- ክርስቶስ ተጸነሰ-ተወለደ ስንል ለዚህ ሁሉ ምሥጢር ማካተቻና የድኅነታችን መጀመሪያ: የመመኪያችን ዘውድና የንጽሕናችን መሠረት ድንግል ማርያም ናትና ከፈጣሪ ቀጥሎ ታላቅ ክብር: ምስጋና: ስግደትና ውዳሴ ለእርሷ ይገባታል:: መድኅናችን ክርስቶስ ያዳነን በእርሷ ምክንያት ነውና::
- ሠለስቱ ምዕት [ ፫ መቶ ፲፰ [318] ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት) ይህንን ምሥጢር ሲያደንቁ እንዲህ ብለዋል :-
- በሥጋ ማርያም ጌታ ተጸነሰ
- በሥጋ ማርያም ጌታ ተወለደ
- በሥጋ ማርያም ጌታ አደገ
- በሥጋ ማርያም ጌታ ተጠመቀ::
- በሥጋ ማርያም ጌታ አስተማረ
- በሥጋ ማርያም ጌታ ተሰቀለ
- በሥጋ ማርያም ጌታ ሞተ
- በሥጋማርያም ጌታ ተነሳ
- በሥጋ ማርያም ጌታ ዐረገ
- በሥጋ ማርያም ጌታ በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ
- በሥጋ ማርያም ጌታ ዳግመኛ በሕያዋንና ሙታን ላይ ይፈርድ ዘንድ ከመለኮቱ ኃይል ጋር ይመጣል:: [ መጽሐፈ ቅዳሴ ]
- በዚያውም ላይ ለዘለዓለም ድኅነት የምንመገበው የጌታ ሥጋና ደም መለኮት የተዋሐደው የድንግል ማርያም ሥጋና ደም ነው::
" ለድንግል ማርያም ክብርና ውዳሴ ከስግደት ጋር ይሁን !!! "
- የድንግል ማርያም ልጅ አማኑኤል ክርስቶስ በርሕራሔው ይማረን:: ከበረከተ ልደቱም ያሳትፈን::
🕊
[ † ታሕሳስ ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. አማኑኤል አምላካችን
፪. በዓለ ጌና ስቡሕ
፫. ዕለተ ማርያም ድንግል
፬. ፻፸፬ "174" ሰማዕታት [ የቅዱስ ዻውሎስ ማሕበር ]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱሳን [ አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ ]
፪. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
፫. ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
፬. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ
፭. ቅዱስ አባዲርና ቅድስት ኢራኢ
" የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ከእርስዋ የተጸነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ:: ልጅም ትወልዳለች:: እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ:: በነቢይ ከጌታ ዘንድ:-
'እነሆ ድንግል ትጸንሳለች:: ልጅም ትወልዳለች:: ስሙንም አማኑኤል ይሉታል::' የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኗል:: ትርጉዋሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው::" [ ማቴ.፩፥፳]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
>>Click here to continue<<