የትኛው ተአምር ፣ የትኛው ድርሳን ፣ የትኛው ተአምረ ማርያም በዚህ ዘመን በየትኛው ማተሚያ ቤት ተጨመረ ፣ ተቀነሰ የሚለው ራሱን የቻለ ጥናት ይካሔድበታል’

ይህንን የብፁዓን አበው ንግግር ይዘው ላለፉት ጥቂት ዐሠርት ዓመታት ከቤተ ክርስቲያን በተቃራኒ የቆሙ አንዳንዶች ሰዎች ‘ቃላችን ተሰማ’ በሚል ስድባቸውን ሁሉ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ከማሰብ የመጣ እንደነበር አድርገው ለመሣል ሲሯሯጡ ታይቶአል፡፡ ግዴለም ክሬዲቱን ይውሰዱ ፣ ሟች ሲባል ‘አቤት’ ገዳይ ሲባል ‘አቤት’ ግን መቼም የሚያስተዛዝብ ነገር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ገድላትንና ተአምራትን በተመለከተ ስለሚሠሩ የሊቃውንት ጉባኤ ሥራዎች ሲናገር ግን የሰሞኑ የመጀመሪያ አይደለም፡፡

በቤተ ክርስቲያንዋ አዋልድ መጻሕፍት ዙሪያ ላይ በሊቃውንት ጉባኤ መሪነት ሥራዎች እንዲሠሩ ተደጋጋሚ ውሳኔዎችን ሲያሳልፍ ቆይቶአል፡፡ የመጨረሻውን እንኳን ብንጠቅስ ግንቦት 2009 ዓ.ም. በተደረገው ርክበ ካህናት በተአምረ ማርያም ፣ በፍትሐ ነገሥት ፣ በስንክሳርና በራእየ ማርያም መጻሕፍት ላይ የተወያየው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፎ ነበር፡-

​‘‘በግል አታሚዎች እየታተሙ በሚወጡ የአዋልድ መጻሕፍት ውስጥ፣ ወቅት እየጠበቁ ኾነ ተብለው በግለሰቦች ተጨምረዋል፤ የተባሉ ተኣምራትና የሕዝቦች ስያሜዎች የመሳሰሉት፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን የማይወክሉና ከዕውቅናዋ ውጭ የወጡ ኅትመቶች (unauthorized versions) እንደኾኑ በምልአተ ጉባኤው ተመክሮበታል፡፡ የቀድሞዎቹን ትክክለኛ ቅጅዎች (authoritative texts) የሚያፋልስና አስተምህሮዋን የሚፃረር ይዘት በግል አታሚዎቹ ተጨማምሮባቸዋል ከተባሉት ውስጥ፥ የራእየ ማርያም እና የተኣምረ ማርያም መጻሕፍት በምሳሌነት የተጠቀሱ ሲኾን፤ የቀድሞውን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስንና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን በማካተት የታተመ ‘ተኣምረ ማርያም’ በአስረጅነት ቀርቧል፡፡

በበላይ ሕጓ እንደተደነገገው፣ ቤተ ክርስቲያን፣ ከጥንት ጀምሮ በሊቃውንት ልጆችዋ አማካይነት እየጻፈች፣ እየተረጎመችና እያዘጋጀች ስትገለገልባቸው፣ ስትጠብቃቸውና ስታስተምራቸው የኖሩትን መጻሕፍት ኹሉ፣ ዛሬም በያሉበት በባለቤትነት የመጠበቅና የማስጠበቅ መብት ያላት በመኾኑ፣ በዚኽም በኩል፥ ስግብግብ አታሚዎችን በማስቆምና የትክክለኛ ቅዱሳት መጻሕፍቷን ኅትመትና ሥርጭት በመቆጣጠር አስፈላጊው ኹሉ እንዲፈጸም፣ ምልአተ ጉባኤው ትእዛዝ ሰጥቷል’’ /ሐራ ተዋሕዶ ፤ ግንቦት 5 2009 ዓ.ም./

ገድላትን ፣ ድርሳናትና ተአምራት እርማት ሊደረግባቸው ይችላል ሲባል ቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነትዋን /ዶግማዋን/ እየከለሰች የሚመስለው የዋህ ሰው ይኖራል፡፡ ይህም የቤተ ክርስቲያንን ሥልጣን ካለመረዳት የሚመነጭ ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንኳንስ አዋልድ መጻሕፍትን ቀርቶ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተካተቱትንም መጻሕፍት ከብዙ መጻሕፍት መካከል መርጣ ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ይሁን ብላ በጉባኤ የወሰነች መሆንዋን የመጽሐፍ ቅዱስን ቀኖና ታሪክ (The History of the Canonaization of the Bible) የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡ ‘ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ሠጠችን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንን አልሠጠንም’ እንደሚባለው ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን እንኳን በዕድሜ ትቀድመዋለች፡፡ ስለዚህ እንኳንስ አዋልድ መጻሕፍት መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ አራት መቶ ዓመታትን በፈጀ ማጣራትና ድካም በቀኖና ተደንግጎ እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰ መጽሐፍ ነው እንጂ ጥንቅቅ ብሎ ከነማውጫውና ከነኅዳግ ማስታወሻው ከሰማይ የዘነበ መጽሐፍ አይደለም፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ቀኖና እንኳን ቅዱስ አትናቴዎስ በትንሣኤ ዕለት በተነበበው አባታዊ መልእክቱ 367 ዓ.ም.

>>Click here to continue<<

እልመስጦአግያ+++

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)