TG Telegram Group & Channel
ኢንፎክን የመጻሕፍት እና የመረጃ ማዕከል | United States America (US)
Create: Update:

የህይወትን ጣዕም የምንለካው በመነካታችን ልክ ነው። በዚህ ምድር ላይ ስትኖር ማድረግ ያለብህ ወይም የሌለብህ የሚባል የተሰላ ቀመር የለም። ምናልባት የምታደርግበትን መንገድ ልትመርጥ ይገባህ ይሆናል። ልብህን በክፋት እንዳታነሳሳው፣ የተቀደሰ የተባለ ተግባርን እንኳን ሳይቀር በክፋት ባትፈፅም መልካም መሆኑ የታመነ ነው። ከዚህ በዘለለ ግን ላንተ ትርጉም የሰጠህ ነገር ሁሉ ዓለምህ ነው። ባቲና አንቺሆዬን ትተህ በሩቅ ምስራቅ ዋሽንት ነፍስህን ታሳርፍ ይሆናል። ከሳሽ የለብህም። መኖርህን የምትለካውም የምትመሰክረውም አንተው ነህ። በዙሪያህ ካሉ ነገሮችና ከምትወዳቸው ነገሮች ጋር ሁሉ ምን ያህል ከልብህ Connect አድርገሃል ይሆናል የመኖርህ ትርጉሙ።

እናትና አባትህ በህይወት ካሉ በደንብ አስጨንቀህ ልጅ ሁንላቸው። ብልጭታህ ቀለሟ ይደምቅ ዘንድ ፍቅርን ስትሰጥ አትሰስት። በሚወዱህ ሰዎች ልብ ውስጥ ያለ ቀመር ያለ ስሌት ደምቀህ ታይ። በቃ! በዚህ መንገድ ሁሉንም መከፋፈያዎች አልፈህ የራስህ ዓለም ንጉስ ትሆናለህ። ይሄ ሁሉም ነገር የሚሆነው ግን በፍቅርና ያለስስት ያለስሌት በሚኖር ዛሬ ነው። ከዛሬ ጋር በደንብ Connect ሁን። ዛሬ ካሉህ ወዳጆች፣ ጓደኞች፣ ቤተሰቦች፣ እንዲሁም ሃብት፣ አቅምና ጊዜ ጋር ስምምነት ፍጠር። ስለምታገኘው 1 ሚሊዮን ብር እያሰብክ በእጅህ ላይ ላለው 1ሺህ ብር ባዕድ አትሁን።

ስለ Connection ስናወራ ነገሮችን ሁሉ Sentimental ለማድረግ ሳይሆን ሁሉም ሰው የየራሱን Reality ቀለም፣ ውብና ደማቅ ማድረግ የሚችልበት መንገድ መሆኑን ለመጠቆም ነው። የየቀን አጀንዳዎቻችን የምር እኛን ይመለከታሉ ወይ የሚለው ጥያቄም ወሳኝ ነው። ለዚህም ነው ትርጉም የሚሰጠን ነገር ላይ ማተኮር ያለብን። ዓለም የምናያትን ያህል ሰፊ አይደለችም። ዓለም የምትጠፋው በኒዩክለር ቦንብ ወይም በዳግም ንፍር ውሃ የሚመስላቸው ብዙ ሰዎች አሉ። ዓለም የምትጠፋው በሰዎች ልብ ውስጥ ነው። አንድ ልጅ ያላት እናት ልጇ የሞተ ቀን ዓለሟ ትጠፋለች። አንዲት ውሻ ያለችው የጎዳና አዳሪ ውሻውን መኪና የገጫት ቀን ዓለሙ ትጠፋለች። Value የምንሰጣቸውን ነገሮች እንዲበዙ መጣርና ከነዚህም ነገሮች ጋር በፍቅር መቆራኘት ህይወትን ውብና አጓጊ ከማድረግ አልፈው የነገዋን ፀሃይ እንድንናፍቅ ያደርጉናል።

በዓለሙ ካለው ሁሉ አንተ የምትወደውና Value የምትሰጠው ነገር የመኖርህ ምክንያት ይሆናል። Purpose ይሰጥሃል። የሰው ልጅን ከሌሎች ፍጡራን የሚለያቸው ነገር አንዱ ኪነጥበብ ነው። የኪነትንና የሰው ልጅን ቁርኝት ስናስብ ሁሉም ነገር በጥቅምና በውለታ የሚቀየር እንዳልሆነ ይገባናል። ግጥም የሚወድን ሰው ለምን ግጥም ወደድክ ብትለው ምክንያታዊ መልስ አይመልስልህም። ትያትር ለማየት 200 ብር የሚከፍልን ሰው ለምን በርገር አትበላበትም ብትለው የሚያቀርብልህ ምክንያት አጥጋቢ ላይሆን ይችላል። ግን በቃ 'በርገር ይበልጣል' ወይም 'ትያትር ይበልጣል' የሚለን የተሰላ ቀመር የለም። ሰው Value የሰጠው ነገር ይበልጣል። ከላይ ያነሳሁላችሁን ነጥቦች በሙሉ በጥበብ ሊነግረን የሚችልና እኔም Value ሰጥቼ ከልቤ የወደድኩትን አንድ ነገር ልጠቁማችሁ። THIS IS US

በቤተሰባዊ ዘውግ የምንጊዜም ምርጡና እጅግ ተወዳጁ THIS IS US ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ባለፈው ሳምንት አየር ላይ በዋለው የመጨረሻውና 108ኛው ክፍል ላይ "If something makes you sad when it ends, it must have been pretty wonderful when it was happening" በማለት ተመልካቾቹን ተሰናብቷል።

በርግጥ እንደኔ ላሉ ተመልካቾቹ ይሄ ቃል ትልቅ መፅናኛ ነበር። አንድም ላለፉት 8 ዓመታት በየሳምንቱ ረቡዕን ጠብቄ ያየሁት ድራማ 'ጨርሻለሁ' ማለቱ የሚፈጥረው ጥሩ ያልሆነ ስሜት በመኖሩ፣ እንዲሁም እንደማንኛውም ሰው በህይወት ውጣውረድ ውስጥ የመጨረሻ የተባሉ ቀናትን ደጋግሜ አሳልፌም ስለማውቅ። This Is Us ሰዎች እንዲያዩት የተሰራ ፊልም አይደለም፣ ራሳቸውን አስገብተው እንዲተውኑት እንጂ። ወደትወናው ለማስገባት triggering button አድርጎ የሚጠቀመው Perfect Melody አለው። ማንም እሱን Escape ማድረግ አይችልም። ለመሳቅ የቀልዱን መጨረሻ መስማትን አይጠይቅም። ለማልቀስም የተዋንያኑን የፊት ገፅታ መመልከት አያስፈልግም።

This Is Us የቤተሰብ ዘውግ የሚመቻቸውን ተመልካቾች ለማርካት የተሰራ ድራማ አይደለም። ይልቁንም ለሰው ልጆች ሁሉ የቀረበ Therapy ነው። ልክ እንደ ርዕሱ ስለ እኛ ነው የሚያወራው። እኛ ማለት ደግሞ ልጅነት፣ ወጣትነት፣ ጉልምስና፣ እርጅና፣ እናትነት፣ አባትነት፣ ሚስትነት፣ ባልነት፣ ፍቅረኛነት፣ አያትነት፣ አማችነት፣ አማትነት ከመሳሰሉት ነገሮች አናልፍም። ተወልደናል ወይም ወልደናል፣ ወደናል ወይም ተወደናል። በዚህ በዚህ ውስጥ ሁሉ እኛ የተነካንባቸውን ወይም ወደፊት የምንነካባቸውን ነገሮች የቴሌቪዥን መስኮት ያመጣልናል። ርዕሱን ሰጥቶን ይሄዳል። ትወናው ከኛ ነው፣ ምክንያቱም This is Us.

This is Us'ን ከልጆቻችሁ ጋር እዩት፣ ከወላጆቻችሁ ወይም አሳዳጊዎቻችሁ ጋር እዩት፣ ከባለቤታችሁ ጋር እዩት፣ ከፍቅረኛችሁ ጋር እዩት፣ ለብቻችሁም እዩት ለውጥ የለውም። ሁሉም ቦታ ላይ እናንተ የምትነኩበትን ርዕስ ያመጣላችኋል። አታመልጡም፣ ሊያስቆዝማችሁ ሳይሆን ራሳችሁን እንድትፈትሹበትና እንድትመለከቱት ጊዜ ለመስጠት ነው። የሚያብሰለስላችሁ ጉዳይ እናንተ ጋር ብቻ ያለ ነገር አለመሆኑን ያሳያችኋል። ከዚያ ደግሞ ማምለጫ መንገድ መኖሩንም ያሳያችኋል። በመደለል ሂደት ሳይሆን በተጨባጭ አመክንዮ ይሞግታችኋል። በቃ its a complete therapy. በስድስት ምዕራፍ የተደራጁ 108 ክፍሎች የናንተን አይኖች ይጠብቃሉ። የፒርሰን ቤተሰቦች ስለብዙ የሰውነት አጀንዳዎች ሃሳብ አላቸው። ፊልም እንደዚህ መሰራት ይችላል እንዴ እስክትሉ ድረስ ያስደምሟችኋል።

"Take the sourest lemon that life has to offer and turn it into something resembling lemonade"

This Is Real, This Is Love, This Is Us! #MoviesToWatch

©ገረመው ፀጋው (@gere_perspective)

#INFOKEN_BOOKS_AND_INFORMATION_CENTER

Join us @infokenamu

>>Click here to continue<<

ኢንፎክን የመጻሕፍት እና የመረጃ ማዕከል

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)