TG Telegram Group & Channel
የኔ ማስታወሻ✍🏾በኪያብ🦋 | United States America (US)
Create: Update:

ክፍል ፫

        በ #ሄኖክ_በቀለ

     “መቼም አልሰማ ብለህ ክሴን እቀጥላለሁ” ካልክ የሆንከውን አብራርተህ ተናገር! አታደናግር!” ሽማግሌው ጮኸ።

     “ነገሩ እንዲህ ነው። የሆነ ቀን አለልማዴ ዓለሜን አስከትዬ ዛፍ ቆረጣ ሄድሁ። በእኔ ቤት ዛፍ ቆርጬ ገንዘብ ላገኝ ነው እንግዲህ። አዬ! ...ምነው በቀረብኝ። ዓለሜን አርቄ አስቀምጬ መጥረቢያዬን ይዤ ዛፉ ላይ ወጣሁና መተግተግ ጀመርሁ። ምን የተረገመው ቀን እንደሆነ እንጃ ከዛፉ ላይ አንዲት ሰላላ ቅርንጫፍ ብላት ብሠራት አልቆረጥ አለችኝ። ዛሬ ደግሞ የምን ተአምር ነው የገጠመኝ? እያልሁ ደጋግሜ ብመታት ጭራሽ እንደድንጋይ መጥረቢያዬን አንጥራ ትመልሳለች እንጂ ፍንክችም አትልም። ሠላሳ ዓመት ዛፍ ስቆርጥ እንዲህ ዓይነት ነገር ገጥሞኝም አያውቅም። የዚህ ሀገር እንጨት እንደምታውቁት ገራም ነው፤ እንኳን ቅርንጫፍ ግንዱም አስሬ ደኅና ካገኙት ይበቃዋል። ተንጋልሎ ያርፋል። የትንግርቴን ተፋጥጬ ሳነሣ ስለው፣ ሳነሣ –ስለው ...እልህ ይዞኝ እንጂ እጄ ዝሎ ኖሮ መጥረቢያው አምልጦኝ ቁልቁል ተምዘገዘገ። በዓይኔ ስከተለው...

   ዕድሉ ቀና ሳግ አንቆ አላናግር ስላለው አቀርቅሮ ጊዜ ወሰደ።

   “ለቅሶህን ተውና ቀጥል ተብለሃል!”

   “በዓይኔ ስከተለው እንደ ኪሩብዔል ሰይፍ ሲገለባበጥ ወርዶ ከየት መጣች ያላልኳት የልጄ አናት ላይ ሰመጠ። ይታያችሁ! ለእንጨት የሰነፈ መጥረቢያ ለልጄ ሲሆን በረታ። ለካ ዓለሜን አርቄ ባስቀምጣትም አሳዝኛት ሥሬ መጥታ ሽቅብ ስታየኝ ነበር። እኔ አፈር ልብላላት ...ሞት ሲጠራት እኮ ነው! ታዲያ ፈጣሪ ቢለው አይደል ሠላሳ ዓመት ሙሉ ገጥሞኝ የማያውቀውን የእዚያ ቀን መጥረቢያ ያመለጠኝ? ታዲያ ፈጣሪ ቢለው አይደል አድርጌ የማላውቀውን መጥረቢያ የሚያመልጠኝ ቀን ልጄን ይዤ የመጣሁት? ታዲያ ፈጣሪ ቢለው አይደል ከዓመት እስከ ዓመት የሚያሰቃያት ንዳድ ያንን ቀን ጋብ ያለላት? ታዲያ ፈጣሪ ቢለው አይደል ለእጅ የምትሰንፍ ቅርንጫፍ በስል መጥረቢያ የለገመቸው? ለምን “እንቢ! ስትለኝ አልተውኋትም? ምነው መጥረቢያውስ ካልጠፋ አውላላ መዳፍ የማታህል የልጄን አናት የመረጠው? ፈጣሪ ቢለው አይደል?”

    አዝማሪው ሐዋዝ ተነሣ
“መቼም እንደሰው ልጅ ጉድ የትም የለም። ጠማማ ዕድሉንም፣ ስንፍናውንም በፈጣሪ ማሳበብ ይወዳል። አንተ የአርባ ዓመት ጎልማሳ ስትሆን ምነው ልጅህን መጠበቅ አላወቅህበት? እጅህ እስኪዝል አንድ ቅርንጫፍ ቀጥቅጥ ያለህ ፈጣሪ ነው? ከእጅህ አሽቀንጥረህ ስትጥለውም ወደወረወርክበት ይሄዳል እንጂ መጥረቢያ እግር የለው፤ ዓይን የለው፤ ምን አድርግ ነው የምትለው? ይህን ድፍረት ለተናገርህበት ራሱ ቅጣት ይገባሃል። ኧረ ምነው! ስንት ነገር ጥለን ነው የመጣነው፤ ጊዜያችንን ባንፈጅ...?”

     ዕድሉ ቀና ክሱን ሰምቶ የሚደግፈው አለማግኘቱ አንገበገበው። ኀዘኑ እጥፍ ድርብ ሆነ። መናገሩ እንደማይጠቅም ሲሰማው ልቡ አመነታ። ቢሆንም የተበደለው አላለቀም። ቢያንስ “ተናግሬ ይውጣልኝ!” ብሎ ተቀበለ።

     “አይ ሐዋዝ! አንተ ጎረቤቴ ሆነህ የደረሰብኝን ሁሉ ስታውቅ እንዲህ ማለትህ አሳዝኖኛል። ጊዜ የተፈጀብህ ለምኑ ነው? አናውቅም የት ውለህ የት እንደምታነጋ? ሌላ ምንም አልልህም አንተም ሴት ልጅ አለችህ። በልጅ የመጣ እንዴት እንደሚያንሰፈስፍ ደርሶብህ እየው።” ንግግሬ እንዳልጠቀመ አይቼያለሁ። ቢሆንም ልናገረውና የመጣው ይምጣ...”

   ዋናው ዳኛ አንካሳ እግራቸውን በእጆቻቸው እያመቻቹ የሚሆነውን በዝምታ ይሰማሉ።

“ይቅር ብዬ አልፌው እንጂ የተበደልሁትስ ይህ ብቻ አልነበረም። ከሆነ አይቀር ግን ይኸው ስሙት።

             ይቀጥላል.........
      @Mahder_Kasahun🦋

>>Click here to continue<<

የኔ ማስታወሻ✍🏾በኪያብ🦋

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)