TG Telegram Group & Channel
ቅንጭብጭብ | United States America (US)
Create: Update:

ህይወት ለሳንዲ ፒርስ ፡ ደስ ትላለች. .. ሳንዲ በችካጎ ከተማ ከሚገኝ አንድ ባንክ ውስጥ ትሰራለች. .እናም እንደተለመደው በከተማዋ ዳርቻ ወደሚገኘው ቤቷ በማምራት ላይ ሳለች. .. ኩርቲስ ጃክሰንን ከርቀት ተመለከተችው. ..
..................
በዚህ ጎዳና ላይ አዘውትሮ የሚመላለስ ሰው ፡ ኩርቲስ ጃክሰንን ያውቀዋል ።
ይህ ሰው ለአመታት በዚህ ጎዳና ላይ አዘውትሮ በሚቀመጥበት ቦታ ላይ ሆኖ ፡ የሰወችን ደግነት ይጠባበቃል ። ኑሮው በሰወች ልግስና ላይ የተመሰረተ ነው ። እናም ዛሬም እንደተለመደው " ቤት አልባ ነኝ እርዱኝ " የሚል ፅሁፍ ደረቱ ላይ አድርጎ መብራት ይዟቸው የቆሙ ሰወችን እየለመነ ነው ።
.............
ሳንዲ ፒርስ ይሄ ጥቁር አሜሪካዊ ያሳዝናታል ፡ እናም አቅሟ በፈቀደ መጠን ሁሌም ትረዳዋለች ፡ ጥቂት ደቂቃ ወስዳም ታወራዋለች ፡ ይህ ለአንድ የጎዳና ተዳዳሪ ሰው ትልቅ ነገር ነበር ። እናም ዛሬ ፡ መብራት የያዛቸውን ሰወች ለምኖ ፡ ወደዘወትር ቦታው ሲመለስ ፡ ያችን ደግ ሴት ቆማ ስትጠብቀው ተመለከተ. . ሃይ ሳንዲ እንዴት ነሽ ፡ ልጅሽ ደህና ነው አላት ፡ የአስር አመት ልጅ እንዳላት ነግራዋለች እናም ሁሌ እሷን ሲያገኝ ይህንን ይጠይቃታል ።
.........
ሳንዲ ፒርስ ሁሉም ሰላም እንደሆነ ነግራው ፡ ህይወት አንድ ቀን መልካም ይሆናልና ተስፋ እንዳይቆርጥ አፅናንታው ፡ ጥቂት ብሮች ሰጥታው ሄደች ።
............
ኩርቲስ ጃክሰን በዚህች ሴት ደግነት ሁሌ ይገረማል ፡ ለሱ ይህች ሴት ዝም ብሎ ሳንቲም ሰጥተውት እንደሚያልፉት አይነት አይደለችም ፡ ፈጣሪ እንድታፅናናው የላከለት እህቱ ትመስለዋለች. . እናም በሳምንት የተወሰነ ጊዜ መጥታ ሰላም ብላው ስትሄድ በህይወት ላይ ተስፋ ያደርጋል ።
................
ሰሞኑን ግን ይህች መልካም ሴት ወደሱ መጥታ አታውቅም ፡ ቢያንስ በሳምንት አንዴ እንኳን ትመጣ የነበረችው ሳንዲ ፒርስ በዛ ጎዳና ማለፍ ከተወች ፡ አንድ ወር ሆናት. ..,በዚህ ጊዜ ኩርቲስ ጃክሰን አንድ ነገር አሰበና ፡ ወደምትሰራበት ባንክ ሄዶ ጠየቀ ። ለአንድ ወር ያህል ገብታ ስራ ገብታ እንደማታውቅ ነገሩት ።
.............
የጎዳና ተዳዳሪው ጃክሰን ይህን ሲሰማ በጣም አዘነ ፡ አዝኖ ብቻ አልተወም ፡ እኖርበታለሁ ወዳለችው ወደከተማዋ ዳርቻ ያሉ መንደሮች ሄዶ ለመፈለግ ወደዚያው ተጓዘ ።

..............
ኩርቲስ ጃክሰን ከብዙ ፍለጋ በኋላ ፡ የሳንዲ ፒርስን መኖሪያ ቤት አገኘ ፡ ነገር ግን በውስጡ ማንም አልነበረም ። ቤቱ በራፍ ላይ የሚከራይ የሚል ፅሁፍ ተለጥፎ ጭር ብሏል ። ያቺ ደግነቷን ሳትነፍግ ትረዳው የነበረችው ሴት ከነልጇ ቤቱን ለቀው ሄደዋል ።

............
ምን እንደተፈጠረ ማወቅ ፈልጎ አንድ ጎረቤቷን ጠየቀ
ሳንዲ ፒርስ ከአንድ ወር በፊት በማታውቀው ሁኔታ ከስራዋ እንደተባረረች ፡ ለተወሰነ ጊዜም ፡ በአቅራቢያ በሚገኝ ሆቴል ክፍል እየተከራየች መቆየቷንና ፡ ያላትን ጥቂት ገንዘብ ጨርሳ የሆቴል መክፈል ሲያቅታት ፡ ከአስር አመት ልጇ ጋር መኪናዋ ውስጥ መኖር እንደጀመረች ነገሩት ።
.........
የጎዳና ተዳዳሪው ኩርቲስ ጃክሰን ይህን ነገር እንደሰማ ፡ መኪናዋን አቁማ ወደምትኖርበት ቦታ ሄደ ፡ እንዳሰበው ፡ የ39 አመቷ ፡የቀድሞ የባንክ ሰራተኛ ከነልጇ መኪና ውስጥ ሆና ፡ ከሰወች ጋር ስትነጋገር ደረሰ ፡ ሰወቹ ከማህበራዊ አገልግሎት የመጡ ደንብ አስከባሪዎች ነበሩ ። እናም ከ10 አመት ልጇ ጋር መኪና ውስጥ መኖር እንደማትችል በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ቢሰጧትም ፡ መተው ስላልቻለች ፡ መንግስት ልጇን በሃይል ነጥቆ ፡ ወደህጻናት ማሳደጊያ ወስዶ እንደሚያሳድገው ለመጨረሻ ጊዜ እያስጠነቀቋት ነበር ።

..............
ኩርቲስ ጃክሰን ይህን ሲሰማ አዘነ ፡ ሰወቹ ጥለዋት እንደሄዱም ቀርቦ ሰላም አላት ፡ ሳንዲ ፒርስ ፡ ይህ ሰው እሷን ፍለጋ መምጣቱን ስትሰማ አለቀሰች ፡ ህይወት እንደጨለመባት ዳግም እዚህ ብትገኝ መንግስት ልጇን እንደሚነጥቃት ነገረችው ። ኩርቲስ ይህችን ህይወት ፊቷን ያዞረችባትን ስታጽናናው ፡ በቻለችው መጠን ስትረዳው የነበረችውን ሴት በተራው ማፅናናት ያዘ ።
............

ከዚያም ፡ ታርፍበት ወደነበረው ሆቴል እንድትመለስ ፡ ክፍያውንም እሱ እንደሚችልላት ነገራት ፡ ሳንዲ ይህንን ስትሰማ ከዚህ ሰው ላይ የሆቴል መውሰድ ቢከብዳትም ፡ ልጇ ከሷ ጋር እንዲኖር ለማድረግ ያላት ብቸኛ ምርጫ በመሆኑ የኩርቲስን ሃሳብ ተቀብላ ፡ ታርፍበት ወደነበረው ሆቴል አመራች ፡ኩርቲስ ለምኖ ካገኘው ብር የጥቂት ቀን የሆቴል ክፍያ ሰጥቷት ወደተለመደው ቦታው አመራ
............
ሳንዲ ፒርስ ስራ ለመፈለግ ብትሞክርም ምንም ሊሳካላት አልቻለም ፡ እናም ለወራት ፡ በዚህ መልኩ ቆየች ፡ ኩርቲስ ጃክሰን ፡ ከወትሮው የበለጠ ፡ ብዙ ሰወችን እየለመነ ፡ ለምግብ ብቻ የሚበቃውን ይቀንስና ፡ በየእለቱ ወደ ሳንዲ ወደተከራየችው ሆቴል በመሄድ ፡ ክፍያውን ይፈፅምላታል ። ኑሮ መልካም በሆነላት ሰአት ደግነቷን ፡ ላልነፈገችው ሴት ከልጇ ጋር ሳትነጣጠል እንድትኖር በማድረጉ ደስተኛ ነው ።
................
እናም ለወራት እየተመላለሰ ፡ ዘጠኝ ሺህ ዶላር በየጊዜው ሰብስቦ ለሳንዲ ፒርስ ሰጥቷታል ። እናም ግን አንድ ቀን እንደተለመደው ክፍያውን ሊሰጣት ሲሄድ ሳንዲ ፒርስ ትልቅ የምስራች ይዛ ጠበቀችው ።
የስራ ማመልከቻ ያስገባችበት ባንክ ቤት ፡ ከዚህ በፊት ታገኝ ከነበረው ደሞዝ እጥፍ ክፍያ በመክፈል ሊቀጥራት በመወሰኑ ዛሬ ውል እንደፈፀመች ። እናም ከነገ ጀምሮ ቅድሚያ ብድር ወስዳ ፡ ጥሩ ቤት መያዝ እንዳሰበች ነገረችው ።
................
ያንን የጨለማ ጊዜ ፡ ከሰወች እየለመነ ያሳለፋትን ደግ ሰው መቼም እንደማትረሳው ፡ የሱም ህይወት የሚሻሻልበትን መንገድ እንደምትፈልግ ነገረችው ። ኩርቲስ ጃክሰን ደግነቷን ሳትነፍግ መልካም ስታደርግለት የነበረችው ሴት በሆነላት መልካም ነገር ሁሉ ተደሰተ ።
..............
በቻልነው መጠን መልካም እናድርግ መልካምነት መልሶ ይከፍላል ።

© ዋስይሁን

ቅንጭብጭብ
ሳንዲ ፒርስ...

>>Click here to continue<<

ቅንጭብጭብ

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)