TG Telegram Group & Channel
ግጥም እናጣጥም | United States America (US)
Create: Update:

#nomore #ethiopia
ይገርማል!
የነጭ አታላይ ቀማኛ ሀበሻን ሊቀራመተው።
አልገዛም ያለን ጫንቃ
ዘመናዊነት አስታኮ በትርኪምርኪ ሊሰብረው።
ሲያሴር ሲያብር ለዘመናት
የየመንን መራር ፅዋ አፉን ለጉሞ ሊግተው።
ዝም አለ ሀበሻ ታጋሽ ሊታዘብ የማሰብ ጥጉን።
የመራቀቁን ከፍታ የሀያልነት ድንበሩን።
እሱ ግን አርምሞ አልገባው ቁማሩን በኛ ቀመረ።
በይፋ እውነትን ቀብሮ ለሀሰት ቆሞ ዘመረ።
ድህነትን ተንተርሶ ህልውናን መዘበረ።
ምናለ...
ምናለ ታሪክን ቢቃኝ የኋሊት ሄዶ ተጉዞ።
ነጭነት እንደማይሰራ በሀበሻ አፈሙዝ መዞ።
ፋሽሽትን ጠይቅ ይንገርህ የማይጨው ገድል ይናገር።
ደመ ሞቃት ቁጡ ናቸው ሲመጡባቸው በሀገር።
ይናገር ቀስተ ደመናው የሰማይ ማህተም ፊርማ።
ኢትዮጵያ ያነባች እንደው ፀባኦት እንደሚሰማ።
ቃላችን እውነት አዘል ነው ጣልቃ ገብነት ይበቃል።
ሀበሻ ለሆዱ ብሎ ሀገሩን መቼ ይሸጣል?
ይበቃል!!!!
ከ ፍፁም ጥበበ
ለአስተያየት 👉 @ft2194
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae

Forwarded from የፍፄ ግጥሞች (Fitsae T)
#nomore #ethiopia
ይገርማል!
የነጭ አታላይ ቀማኛ ሀበሻን ሊቀራመተው።
አልገዛም ያለን ጫንቃ
ዘመናዊነት አስታኮ በትርኪምርኪ ሊሰብረው።
ሲያሴር ሲያብር ለዘመናት
የየመንን መራር ፅዋ አፉን ለጉሞ ሊግተው።
ዝም አለ ሀበሻ ታጋሽ ሊታዘብ የማሰብ ጥጉን።
የመራቀቁን ከፍታ የሀያልነት ድንበሩን።
እሱ ግን አርምሞ አልገባው ቁማሩን በኛ ቀመረ።
በይፋ እውነትን ቀብሮ ለሀሰት ቆሞ ዘመረ።
ድህነትን ተንተርሶ ህልውናን መዘበረ።
ምናለ...
ምናለ ታሪክን ቢቃኝ የኋሊት ሄዶ ተጉዞ።
ነጭነት እንደማይሰራ በሀበሻ አፈሙዝ መዞ።
ፋሽሽትን ጠይቅ ይንገርህ የማይጨው ገድል ይናገር።
ደመ ሞቃት ቁጡ ናቸው ሲመጡባቸው በሀገር።
ይናገር ቀስተ ደመናው የሰማይ ማህተም ፊርማ።
ኢትዮጵያ ያነባች እንደው ፀባኦት እንደሚሰማ።
ቃላችን እውነት አዘል ነው ጣልቃ ገብነት ይበቃል።
ሀበሻ ለሆዱ ብሎ ሀገሩን መቼ ይሸጣል?
ይበቃል!!!!
ከ ፍፁም ጥበበ
ለአስተያየት 👉 @ft2194
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae


>>Click here to continue<<

ግጥም እናጣጥም






Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)