TG Telegram Group & Channel
ኢንፎክን የመጻሕፍት እና የመረጃ ማዕከል | United States America (US)
Create: Update:

የተጠላው እንዳልተጠላ፣ የያዘው መንገድ
ገንፎን አጥላልቶ፣ ለሙቅ ማጎብደድ!!!
-©ገረመው ፀጋው(@gere_perspective)-

አለማየሁ ገላጋይ (የእኔን ምስክርነት የማይሻ) ጎበዝ ደራሲ ነው። ለስነፅሁፍ ራሱን አሳልፎ ሰጥቷል። ተፈትኗል፣ ዋጋ ከፍሏል፣ በዚያውም ልክ ብዙዎቹ ያልታደሉትን መከበርና ተቀባይነትንም አግኝቷል። አሌክስ ሲናገር ጆሮዎች ሁሉ ይከፈታሉ። ንግግሩ በራሱ በዜማ የታጀበ ነውና የአድማጭን ቀልብ ይገዛል። በየጊዜው አዳዳስ ሃሳቦችንና የአፃፃፍ ዘዴዎችን የሚያስተዋውቀን ለትውልዱ የተሰጠ የስነፅሁፍ ገፀበረከት ነው። ይህም በመሆኑ ይሄ ፅሁፍ ከአለማየሁ ገላጋይ የስነፅሁፍ ችሎታ ጋር በተነሳ ለውዳሴም ለወቀሳም የተወደረ አይደለም።

በምድር የሚኖር የሰው ልጅ ሁሉ ፖለቲካዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ መሆኑን ሁላችንም እናስተውላለን። ይሄ ቀውስ በመጠን ይለያይ እንደሆነ እንጂ የሌለበት የዓለም ንፍቀ ክበብ የለም። በርግጥ ችግሮች አፍሪካ ውስጥ ውስብስብና የጎሉ ናቸው። ከበርካታ አፍሪካ ሃገራት አንፃር ሲታይ ግን የኢትዮጵያ ችግር ቀለል ሊል ይችል ይሆናል እንጂ የበለጠ አይደለም። ይሄ ማለት ግን የኛ የኢትዮጵያውያን ችግር የሚናቅና ለይደር የሚተው ነው ማለትም አይደለም። በርካታ ውስብስብ ችግሮች አሉብን። ዘርፈ ብዙ ቀውስና ችግር መሃል ነው ጥርሳችንን የነቀልነው። የምንተነፍሰው፣ የምናስበው ሁሉ ችግር ችግር ይሸታል።

የአለንበትን የችግር መጠን ለመግለፅ የዓለማችን ጉምቱ ፀሃፊዎች ሁሉ ተሰብስበው ቃል ቢያዋጡ እንኳን ከውስብስብነቱ አንፃር በትክክል ሊገልፁት ሁሉ የሚችሉ አይመስለኝም። 'መልሱን ተይው ጥያቄው ከገባሽ ይበቃል' እንዲል እያዩ ፈንገስ፣ እንደሃገር የጋራ ችግራችንን በትክክል ለይቶ የሚነግረን ሰው ቢገኝ ትልቅ ባለውለታችን ለመሆን ይበቃል።

ከዚህ ጋር በተገናኘ አለማየሁ ገላጋይ ሃገሩና የሚኖርበት ማህበረሰብ የሚገኝበት ቀውስ አስደንግጦታል። ሁላችንም አይተን እንዳላየንና ምን አገባኝ ብለን የተውናቸው የጋራ አዘቅቶቻችንን እንደዋዛ ሊተዋቸው አልፈለገም። መደንገጥና መታዘብ የአንድ ጎበዝ ደራሲ Motive ነው። ቀጣዩ ጉዳይ የሚሆነው ተደራሲን በሚገባው ቋንቋ ማስደንገጥ ይሆናል። ይሄኔ ነው አሌክስ ሙሉ አቅሙንና ችሎታውን ተጠቅሞ ሊያስደነግጠን ያልቻለው።

ችግር ውስጥ መሆናችንን የተናገረበት ቋንቋ የሚጋባ አይደለም። አሌክስ ካለው የስነ ፅሁፍ አቅም አንፃር በተጠላው እንዳልተጠላ ላይ ሲሶውንም የተጠቀመ አይመስልም። በቂ መደንገጥን መፍጠር አልቻለም። አንድን አንባቢ መፍትሔ አብሮህ እንዲፈልግ ካሰብክ የጋራ ችግር አንስተህ፣ ተንትነህና አባብለህ ልታስደነግጠው ይገባል። የደነገጠ ሰው ደግሞ የችግሩን መፍትሔ አብሮህ ባይፈልግ እንኳን የምታቀርብለትን ምርጫ ተጣድፎ ይመርጣል፤ የምትወስንለትን ውሳኔ ሳያቅማማ ይቀበላል።

አሌክስ በማህበረሰቡ ልብ ውስጥ ያለውን እግዜር ሊመረምር ተነስቷል። የዋዛ ድፍረት አይደለምና 'የነብሩን ጅራት ጨብጧል' ልንለው እንችላለን። ከዚህ በኋላ ማፈግፈግ የለም፣ ጅራቱን አጥብቆ ይዞ በጠንካራ አመክንዮ መሞገት ይኖርበት ነበር። አሌክስ ግን ያነሳውን ርዕሰ ጉዳይ የማይመጥን ግልብ Premises ደርድሮ ለውሳኔ ይጣደፋል። የሚከተለውን አንቀፅ እንመልከት....

[“አንድ ጊዜ ለአንዲት መንደር የጉድጓድ ውሃ ልናወጣ ማስቆፈር ጀመርን። ግማሽ ስንደርስ ጉድጓዱ በድንጋይ ይደፈናል። አሁንም አውጥተን ስንጨርስ ድጋሚ በድንጋይ ይሞላል። ለምን? ብለን መንደሩን ስናጠያይቅ እንዲህ የሚያደርጉት ወጣቶቹ ናቸው። ምክንያታቸውም የከንፈር ወዳጆቻቸውን የሚያገኙት ውሃ ሊቀዱ ራቅ ብለው ሲሄዱ ስለሆነ መንደር ውስጥ ውሃ ከወጣ አያገኙዋቸውም፡፡ ትንሽ ራቅ ብለን ጉድጓዱን አስቆፈርን።” ገፅ 6] ይህ አንቀፅ ወደ አንባቢ ልብ ውስጥ የመጋባት አቅሙ አንድ ለዛ ቢስ ኮሜዲያን ሳይዘጋጅ መድረክ ላይ ከሚቀልደው ቀልድ ያነሰ ነው።

ሌላ ቦታ ላይ ጥያቄ ማጋነን መልስ እንደሚያቀጭጭ አሌክስ የተረዳ አልመሰለኝም። [“አንዲት ልጅ ወዛ ብላለች፣ ጋይቴ ደስታ እሚባል ነበርና እሱ እየረዳት ተነስታ ፍሎሃ ወረደች ፤ ብዙ ሰው የተቀመጠው እዚያ ነው፣ ይኸ ስደተኛው ሁሉ ተቀበለና እዚያ አረደና በላት፡፡ ልጆቻቸውን ጥቃቅኖቹን እያረዱ የበሉ ሴቶች ብዙ ናቸው፡፡" ገፅ 93]

እውነቱን ለመናገር ስለመጨካከን ካነሳን እኛ ጨካኞች ነን። ጭካኔያችን ግን የራሱ የእኛነት ለዛ እና አይነት አለው። በእንተማርያም ብሎ ለምኖ የሚበላ ሰው የተሰጠውን ነገር ሁሉ አለመብላቱን አሌክስ ዋጋ አልሰጠውም።  መከልከል ስንፈልግ "እምቢ" ከማለት ይልቅ "ውይ አሁን ጨረስኩ፣ አለቀብኝ" ብለን መዋሸታችን የእኛ የብቻችን ክፋት መሆኑንና አብረን ለመቀጠል የሚያስችል ዋጋ እንዳለው አልተረዳም።(ማስተዋል አልፈለገም)

ጣት ጠቋሚ ሃሳቦች፣ አንኳሳሽና የሚፈርጁ (ሰዳቢ) ቃላት እንዴትም ሆነው በሚያምር ቋንቋ ቢፃፉ በሰዎች ልብ ውስጥ ቦታ አግኝተው ለለውጥ የማነሳሳት አቅማቸው ደካማ ነው።

["ጥቁር ሽሮ፣ ነገሩ የጥንት ነው። ንጉሳውያን ቤተሰቦች፣ መሣፍንቶች፣ መኳንንቶች፣ ጳጳሳትና፣ ሊቆች ሁሉ በፆም ወቅት በምስጢር የሚገባበዙት ነው።"
"እንዴት ያለ?"
"ለፆም መያዣ የታረደ ሥጋ ሲተርፍ ቋንጣ ተደርጎ ይወቀጣል። ቡን ብሎ ሲደቅ ከሽሮ ጋር ተቀላቅሎ ትክን ተደርጎ ይሰራና በምስጢር 'ጥቁር ሽሮ ይብሉ' እየተባባሉ ይገባበዛሉ።" ገፅ 85]

አዲስ ሃሳብ ወደሰዎች ማጋባት የፈለገ የለውጥ ሰው አሮጌውን በመስደብ ላይ ከተጠመደ ሊሳካለት አይችልም። መጀመሪያ ለመደማመጫ የሚሆን የጋራ መሬትን መፍጠር ያስፈልጋል። አለማየሁ አሮጌውን መስደቡና ማንቋሸሹ ከደከመው በኋላ አጠገቡ አዲስ ቤት ሊሰራ ሞክሯል። አሮጌውን አስንቆ 'ኑ ወደ እኔ' እያለ የሚያስጎመጀን አዲሱን ቤት እንይለት ብለን ስንመረምር የሚከተለውን እናገኛለን።

#የሚቀጥል

>>Click here to continue<<

ኢንፎክን የመጻሕፍት እና የመረጃ ማዕከል

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)